2022-05-18 17:51:27
የሥራ ፈጠራ በኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ ውስጥ እንዲካተት ተጠየቀ። ትኩረቱን የሥራ ፈጠራን ማሳደግ ላይ ያደረገው "ብራይት ፊውቸር ኢን አግሪካልቸር" ፕሮጀክት እ.አ.አ. ከ2019 ጀምሮ በኢትዮጵያ በመተግበር ላይ ይገኛል።
በተለይም በግብርና ዘርፍ ያለውን የሥራ ፈጠራ ለማሳደግ እየሠራ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ሰለሞን ሞገስ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በአራት ሚሊዮን ዩሮ በጀት ለ4 ዓመታት የሚተገበረው ፕሮጀክቱ፤ በተለይም የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት መምህራን በሥራ ፈጠራ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ይሠራል። ይህም ከቴክኒክና ሙያ ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች ድክመት የሆነውን የዕውቀት ችግር ለመፍታት የመጀመርያ ዕርምጃ መሆኑን አክለዋል።
በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች በሚገኙ ሰባት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚተገበረው ፕሮጀክቱ፤ በእስካሁኑ ቆይታው የሥራ ፈጠራን በተመለከተ መምህራን የዕውቀት ችግር እንዳለባቸው ለይቷል ብለዋል።
በተጨማሪም ለቴክኒክና ሙያ የሚመደበው በጀትና የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ በሚፈለገው ልክ ውጤታማ አለመሆኑን ይናገራሉ። በፕሮጀክቶች ከሚገኘው ድጋፍ በተለየ በዘላቂነት አቅማቸውን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ የሥራ ፈጠራ ግንዛቤ ለማሳደግ ብሔራዊ የሥራ ፈጠራ ትምህርት ፖሊሲ ሊኖር እንደሚገባም ሰለሞን (ዶ/ር) ጠቁመዋል።
ትምህርቱ ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ድረስ ራሱን ችሎ መሰጠት እንዳለበትም አክለዋል። #ሪፖርተር
@tikvahuniversity
24.8K viewsedited 14:51