Get Mystery Box with random crypto!

#የትምህርትና_ሥልጠና_ባለሥልጣን በርካታ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሐሰተኛ የትምህርት ማስ | Tikvah-University

#የትምህርትና_ሥልጠና_ባለሥልጣን

በርካታ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚታደልባቸው እየሆኑ መምጣታቸው ተገለጸ።

በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በመገኘት የመስክ ምልከታ አድርጓል።

ሕገ-ወጥ የትምህርት ማስረጃ እና ሕገ-ወጥ ተቋማት መበራከታቸውን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አንዱዓለም አድማሴ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ተቋሙ የተሰጠውን አገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ ለመፈጸም የሚያስችል የሰው ኃይል አደረጃጀት አለመኖሩንም ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ስብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በበርካታ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚታየውን የሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እደላ ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት ቀልጣፋና ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ከዓለም ባንክ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ባለ ሰባት ወለል ህንጻ ለማስገንባት በሂደት ላይ መሆኑም ተገልጿል።

@tikvahuniversity