Get Mystery Box with random crypto!

#Werabe_University ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለ | Tikvah-University

#Werabe_University

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ ከ3 ሺህ 200 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

የመማር ማስተማር ሥራ ከጀመረ ወዲህ ዘንድሮ ለአምስተኛ ዙር አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የሚቀበለው ዩኒቨርሲቲው፤ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ግንቦት 15 እና 16/2014 ዓ.ም ለመቀበል ጥሪ አድርጓል።

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መኪናዎች መዘጋጀታቸውን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት መሀመድ አዎል (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

በ2010 ዓ.ም የማስተማር አገልግሎት መስጠት የጀመረው ወራቤ ዩኒቨርሲቲ አሁን ላይ ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብሮች በማስተማር ላይ ይገኛል።

@tikvahuniversity