Get Mystery Box with random crypto!

#DebreBerhanUniversity የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) | Tikvah-University

#DebreBerhanUniversity

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በሥራ ገበታቸው ላይ ከታዩ አንድ ወር እንዳለፋቸው አል-ዐይን አማርኛ የተቋሙን አንድ አመራር በመጥቀስ ዘግቧል፡፡ ፕሬዝዳንቱ "የት እንዳሉ እንደማይታወቅ" ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ከሦስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል።

"ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በሥራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ለአል-ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡

"ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ ፕሬዝዳንቱ የት እንደሔዱና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ያሉት የተቋሙ አመራር፤ "ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ኃይሎች መታገታቸውን ሰምተናል" ሲሉም አክለዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መሰወርን አስመልክቶ አል-ዐይን አማርኛ የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚኒስቴር እና የደብረ ብረሃን ከተማ ፖሊስ ምላሽ እንዲሰጡ ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ገልጿል። የፕሬዝዳንቱ ቤተሰብ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡ አል-ዐይን ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረትም አልተሳካም።

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር የሚሉትን ወደናንተ እናደርሳለን፡፡ #አልዐይንአማርኛ

@tikvahuniversity