Get Mystery Box with random crypto!

#Bahir_Dar_University የጨርቃ ጨርቅ እና ፋሽን ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ፣ ባዛርና ኤግዚቢ | Tikvah-University

#Bahir_Dar_University

የጨርቃ ጨርቅ እና ፋሽን ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ፣ ባዛርና ኤግዚቢሽን በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ግቢ በተከፈተው አውደ ርዕይ ሸማች እና አምራቾች እየተገበያዩ ይገኛሉ።

በጉባዔው ጥናታዊ ፅሁፎችና የልምድ ተሞክሮዎች የቀረቡ ሲሆን የጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ ውጤቶችም ለእይታ ቀርበዋል።

ዛሬ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ዓለም ዐቀፍ የፋሽን ትርዒት የሚቀርብ ሲሆን የመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ይሆናልም ተብሏል።

ጉባዔው በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና በኢትዮጵያ ቴክስታይል ኢንስቲትዩት በጋራ ተዘጋጅቷል።

@tikvahuniversity