Get Mystery Box with random crypto!

#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማቋቋሚ | Tikvah-University

#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ምክር ቤቱ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በቦርድ እንዲመራም ወስኗል።

በዚህም ለባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል፦

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል።

ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ ተስፋዬ ዳባ፣ ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) እና ሳህረላ አብዱላሂ በአባልነት ተመድበዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አንዱዓለም አድማሴ (ዶ/ር) የሥራ አመራር ቦርዱ አባል እና ፀሀፊ ሆነዋል።

@tikvahuniversity