Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.80K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-08-04 09:53:50
27.2K viewsTadele Tibebu, 06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-04 09:53:28 በአስቸኳይ #ሼር_ፖስት ይሁን። የአብይ አሕመድ አገዛዝ አማራ ክልል ላይ ወረራ ፈጽሟል። ዳታና ዋይፋይ በማጥፋት ንፁሃንን በጅምላ እየጨፈጨፈ ይገኛል። ትናንት ጎንደር ማረሚያ ቤት ብቻ ከ10 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ልክ እንደ ቀይ ሽብር ዘመን ሰዎች አውራ ጎዳና ላይ ተግድለው እየተጣሉ ናቸው። በጥቅሉ አማራ ክልል አፈና ተፈጽሟል። የዘር ማጥፋት እና የጦር ወንጀል እየተፈጸመ ነው።

ኔትዎርክ ባለበት አካባቢ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊን፣ በውጭ የምትኖሩ ዲያስፖራዎች፣ በመላው ዓለም የምትገኙ የአማራ ማህበራት፣ የሲቪክ ተቋማት፣ የአማራ ህዝብ ጉዳይ ያገባናል የምትሉ በሙሉ ለሰብአዊ መብት ተቋማት፣ ለዲፕሎማቲኩ ማኅበረሰብ እንዲሁም ሚዲያዎች በማሳወቅና ጫና በማድረግ እንድታግዙ ጥሪ ቀርቦላችኋል። መሬት ላይ ያለው ወታደራዊ ጀብዱ በፖለቲካ ክንፍ መታገዝ ስለሚኖርበት በጋራ ተሰባስባችሁ የምትመክሩበት ጊዜው አሁን ነው። አስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቶ በውጭው አለም የጋራ ደጋፊ ኃይል መቋቋም ይኖርበታል።

በአሁኑ ሰዓት የጎጃም፣ የጎንደር፣ የወሎና የሸዋ ፋኖ ታላቅ ተጋድሎ እየፈፀመ ይገኛል። እንደ አርመኖች ያለፍትህ ላለመቅረት፣ እንደ ኩርዶች ተበትኖ ላለመኖር የመጨረሻውን መሰዋእትነት እየከፈለ ነው። ከኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ ነፃ ያወጣቸውን አካባቢዎችም የአማራ ፋኖ የራሱን ኮማንድ ፖስት አቋቁሞ ፀጥታ እያስከበረ ይገኛል። የግለሰብም ይሁን የህዝብ መገልገያ ተቋሞች ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው። እስካሁን የመርፌ ስባሪ ታህል ንብረት አልተዘረፈም። ይህ ጥብቅ ስነ-ምግባር ለትግሉ ወደፊት መገስገሻ ፓወር ነው። ፋኖነት ሕዝባዊነት ማለት በተግባርም ይሄው ነው። ስለሆነም ሁሉም በሚችለው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግና የመከራችንን ግዜ ለማሳጠር መረባረብ ይኖርበታል!

ድል ለዐማራ ሕዝብ
ድል ለኢትዮጵያ!

@እንደዚህ ኔትዎርክ ከተገኘ መረጃዎችን
update ለማድረግ እሞክራለሁ!


ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut
27.0K viewsTadele Tibebu, edited  06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-02 20:49:13
28.4K viewsTadele Tibebu, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-20 19:49:46
26.9K viewsTadele Tibebu, 16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-20 19:49:19 እናመሰግንሻለን ምሳወይ አባተ እንደ ምሳወይ ያሉ ጋራና ሸንተሩን እያቆራረጡ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ህዝባቸውን የሚያገለግሉ አሉ። ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ደግሞ ቢሮ ወንበር ውስጥ ተቀምጠው ህዝቡን የሚያማርሩ አሉ። መኪና የሚገባቸው እንደ ምሳወይ በእግር እየተጓዙ ህዝቡን ለሚያገለግሉ ሆኖ ሳለ፣ አንድ ሰዓት እንኳን ቢሮ ቁጭ ብለው በትክክል ህዝቡን ማስተናገድ የማይችሉ ደግሞ ዘመናዊ መኪና ይዘው በጎርፍ ውሐ ረጭተውን ያልፋሉ።

ምሳወይ በአማራ ክልል በሰቆጣ ከተማ ከ17 ዓመት በላይ የጤና ባለሙያ ሁና አገልግላለች። "Global Citizen" ስለ ምሳወይ አባተ "This Health Worker Walks 6 Hours to Vaccinate Children in Ethiopia" በሚል ይዞት በወጣው ዘገባ፣ ምሳወይ ለህፃናት ክትባት ለመሥጠት የሰቆጣን አቀበትና ቁልቁለት፣ ተራራና ሸንተረር በማቆራረጥ 6 ሰዓት በእግሯ ትጓዛለች። በሰቆጣ ዙሪያ ባሉ መንደሮች ለህፃናት ክትባት ትሰጣለች። ህዝቧን ስለቤተሰብ ምጣኔ፣ ስለእርግዝና፣ ስለጡት ማጥባት እና ስለተመጣጠነ ምግብ ታስተምራለች።

ነገም በጥዋቱ ተነስታ የክትባቱን ሳጥን በትከሻዋ በማንገት የቆቦ ሰንሰለታማ ተራሮችን ትወጣለች፤ ትወርዳለች። ወደ ወገኖቿ ለመድረስ በጣም አስቸጋሪ የሆኑ መልክዓ ምድርን ታቆራርጣለች። ከስድስት ሰዓት በላይ ትጓዛለች....ይህ ለ17 ዓመት የኖረችበት ሕይወቷ ነው።

በተለይም በጦርነቱ ምክንያት በሰቆጣና አካባቢው ከሦስት ዓመት በላይ ክትባት ተቆርጦ በመቆየቱ ከአስፈላጊም በላይ ሆኗል። ምሳወይ ለግሎባል እንደተናገረችው ጤናማ የነበሩ ህፃናት በጦርነቱ ምክንያት ተጎሳቁለዋል። በክትባት እጥረት ታመዋል። ክብደታቸው ቀንሷል። "እናም ደሞዜ ትንሽ ቢሆንም የእነዚህን ህፃናት ህይወት ለመታደግ በመሆኑ በሥራዬ ደስተኛ ነኝ። የኔ ትልቁ ክፍያ የህፃናቶችን ሕይወት መታደግ ነው" ትላለች።

እንግዲህ ኢትዮጵያ እንደ ምሳወይ የሚያገለግሏት አሉ። እንደማትነጥፍ ላም እያለቧት የሚኖሩም አሉ። ሀቀኛ ነጋዴዎች አሉ፤ ፣ ከተመኑ በላይ አንድን ዕቃ አስወድደው የሚሸጡም አሉ። ንፁህ ወተት የሚሸጡ አሉ፤ በወተቱ ላይ ውሐ ጨምረው የሚሸጡ አሉ። በተመሳሳይ በቅቤ ላይ ለውዝ፣ በዱቄት ላይ ሳጋቶራ፣ በማር ላይ ስኳር ጨምረው የሚሸጡ ለማኅበረሰቡ ጤና የማይጨነቁ አሉ። ከታሪፉ በላይ የሚያስከፍሉ ሹፌሮች፣ ጉቦ ተቀብለው በንፁሃን ላይ የሚፈርዱ ዳኞች፣ ገንዘብ ተቀብለው በሀሰት የሚመሰክሩ፣ የሥራ ቅጥር ሲወጣ ገንዘብ ተቀብለው የሚቀጥሩ አሉ።

እንደ ምሳወይ በማለዳ ተነስተው ለሥራ የሚጓዙ አሉ፤
ዘግይተው ወይንም ሰዓቱ ሳይደርስ ቀድመው ከቢሮ የሚወጡ አሉ። እንደ ምሳወይ ደሞዝ በቅጡ ሳይከፋላቸው ባልተመቻቸ ሁኔታ ማኅበረሰባቸውን እንደ ሻማ እየቀለጡ የሚያገለግሉ አሉ፣ በጆርጅ አርዌል "የእንስሳት እርሻ" ውስጥ እንዳሉት ባህርያት በሥልጣናቸው ህዝብን ከማግለል ይልቅ የሚባልጉ፣ለራሳቸው ምቾት የሚጨነቁ አሉ።


እኛ ግን እንደ ምሳወይ እና እንደሷ ላሉ ብርቱ ሠራተኞች ክብረት ይስጥልን እንላለን

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut
26.7K viewsTadele Tibebu, edited  16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 12:31:43
28.0K viewsTadele Tibebu, 09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 12:31:34 የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ንግስ እና የፃዲቁ ንጉስ ቅዱስ ላሊበላ የእረፍት መታሰቢያ በዓል በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ በዚህ መልኩ ተከብሯል። እንኳን አደረሳችሁ
Menilk Farahun
26.5K viewsTadele Tibebu, 09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 20:12:37
29.0K viewsTadele Tibebu, 17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 20:12:31 አያት፣ አባትና ልጅ። መሀከለኛው ባያብል ምትኩ ይባላሉ አያቴ ናቸው። በቀኝ በኩል አባቴ ቄስ ጥበቡ ባያብል ናቸው። በግራ እኔ። አባቴ የአያቴ የመጀመሪያ ልጅ ነው። እኔ ደግሞ የአባቴ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ። ፎቶውን የዛሬ ሳምንት ነበር የተነሳነው። አያቴ ትንሽ አመመኝ ብለው ህክምና ላሳያቸው ሲመጡ ነበር በስልክ ካሜራ ያስቀረሁት። በነገራችን አያቴ 85 አመት ሆኗቸዋል። እግዚአብሔር ይመስገን ይህን ያህል ግዜ ሲኖሩ ለመጀመሪያ ግዜ አመመኝ ብለው ህክምና የታዩት አንድ ግዜ ብቻ ነው። በዚህ ምርመራም ሙሉ ጤነኛ ናቸው ተብለው ወደቤታቸው ተመልሰዋል።

አያቴ እጅግ ሲበዛ ሰው ወዳድ፣ ሰው አክባሪና በሀገሩ የተከበሩ፣ አስታራቂ፣ ልጆቻቸውን በሥርዓት ያሳደጉ አባት ናቸው። ሴቷ አያቴም በሙሉ ጤንነት በህይወት አሉ።

ለአባቶቻችን እድሜና ጤና ይስጥልን

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut
26.0K viewsTadele Tibebu, edited  17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 13:09:12
16.8K viewsTadele Tibebu, 10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ