Get Mystery Box with random crypto!

ባለ ብዙ ሙያ ተመራቂው ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባሳለፍነው ቅዳሜ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል ባለ ብዙ | Tikvah-University

ባለ ብዙ ሙያ ተመራቂው

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባሳለፍነው ቅዳሜ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል ባለ ብዙ ሙያ ተመራቂ የሆኑት ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ ይገኝበታል።

የቴሌቪዥን ድራማዎች ፅሁፍ ዝግጅት እና መፃሕፍት ማሳተም ዶ/ር በዛብህ የሚታወቅባቸው ሌሎች ጉዳዮች ናቸው፡፡

ዶ/ር በዛብህ በቅርቡ የሚያሳትመውን ጨምሮ አራት መፃሕፍትን የፃፈ ሲሆን፤ ስድስት ሲትኮም ድርሰቶችን በመድረስ ለህዝብ አድርሷል፡፡

በጥርስ ህክምና የዶክትሬት ዲግሪ ተመራቂው በዛብህ፤ በሀገራችን በተለያዩ ቴሌቪዥን የሚተላለፉ ተከታታይ ድራማዎች ላይ በደራሲነት ተሳትፏል፡፡

ዘጠነኛው ሺ ከ35 ክፍል በላይ፣ መስሪያ ቤት፣ ሳሎኑ፣ ዶክተሮቹ፣ ፊሽካዎቹ እና አንድ ላይ የተሰኙ ድራማዎች ላይ በደራሲነትና በዳይሬክተርነት ተሳትፏል። በርካታ የቴሌቪዥን እና የራዲዮ ማስታወቂያዎችንም አዘጋጅቷል።

ደራሲ እና የጥርስ ሐኪም ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ፤ በቅርቡ ለህትመት የሚበቃ "የአፍ ጤና አጠባበቅ ለልጆች እና ለወላጆች" የሚል መማሪያ መፅሐፍ አዘጋጅቶ ማጠናቀቁንም ገልጿል።

@tikvahuniversity