Get Mystery Box with random crypto!

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙና ዘንድሮ የመልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ | Tikvah-University

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙና ዘንድሮ የመልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በበጎ ፍቃደኛ መምህራን በመታገዝ በተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የማስጀመሪያ መርሐግብር አከናውኗል፡፡

በጉዲኦ ዞን ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አምስት ትምህርት ቤቶች ላለፉት ሦስት ዓመታት አንድም ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ አለማሳለፋቸውን የዲላ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እና ስነ-ባህሪ ተቋም ያደረገው ጥናት ያሳያል፡፡

በመሆኑም የማጠናከሪያ ትምህርቱ በጌዴኦ ዞን የሚታየውን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ማነስን ለማሻሻል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ ለአንድ ወር ከአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን፤ በተመረጡት ትምህርት ቤቶች አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity