Get Mystery Box with random crypto!

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት የመግባቢያ ስምም | Tikvah-University

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በዋነኝነት ዩኒቨርሲቲው በሚያከናውናቸው የጥናትና ምርምር ሥራዎች ላይ በትብብር መስራት የሚያስችል ነው። የቱሪስት ሳይቶችን ካርታ ማንሳት ሌላው የስምምነቱ አካል እንደሆነ ተመላክቷል።

ተማሪዎች ለተግባር ትምህርት ወደ ተቋሙ በመሄድ ስልጠና እንዲወስዱ የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።

የኢንስቲትዩቱ የስፔስ ዘርፍ ም/ዳይሬክተር ይሽሩን አለማየሁ (ዶ/ር) እና የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት በዛብህ ወንድሙ (ዶ/ር) ስምምነቱን ፈርመዋል።

@tikvahuniversity