Get Mystery Box with random crypto!

#Haramaya_University ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን አዲስ የተመደቡ ተ | Tikvah-University

#Haramaya_University

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን አዲስ የተመደቡ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ከግንቦት 12 እስከ 14/2014 ዓ.ም መሆኑን የገለጸ ቢሆንም ከትላንት ምሽት ጀምሮ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው አዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች ላይ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያስተባብሩ ሰዎች መመደቡን በዩኒቨርሲቲው የፍሬሽማን ፕሮግራም ዳይሬክተር ጌታቸው ተሾመ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ተማሪዎች የተመደቡትን ካምፓስ እና የመኝታ ክፍል በበይነ መረብ አማካኝነት እንዲያውቁ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከ5 ሺህ 100 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

@tikvahuniversity