Get Mystery Box with random crypto!

Tikvah-University

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 214.08K

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 251

2022-05-23 16:37:24
#Wollo_University

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በወሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ግንቦት 21 እና 22/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ግንቦት 23/2014 ዓ.ም ብቻ በቅጣት መመዝገብ ይቻላል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• ከ8 እስከ 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች
ዋናውና ሁለት ኮፒ
• 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (8)
• ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

(ለተጨማሪ መረጃ ከላይ የተያያዘውን ይመልከቱ።)

@tikvahuniversity
16.2K viewsedited  13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 11:51:56
#Assosa_University

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው የአዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ግንቦት 15 እና 16/2014 ዓ.ም እንደሆነ መግለጹ ይታወቃል።

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም ከ3 ሺህ በላይ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

@tikvahuniversity
17.6K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 11:36:58
የት ለመማር ወሰኑ?

በ Software Engineering እና በ Information Technology and Systems በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርትዎን ለመማር ወደ #ቢትስኮሌጅ ቢመጡ አብዝተው ያተርፋሉ።

በአራት ዓመት ውስጥ በዲግሪ ብቻ ሳይሆን ብቁ ሰራተኛ ሆነውም ይመረቃሉ።

ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መምህራን፣ ጥራታቸውን የጠበቁና በዘመናዊ መልክ የተደራጁ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ-መፅሀፍት፣ የኮምፒዩተር ላብራቶሪዎች እና እጅግ ዘመናዊ የአይቲ መሠረተ ልማት #በቢትስኮሌጅ የተሟሉ ናቸው።

ለማመልከት እና ለበለጠ መረጃ፦

ድረ-ገጽ www.bitscollege.edu.et

0982363636
0978028655

#BITSCollege
17.3K viewsedited  08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 11:12:29
#ጥቆማ
#Dire_Dawa_University

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በማቴሪያል ሳይንስ እና ኢንጅነሪንግ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያ የምርምር ዓለም ዐቀፍ ኮንፈረንስ ማካሄድ ጀምሯል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ኮንፈረንስ ከጅቡቲ፣ ሶማሊላንድ፣ ሶማልያ እና ደቡብ አፍሪካ የመጡ ተመራማሪዎች ይሳተፋሉ።

ከሀገር ውስጥ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተጋበዙ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎችን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።

አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ፣ ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር እና የድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኮንፍረንሱን ስፖንሰር ያደረጉ ተቋማት ናቸው።

@tikvahuniversity
15.8K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 10:12:52
#Samara_University

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ የአፋር ህዝብ ባህልና ጥናት ምርምር ኢንስቲትዩትን ለማጠናከር እየሰራሁ ነው ብሏል።

የኢንስቲትዩቱን ህንጻ ለሙዚየም በሚሆን መልኩ የማስተካከል ሥራዎች እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው የአፋርኛ ቋንቋን በ2ኛ ዲግሪ ደረጃ እያስተማረ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መሀመድ ኡስማን (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የአፋር ህዝብ ባህል እና ሀገር በቀል እውቀቶች ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት በዚህ ዓመት አጋማሽ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ኃይማኖታዊ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ሥራ ማከናወኑን ጠቁመዋል።

በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የአፋር ተወላጆችና ወዳጆች በእጃቸው የሚገኙ ቅርሶችን ለዩኒቨርሲቲው እንዲያበረክቱ ፕሬዝዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahuniversity
17.5K views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 20:42:21
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል፡፡

ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የተመረቁትን እናስተዋውቅዎ፦

ዑመር ሚፍታህ
• የሕክምና ዘርፍ ተመራቂ ሲሆን 3 ነጥብ 98 ውጤት በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

ኑሀሚን አለማየሁ
• በሕክምና መስክ 3 ነጥብ 92 ውጤት በማምጣት በማዕረግ ተመርቃለች።

@tikvahuniversity
10.8K views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 14:26:17
#Update
#WollegaUniversity

በ2014 ዓ.ም ወደ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከግንቦት 15 እስከ 17/2014 ዓ.ም እንደሆነ መገለጹ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ማዘጋጀቱን ገልጿል።

• መነሻ ከተማ፦ ደምቢ ዶሎ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
ለገሰ ግርማ ~ 0916640790
ዱሬሳ አለማየሁ ~ 0919521309

• መነሻ ከተማ፦ መንዲ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
መሀመድ ዑመር ~ 0912700614
ሚልኬሳ ታከለ ~ 0935063833

• መነሻ፦ አያና ከተማ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
ገመቹ ገለታ ~ 0930770690
ኒሞና ከበደ ~ 0918171173

• መነሻ፦ ሻምቡ ከተማ
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦ በ15/09/2014 ዓ.ም
አስተባባሪዎች፦
ሸሚን ኢብራሂም ~ 0917434355
አዳነች ደገፋ ~ 0964629049

• መነሻ፦ አዲስ አበባ (አስኮ)
መነሻ ሰዓት፦ ከጧቱ 12:00
ጉዞ ወደ ነቀምቴ፦
በ15/09/2014 ዓ.ም (2 አውቶቡሶች)
በ16/09/2014 ዓ.ም (1 አውቶቡስ)
አስተባባሪዎች፦
ጀማል አደም ~ 0916700774
ደጋጋ ፈቀደ ~ 0917033569
ጃቤሳ አመንቴ ~ 0912290387
ቦንቱ ተመስገን ~ 0917675546

@tikvahuniversity
18.3K views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 13:22:56
#Bule_Hora_University

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ለሚከፍተው ማህበረሰብ ተኮር ሬዲዮ የስቱዲዮ ግንባታ አስጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ ተኮር ሬዲዮ ለመክፈት
ባለፈው ዓመት ከኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን ፈቃድ አጊኝቷል።

ይህንን ተከትሎም የማሰራጫ ማዕከል/ስቱዲዮ ግንባታ ለማከናወን የወጣውን ጨረታ ያሸነፈው ድርጅት ሥራ መጀመሩን የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዳንኤል ሰይፉ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

የሬዲዮው መጀመር ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸውን የመማር ማስተማር፣ የምርምር እና የማኅበረሰብ አገልገሎት ሥራዎችን በተለይ በጉጂ እና በምዕራብ ጉጂ ዞን ተደራሽ ለማድረግ ያስችለዋል ብለዋል።

የማህበረሰብ ተኮር ሬዲዮው በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ሥርጭቱን ያስተላልፋል።

የማህበረሰብ ተኮር ሬዲዮው (ኤፍ.ኤም 99.0 MHz) በቅርቡ የሙከራ ስርጭት እንደሚጀምር ይጠበቃል።

@tikvahuniversity
17.9K views10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 12:20:52
የት ለመማር ወሰኑ?

በ Software Engineering እና በ Information Technology and Systems በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርትዎን ለመማር ወደ #ቢትስኮሌጅ ቢመጡ አብዝተው ያተርፋሉ።

በአራት ዓመት ውስጥ በዲግሪ ብቻ ሳይሆን ብቁ ሰራተኛ ሆነውም ይመረቃሉ።

ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መምህራን፣ ጥራታቸውን የጠበቁና በዘመናዊ መልክ የተደራጁ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ-መፅሀፍት፣ የኮምፒዩተር ላብራቶሪዎች እና እጅግ ዘመናዊ የአይቲ መሠረተ ልማት #በቢትስኮሌጅ የተሟሉ ናቸው።

ለማመልከት እና ለበለጠ መረጃ፦

ድረ-ገጽ www.bitscollege.edu.et

0982363636
0978028655

#BITSCollege
16.0K viewsedited  09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 12:13:54
#Dilla_University

3ኛው አገር ዐቀፍ የሕግ ጥናትና ምርምር ጉባኤ በዲላ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

ጉባኤው "የታክስ ስርዓትና የሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ" በሚል ጭብጥ ላይ እየመከረ ነው።

በጉባኤው የተለያዩ የጥናትና ምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ የፌዴራል ፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ የሕግ ትምህርት ቤቶች ኅብረት የሁለት ቀናት ጉባኤውን በጋራ አዘጋጅተውታል።

@tikvahuniversity
15.0K views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ