Get Mystery Box with random crypto!

#Bule_Hora_University ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ለሚከፍተው ማህበረሰብ ተኮር ሬዲዮ | Tikvah-University

#Bule_Hora_University

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ለሚከፍተው ማህበረሰብ ተኮር ሬዲዮ የስቱዲዮ ግንባታ አስጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ ተኮር ሬዲዮ ለመክፈት
ባለፈው ዓመት ከኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን ፈቃድ አጊኝቷል።

ይህንን ተከትሎም የማሰራጫ ማዕከል/ስቱዲዮ ግንባታ ለማከናወን የወጣውን ጨረታ ያሸነፈው ድርጅት ሥራ መጀመሩን የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዳንኤል ሰይፉ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

የሬዲዮው መጀመር ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸውን የመማር ማስተማር፣ የምርምር እና የማኅበረሰብ አገልገሎት ሥራዎችን በተለይ በጉጂ እና በምዕራብ ጉጂ ዞን ተደራሽ ለማድረግ ያስችለዋል ብለዋል።

የማህበረሰብ ተኮር ሬዲዮው በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ሥርጭቱን ያስተላልፋል።

የማህበረሰብ ተኮር ሬዲዮው (ኤፍ.ኤም 99.0 MHz) በቅርቡ የሙከራ ስርጭት እንደሚጀምር ይጠበቃል።

@tikvahuniversity