Get Mystery Box with random crypto!

'ትምህርት ለትውልድ' በተባለውና የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅ | Tikvah-University

"ትምህርት ለትውልድ" በተባለውና የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት መሰብሰቡን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ባለፈው ዓመት መጨረሻ በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ፤ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አሰተዳደሮች ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መሰብሰቡን በሚኒስቴሩ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል።

በ2016 ዓ.ም ብቻ በትምህርት ለትውልድ መርሐግብር ከ4 ሺህ በላይ አዳዲስ የቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

የትምህርት ቤቶች ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ሥራ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

@tikvahuniversity