Get Mystery Box with random crypto!

#የኢንፎርሜሽን_ቴክኖሎጂ_ውድድር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ | Tikvah-University

#የኢንፎርሜሽን_ቴክኖሎጂ_ውድድር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የተሻለ የፈጠራ ሥራ ያላቸውን ባለሙያዎች እውቅና መስጠት እና ሥራዎቻቸውን ማስተዋወቅ እንደሚፈልግ ገልጿል።

ኅብረተሰቡን የሚጠቅምና ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸው የፈጠራ ሥራ ያላችሁ እስከ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም አዲስ አበባ አምስት ኪሎ በሚገኘው የተቋሙ ቢሮ ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል።

• በኢ-መንግስት ሶሉሽን፣
• በሶፍትዌር ልማት፣
• በሮቦቲክስ፣
• በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ/ዳታ ሳይንስ እና ሌሎችም መሰል ዘርፎች የፈጠራ ሥራ ያላችሁ ማመልከት ትችላላችሁ።

የፈጠራ ሥራዎቹ ቢሮው በሚያዘጋጀው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ ላይ ይቀርባሉ ተብሏል።

@tikvahuniversity