Get Mystery Box with random crypto!

#AddisAbabaUniversity የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ከአምስት ዓመታት በኋላ ዳግም | Tikvah-University

#AddisAbabaUniversity

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ከአምስት ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ህትመት ሥራ መመለሱ ተሰምቷል።

ለዘመናት የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን ለአንባብያን ሲያበረክት የቆየው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፤ በግብርና፣ በኢኮኖሚ፣ በትምህርት እና በፓን አፍሪካኒዚም ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስምንት መፃሕፍትን በማተመ ዳግም ሥራ መጀመሩን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በሌላ መረጃ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመፃሕፍት አውደ ርዕይ በ 6 ኪሎ ካምፓስ (ዋናው ግቢ) ትናንት ተከፍቷል፡፡

በርካታ መፃሕፍት የቀረቡበት አውደ ርዕዩ፤ እስከ እሁድ ሚያዝያ 13/2016 ዓ.ም ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።

@tikvahuniversity