Get Mystery Box with random crypto!

Tikvah-University

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahuniversity
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 213.59K

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2024-04-17 11:47:35
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል?

2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ በርካቶች ጥያቄ አድርሰውናል።

12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
35.7K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 11:47:24
#ጥቆማ

የመሬት ሕግ እና ፖሊሲ ቅኝት በኢትዮጵያ የተሰኘ መፅሐፍ አርብ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም ይመረቃል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ለህትመት የበቃው መፅሐፉ፤ በዳንኤል በሀይሉ የተፃፈ መሆኑ ታውቋል፡፡

መፅሐፉ አርብ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 በራስ መኮንን አዳራሽ ይመረቃል፡፤

@tikvahuniversity
31.7K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 11:34:18
#የቻናል_ጥቆማ

ለኢንጂነሪንግ ተማሪዎች እና Construction ዘርፍ ላይ ለተሰማራችሁ በሙሉ

የኮንስትራክሽን፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ የአርክቴክቸር ተማሪ ነዎት? በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት?

በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መፃሕፍቶች፣ ቪዲዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን ዕውቀቶች ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን!

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣
አዲስ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣
እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣
በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሌክቸር የምታገኙበት፡፡

Join Us :-

on Telegram

https://t.me/ethioengineers1
https://t.me/ethioengineers1

on TikTok

tiktok.com/@ethiocons
tiktok.com/@ethiocons
25.7K views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 11:18:20
13ኛ ዙር የድረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።

100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
መሠረታዊ የኮምፒውተር እና ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
በተግባር ድረ-ገፆችን እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

ለበለጠ መረጃ፦  0906777799 / 0906777755

አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ

የበለጠ ይጠብቁ ...
        ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት


Facebook | Telegram | Instagram | LinkedIn
25.5K views08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 09:53:23
#AddisAbabaUniversity

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ከአምስት ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ህትመት ሥራ መመለሱ ተሰምቷል።

ለዘመናት የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን ለአንባብያን ሲያበረክት የቆየው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፤ በግብርና፣ በኢኮኖሚ፣ በትምህርት እና በፓን አፍሪካኒዚም ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስምንት መፃሕፍትን በማተመ ዳግም ሥራ መጀመሩን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በሌላ መረጃ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመፃሕፍት አውደ ርዕይ በ 6 ኪሎ ካምፓስ (ዋናው ግቢ) ትናንት ተከፍቷል፡፡

በርካታ መፃሕፍት የቀረቡበት አውደ ርዕዩ፤ እስከ እሁድ ሚያዝያ 13/2016 ዓ.ም ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።

@tikvahuniversity
37.8K views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 14:49:59
ባለ ብዙ ሙያ ተመራቂው

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባሳለፍነው ቅዳሜ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል ባለ ብዙ ሙያ ተመራቂ የሆኑት ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ ይገኝበታል።

የቴሌቪዥን ድራማዎች ፅሁፍ ዝግጅት እና መፃሕፍት ማሳተም ዶ/ር በዛብህ የሚታወቅባቸው ሌሎች ጉዳዮች ናቸው፡፡

ዶ/ር በዛብህ በቅርቡ የሚያሳትመውን ጨምሮ አራት መፃሕፍትን የፃፈ ሲሆን፤ ስድስት ሲትኮም ድርሰቶችን በመድረስ ለህዝብ አድርሷል፡፡

በጥርስ ህክምና የዶክትሬት ዲግሪ ተመራቂው በዛብህ፤ በሀገራችን በተለያዩ ቴሌቪዥን የሚተላለፉ ተከታታይ ድራማዎች ላይ በደራሲነት ተሳትፏል፡፡

ዘጠነኛው ሺ ከ35 ክፍል በላይ፣ መስሪያ ቤት፣ ሳሎኑ፣ ዶክተሮቹ፣ ፊሽካዎቹ እና አንድ ላይ የተሰኙ ድራማዎች ላይ በደራሲነትና በዳይሬክተርነት ተሳትፏል። በርካታ የቴሌቪዥን እና የራዲዮ ማስታወቂያዎችንም አዘጋጅቷል።

ደራሲ እና የጥርስ ሐኪም ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ፤ በቅርቡ ለህትመት የሚበቃ "የአፍ ጤና አጠባበቅ ለልጆች እና ለወላጆች" የሚል መማሪያ መፅሐፍ አዘጋጅቶ ማጠናቀቁንም ገልጿል።

@tikvahuniversity
27.0K views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 14:33:12
#የቻናል_ጥቆማ

ለኢንጂነሪንግ ተማሪዎች እና Construction ዘርፍ ለይ ለተሰማራችሁ በሙሉ

የኮንስትራክሽ፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ የአርክቴክቸር ተማሪ ነዎት?
በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት?

በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መፃሕፍቶች፣ ቪድዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን ዕውቀቶች ለማግኝት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን!

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣
የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣
እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣
በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት

Join Us :-

on Telegram

https://t.me/ethioengineers1
https://t.me/ethioengineers1

on TikTok

tiktok.com/@ethiocons
tiktok.com/@ethiocons
24.9K views11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 12:01:31
የትምህርት ማስረጃዎችን የማጥራት ሥራ በክልሎች ደረጃ ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡

በፌደራል ተቋማት ላይ የተጀመረው ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን የመመርመር ሥራ በክልሎች ደረጃ እንደሚጀመርም የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ም/ዋ/ዳይሬክተር ቢኒያም ሔሮ ለአሐዱ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ማስረጃዎችን የመመርመር ሥራው በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እንደሚመራ ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ የትምህርት ማስረጃዎችን በዲጂታል አማራጭ ብቻ ለመስጠት ሙከራ እየተደረገ እንደሆነም ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

ማስረጃዎችን በመፈተሽና በማረጋገጥ የህግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡ #AhaduFM

@tikvahuniversity
27.7K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 14:14:42
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 256 ተማሪዎች አስመርቋል።

በጤና ሳይንስና ህክምና ትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና የመውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡ 32 ተማሪዎች ተመርቀዋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 224ቱ በተለያዩ የድኅረ ምረቃ መርሐግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
19.2K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 11:40:07
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 778 ተማሪዎች አስመረቀ።

ከተመራቂዎቹ 26 በሦስተኛ ዲግሪ፣ 350 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም 402 በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

በህክምና፣ በጥርስ ህክምና፣ በነርሲንግ፣ በሚድዋይፈሪ እና በፊዚዮቴራፒ የትምህርት መስኮች የሰለጠኑ የህክምና ተማሪዎች ከተመራቂዎቹ መካከል ይገኙበታል።

@tikvahuniversity
23.0K views08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ