Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.57K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 48

2022-06-21 15:46:00
15.5K viewsTadele Tibebu, 12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 15:43:38 #ሼር_ፖስት! እነ ዶክተር ደሳለኝ ፓርላማውን ጥለው መውጣታቸው የሚያስመሰግናቸው ነው ይህን ቀን ታሪክ የሚመዘግበው ስለሆነ "በዛሬው የምክርቤት ውሎ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለአፈጉባኤው ያቀረቡት ጥያቄ እና ቃለምልልሱ....እንደሚከተለው ነው!

አቶ ታገሰ ጫፎ

" ... በዛሬው ዕለት የተያዙ አጀንዳዎች አንደኛ የምክር ቤቱ አንደኛ ዓመት የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ ፤ 2ኛ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የ2013 በጀት ዓመት የሂሳብ፣ ፋይናንስ እና ህጋዊነት ኦዲት እና የክንዋኔ ኦዲት ሪፖርት ማዳመጥ ናቸው ፤ ...የሚቀርቡ ማስተካከያዎች እና እርማቶች ካሉ "

የአብን ተወካይ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔን " እ... "

አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " ቃለ ጉባኤ ላይ ነው ? "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " ቃለ ጉባኤው ላይ ሳይሆን "

አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " አይቻልም "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " አጀንዳው ላይ ቀዳሚ አጀንዳ እንዲያዝልን ለመጠየቅ ነው "

አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " አይቻልም ፤ ባለተያዘ አጀንዳ አንወያይም። "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " የተከበሩ አፈጉባኤ ...አንድ ደቂቃ እድል እንዲሰጠኝ ጥያቄ ለማቅረብ "

አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ " ስነስርዓት ፤ ድምፅ ማሰማት አይቻልም ስነስርዓት "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ " ቀዳሚ አጀንዳ እንዲያዝልን ጥያቄ ለማቅረብ ነው "

አቶ ታገሰ ጫፎ፤ " ማይክራፎኑን ይዝጉት "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ " ቀዳሚ አጀንዳ አለን የአብን ተወካዮች እሱ እድል ይሰጠን "

አቶ ታገሰ ጫፎ፤ " ማይክራፎኑን ይዝጉት፤ አጀንዳ ካለ በአማካሪ ኮሚቴ አባል ስለሆኑ በአማካሪ ኮሚቴ እንነጋገራለን "

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ " አስቸኳይ ነው ዛሬ ም/ቤቱ እንዲያይልን የምንፈልገው "

አቶ ታገሰ ጫፎ፤ " ቃለ ጉባኤ ላይ ሚቀርቡ እርማቶች እና ማስተከከያዎች ካሉ .."

ከዚህ በኃላ ዶ/ር ደሳለኝን ጨምሮ 4 አብን ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል። እነሱም፦

1.ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ (የባህርዳር ተወካይ)

2.አቶ አበባው ደሳለኝ (የጅጋ/ም/ጎጃም ተወካይ)

3.አቶ ሙሉቀን አሰፋ (ሸበል በረንታ/ዕድ ውሃ ተወካይ

4.አቶ ዘመነ ኃይሉ (የጭስ ዓባይ ተወካይ)

ለሀሳብ ለአስተያየት በዚህ ሊንክ @Tadeletibebut
15.4K viewsTadele Tibebu, edited  12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 07:13:46
16.5K viewsTadele Tibebu, 04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 07:13:21 ዘጋርዲያን፣ አሶሺየትድ ፕረስ፣ አርቲና ሌሎች ዓለማቀፍ ሚዲያዎች በወለጋ በዐማሮች ላይ የተፈፀመውን ፍጅት ዘግበውታል የኛዎቹ የጓሮ አትክልት ሲዘግቡ ነው የዋሉት። ኢትዮጵያ ውስጥ
የሰው ልጅ ይህን ያህል ነው የረከሰው። አለምአቀፍ ሚዲያዎች እስካሁን የተገደሉት ከ200 በላይ ናቸው ቢሉም የሟቾች ቁጥር 330 ደርሷል። ጭፍጨፋው የተፈፀመው ስልሳው፣ ደጀኔ፣ አሶሳ ሰፈር እና 13 ተብለው በሚጠሩ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በሚገኙ መንደሮች ነው።
16.3K viewsTadele Tibebu, 04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 21:03:10 በዚህ ዘመን እንደ ኢትዮጵያ አስፈሪና አሳፋሪ ሀገር የለም። በየቀኑ በሰው ልጅ ደም መሬቷ ይረሰርሳል፤ ማቆሚያ የሌለው የግፉአን ዕንባ በየቀኑ ይፈሳል፤ በየቀኑ ክቡር የሰው ልጅ እንደ ቅጠል ይረግፋል፤ ሀገሪቱ በነፍሰ ገዳዮች የተሞላች ነች፤ ዘረኝነት፣ ድንቁርና ኋላቀርነት ሠልጥኖባታል፤ ደህነነት አጉብጧታል፤ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰው ልጅ ከትንኝ ያነሰ ዋጋ ነው ያለው። ማንም ይገድለዋል፥ የትም ይቀበራል። ፍትህ ርትዕ የለም፣ ህግ የለም፣ ሽማግሌ የለም፣ መንግሥት የለም፣ በሀገሪቱ ሰው ጠፍቶ የጃርት መፈንጫ ከሆነች ቆዬች። እናም ኢትዮጵያ ታስፈራለች፣ በኢትዮጵያ ለመኖር ሰቀቀን ነው። በነፃነት መኖር የለም፣ በነፃነት ከጎጃም ተሳፍሮ ወለጋ ዘመድ ጠይቆ መመለስ አይቻልም፣ እንደ ጥንቱ ስንቅ አዘጋጅቶ በእግር ተጉዞ አክሱም ፅዮን ተሳልሞ መመለስ አይቻልም። በምድሯ የበቀሉ ጃርቶች አደገኛዎች ናቸው።

ቴዲ አፍሮ "ኢትዮጵያ መምጫሽ ናፈቀኝ" ያለው ያቺዋን ቅድስት ኢትዮጵያ እንደሆነ ልብ ይለዋል!
8.9K viewsTadele Tibebu, edited  18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:04:23 "ሲሆን ተከናነብ፤ ሳይሆንም አጣፋው፣
መታጠቅ አይሆንም ለእንዳተ ያለሰው፣
እንዴት ያለ ሩቅ ነው ጭንቅ ያለ መንገድ፣
አሻቅቦ ወጥቶ አቆልቁሎ መውረድ፣"
11.5K viewsTadele Tibebu, 17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:00:11 "የነብርን መንጋጋ ፍየል ገብቶ ላሰው፣
እንዲህ አይደለም ወይ ጊዜ የጣለው ሰው"
11.6K viewsTadele Tibebu, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 12:08:08 እዚች አገር እስትንፋስ ያለው መንግሥት አለ ማለት አይቻልም። የትናንቱን ደስታ ሳናጣጥም ወይኑ ላይ ደማችንን ጨምረውበት አድረዋል። ወለጋ የሆነው እልቂት እጅግ ዘግናኝ ነው። በአንዲት ጀምር ከ100 በላይ ዐማሮች አልቀዋል፤ ከአንድ ቤተሰብ 3 እና 4 ሰዎች በግፍ ተገድለዋል።

በፈረንጆች ግንቦት 30 የኦሮሚያ የፀጥታ ሀላፊው "በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሸኔ የተያዘ አንድ ቀበሌ የለም" ብሎ ከነገረን በኋላ፣ ሰኔ 11 ቀን ደግሞ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በመቶ የሚቆጠሩ ዐማሮች ተጨፍጭፈው አድረዋል!

የሚነግሩን የማይጨበጥ፣ ወይንም ለውጥ የማይታበት ነጭ ውሸት፣ እየሆነ ያለው ሞት ነው።
17.1K viewsTadele Tibebu, edited  09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 19:48:13
10.9K viewsTadele Tibebu, 16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 19:48:09 በዛሬው ቀን ከአንድ ቤተሰብ 5 ሰዎች የአማራ ባንክ ደብተር ከፍተዋል። ዛሬ ተሰልፎ ያልደረሰው ሰው እልቆቢስ ነው። በየባንኩ ቅርንጫፍ የነበረው ሰው ብዛት ማመን ይከብዳል። እኔም ተሰልፌ ውዬ ሳይደርሰኝ ቀርቷል። በነገራችን ላይ ሁለት ለምወዳቸው ሰዎች የባንክ ደብተር አስከፍቼ በስጦታ አበርክቻለሁ፣ እኔም ዛሬ ተራዬ ስላልደረሰ ሰኞ የአማራ ባንክ ደብተር በስጦታ አስከፍቶ የሚሰጠኝ ሰው እየጠበቅሁ እገኛለሁ በነገራችን ላይ ለምትወዱት ሰው ከ50 ብር ጀምሮ ደብተር በማስከፈት ስጦታ ማበርከት ትችላላችሁ!

ለሀሳብ ለአስተያየት በዚህ ሊንክ @Tadeletibebut
11.0K viewsTadele Tibebu, edited  16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ