Get Mystery Box with random crypto!

#Update በሰሜን ጎንደር ዞን በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና | Tikvah-University

#Update

በሰሜን ጎንደር ዞን በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ እና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በሙሉ በቀጣይ ዓመት ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ተማሪዎቹ በቀጣይ ዓመት ለሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

በዚህም የማጠናከሪያ ትምህርት ከግንቦት ወር ጀምሮ ለሁለት ወራት እንደሚሰጥ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገልጿል።

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ እና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም ተፈታኞች ጋር በድጋሚ ፈተናውን እንዲፈተኑ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ መወሰኑ ይታወሳል።

(በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ስለጉዳዩ የጻፈው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity