Get Mystery Box with random crypto!

እስካሁን ጥሪ ያልተደረገላቸው የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም የሪሚዲ | Tikvah-University

እስካሁን ጥሪ ያልተደረገላቸው የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ተማሪዎች

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

ተማሪዎቹ ከታህሳስ ወር ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የአቅም ማሻሻያ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም።

ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ የጀማሪ መርሐግብር እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ለተከታተሉ ተማሪዎች መጋቢት 14/2016 ዓ.ም ጥሪ ሲያደርግ፤ በ2016 ዓ.ም ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ ሳያደርግ ቀርቷል።

እነዚህ ተማሪዎች በቀጣይ ጥሪ ይደረግልናል በሚል በተስፋ ሲጠብቁ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ከአንድ ወር በኋላም ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አላደረገላቸውም።

"የትምህርት ጊዚያቸው እየባከነባቸው እንደሆነ"ና "አስቸጋሪ ጊዜያትን እያሳለፉ እንደሚገኙ" ለቲክቫህ አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች፤ መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ጠይቀዋል።

የሪሚዲያል ፈተናው ይሰጣል ተብሎ በመንግሥት የተቀመጠው ጊዜ 45 ቀናት የቀሩት መሆኑ ሌላው ተማሪዎቹን እያሳሰበ ያለ ጉዳይ ነው።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ መቼ ጥሪ እንደሚደረግ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችን በስልክ እና በአጭር መልዕክቶች የጠየቀ ቢሆንም ምንም አይነት ምላሽ ማግኘት አልቻለም።

ተማሪዎቹ ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተዘዋውረው የሚማሩበት ዕድል ካለ፣ አማራጭ የፈተና ጊዜ የሚዘጋጅላቸው ከሆነ እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ወይም/እና ትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጡትን ምላሽ ወደናንተ እናደርሳለን።

@tikvahuniversity