Get Mystery Box with random crypto!

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በፍተሻ ላቦራቶሪ የIS | Tikvah-University

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በፍተሻ ላቦራቶሪ የISO/IEC 17025 ዓለም ዐቀፍ ዕውቅና አገኘ።

ኢንስቲትዩቱ ዓለም ዐቀፍና ብሔራዊ መሥፈርት  ማሟላቱ በፊዚካልና ኬሚካል ፍተሻዎች መረጋገጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ዕውቅና ተሰጥቶታል።

ኢንስቲትዩቱ ዕውቅና ማግኘቱ በአማራ ክልል ለሚገኙ እና በጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ለሚያመርቷቸው ምርቶች የጥራት የላቦራቶሪ ፍተሻ ውጤት መስጠት ያስችለዋል።

በ2003 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልገሎት፤ መስፈርቶችን ላሟሉ 13 ተቋማት የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ዕውቅና መስጠቱን በዚህ ሳምንት መግለጹ ይታወቃል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር  አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሌላው በሕክምና ላቦራቶሪ ዕውቅና የተሰጠው የትምህርት ተቋም ነው።

@tikvahuniversity