Get Mystery Box with random crypto!

#Update የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ2016 የትምህርት ዘመን | Tikvah-University

#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia