Get Mystery Box with random crypto!

#Wollo_University ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 | Tikvah-University

#Wollo_University

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በእንስሳት ሕክምና ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከዛሬ ተመራቂዎች ውስጥ 106ቱ በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ከደረሰበት ውድመት መልሶ በመቋቋም የመማር ማስተማር ሥራውን ዳግም በማስጀመር፤ ለተማሪዎቹ ቅዳሜ እና እሁድ የማካካሻ ትምህርት በመሰጠት ለምርቃት እንዲበቁ መደረጉን ገልጿል።

@tikvahuniversity