Get Mystery Box with random crypto!

Tikvah-University

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 214.08K

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 250

2022-05-25 11:47:52
#HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎቹ ተቋማዊ ገለጻ እየሰጠ ነው።

ገለጻው በዩኒቨርሲቲው ደንብና መመሪያዎች፣ በተቋሙ ስለሚቀርቡ አገልግሎቶች እና ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ተግባራት የተመለከተ መሆኑ ተገልጿል።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን የተመደቡለትን 5 ሺህ 180 አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎችን ተቀብሏል።

በተጨማሪም በተለያየ ምክንያት ባለፈው የትምህርት ዘመን ትምህርታቸውን ያቋረጡ 300 የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ገለብተዋል።

በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ነጻ የትምህርት እድል ያገኙ የሶማሊላንድ፣ የደቡብ ሱዳን እና የጅቡቲ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው መግባታቸውን የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኡርጌ (ፕ/ር) ገልጸዋል።

@tikvahuniversity
15.6K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 11:03:39
#Golden_Sales_and_Marketing_Institute

ቢዝነስዎን ማሳደግ ይፈልጋሉ?
ክህሎትዎንስ ማዳበር ይፈልጋሉ?

ጎልደን የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ተቋም

ፕሮፌሽናል የሽያጭና ክህሎት ስልጠና
ቢዝነስዎን ለማሳደግ የሚያስችል
ስልጠና
ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና
የሥራ እድሎች
የሙያ ብቃት COC ማረጋገጫ
አዲስ ክህሎት ለመገንባት

አድራሻ፦ ቦሌ፣ መገናኛ፣ ፒያሳ እና ሜክሲኮ ያገኙናል

ለበለጠ መረጃ፦

0941552035
0941811825

#Golden_Sales_and_Marketing_Institute
14.5K viewsedited  08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 10:50:18
#UniversityOfGondar

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 30ኛ የምርምር ጉባኤና የቴክኖሎጅ ሽግግር ኤግዚቢሽን ማካሄድ ጀምሯል።

ሀገር ዐቀፍ ጉባኤው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም ለሦሥት ቀናት ይካሄዳል።

በሰሜኑ ጦርነት በአማራ እና አፋር ክልሎች የደረሰውን ውድመት መልሶ ማቋቋም እንዲሁም ቴክኖሎጂ እና ሥራ ፈጠራ ጉባኤው ከሚመክርባቸው ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ።

ሀገር ዐቀፍ ጉባኤው በኮቪድ-19 እና በበሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ላለፉት ሦሥት ዓመታት ሳይደረግ ቆይቷል።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከግንቦት 15/2014 ዓ.ም ጀምሮ የምርምር ሳምንት እያከበረ ይገኛል።

@tikvahuniversity
15.6K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 17:15:20
#AddisAbabaEducationBureau
#MinistryOfEducation

"ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ክፍል ትደግማላቸሁ" በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ተማሪዎች የ2014 የትምህርት ዘመን የማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ እየተዘጋጁ መሆኑን የገለጸው ቢሮው፤ ኃላፊነት የጎደላቸው አካላት ሆን ብለው ተማሪዎችን ለማዘናጋት ዘንድሮ ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለም የሚል ሀሰት መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ገልጿል።

መረጃው ፍጹም ከእውነት የራቀ እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዘ ከትምህርት ሚኒስቴር የወረደ አቅጣጫ የሌለ መሆኑን ቢሮው አረጋግጧል።

በተመሳሳይ "ሁሉም የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባሉበት የትምህርት ደረጃ እንዲቀጥሉ ተወስኗል" በሚል የሚዘዋወረው መረጃ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የተቋሙን ስም እና አርማ በመጠቀም የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎችን በመልቀቅ ውዥንብር እየፈጠሩ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ማየቱን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

በመሆኑም ተማሪዎች የሚሰራጩት መረጃዎች የተሳሳቱ እና ከእውነት የራቁ መሆናቸውን አውቀው ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጠይቋል።

@tikvahuniversity
14.2K views14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 16:06:03
#GambellaUniversity

በ2014 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 29 እና 30/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (6)
• አንሶላ እና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ www.gmu.edu.et ይመልከቱ።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@tikvahuniversity
14.4K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 15:53:16
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሃ ግብር የ2ኛ ዓመት (2013 ባች) የ2ኛ ሴሚስተር ምዝገባ ግንቦት 17 እና 18/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

የ2ኛ ዓመት 2ኛ ሴሚስተር ተማሪዎች ትምህርት ምዝገባ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

(ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል። )

@tikvahuniversity
14.1K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 11:13:02
#ScholarshipTip

መልቲቾይስ አፍሪካ/DSTV በየዓመቱ ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች የአንድ ዓመት የፊልም ጥበብ ስኮላርሺፕ ይሰጣል።

የመልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ የስኮላርሺፕ ዕድል ወጣት ባለሙያዎችን ኬንያ በሚገኘው የመልቲቾይስ አካዳሚ የፊልም ጥበብ እውቀታቸውን የሚያጎለብቱበት ዕድል ይፈጥራል።

እድሚያችሁ ከ18-30 የሆነ ወጣቶች እስከ ግንቦት 26/2014 ዓ.ም ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም ማመልከት ትችላላችሁ፦

www.multichoicetalentfactory.com

ለበለጠ መረጃ፦

https://cte.multichoicetalentfactory.com/Master/entrycriteria

(ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
17.5K views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 11:11:04
የት ለመማር ወሰኑ?

በ Software Engineering እና በ Information Technology and Systems በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርትዎን ለመማር ወደ #ቢትስኮሌጅ ቢመጡ አብዝተው ያተርፋሉ።

በአራት ዓመት ውስጥ በዲግሪ ብቻ ሳይሆን ብቁ ሰራተኛ ሆነውም ይመረቃሉ።

ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መምህራን፣ ጥራታቸውን የጠበቁና በዘመናዊ መልክ የተደራጁ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ-መፅሀፍት፣ የኮምፒዩተር ላብራቶሪዎች እና እጅግ ዘመናዊ የአይቲ መሠረተ ልማት #በቢትስኮሌጅ የተሟሉ ናቸው።

ለማመልከት እና ለበለጠ መረጃ፦

ድረ-ገጽ www.bitscollege.edu.et

0982363636
0978028655

#BITSCollege
15.3K viewsedited  08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 10:36:13
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 9ኛ ሀገር ዐቀፍ የማህበራዊ ሳይንስ የምርምር ጉባኤ እያካሄደ ነው።

የምርምር ጉባኤው በመጀመሪያ ቀን ውሎው "በኢትዮጵያ የተከሰተው ግጭት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ" በሚል ጭብጥ ላይ ተወያይቷል።

ትላንት ሰባት ተመራማሪዎች ሥራቸውን አቅርበው ምከክር ተደርጎባቸዋል፡፡

በጉባኤው የዛሬ ውሎ ተጨማሪ ስድስት ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
16.6K views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 19:56:21
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ሳምንት ማካሄድ ጀምሯል።

የምርምር ሳምንቱ በመጀመሪያ ቀን ውሎው በምርምር ተቋማት እና በዩኒቨርሲቲው ጆርናል ህትመቶች ላይ ተወያይቷል።

በተስፋሁን መለሰ (ዶ/ር) ’’ዳባት የምርምር ማዕከል’’ እና በቡሻ ታዓ (ዶ/ር) ’’ናይል የኢትዮጵያ ህዳሴ ጆርናል’’ን የተመለከቱ ሁለት ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከግንቦት 17 እስከ 19/2014 ዓ.ም ሀገር ዐቀፍ ጉባኤ ያካሂዳል።

@tikvahuniversity
12.2K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ