Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.80K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 50

2022-05-11 15:12:56 አንደኛ ተሸላሚ የሚባል ነገር የለም፤ ትክ የሌላትን ነፍሱን ለመስጠት የዘመተ ሁሉ ለኔ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ነው። አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ሦስተኛ እያሉ ደረጃ ማውጣት ምን ማለት ነው? በዚህ የህልውና ዘመቻ በሺህ የሚቆጠር ሰው ሞቶአል፣ ቆስለዋል፣ የአካል ጉዳተኛ ሆነዋል፣ አሁንም ከቁስላቸው ያላገገሙ፣ በቦንብ ፍንጣሪ አይናቸው ጠፍቶ በሰው የሚመሩ፣ እግራቸው ተቆርጦ በሰው ድጋፍና በክራንች የሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች፣ ልዩ ኃይልና ሚኒሻዎች አሉ። በእነዚህ መካከል የወርቅ፣ የብር፣ የንስሐ ሽልማት እያሉ ደረጃ ማውጣት ትክክል አይደለም። ምሥጋና ማቅረብና የተጎዱትን ለመርዳት ምን እንደታሰበ ማሳወቁ ብቻ በቂ ነበር።

ሌላው ሽልማቱ በጥናት ላይ የተመረኮዘ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አለኝ። እንደማየው ከሆነ በቴሌቪዥንም ሆነ በፌስቡክ የተወራላቸው ሰዎች፣ ተደጋጋሚ ድጋፍና እገዛ ያገኙ ሰዎች ናቸው ሽልማቱ ላይ ያየኋቸው። ጀብዱ የፈፀሙ ግን የሚዲያ ሽፋን ያላገኙ፣ ጀብዱ ፈጽመው ልጃቸውን ጥለው የሞቱ ግን ድጋፍ ያልተደረገላቸው፣ አንዳንዶቹ ስማቸው ያልተመዘገበ ግን በራሳቸው ፍቃድ ዘምተው ታሪክ የሰሩ እንዳሉ አውቃለሁ።

በዚህ ሽልማት ቢያንስ ሚስቶቻቸው ይገኛሉ ብዬ ጠብቄ ነበር ግን የተጋበዙ ሰዎች አስቀድሞ የሚዲያ ሽፋን የነበራቸው ናቸው። ያለጥርጥር 12 እና ከዛ በላይ ጠላት ረፍርፈው የሞቱ እንዳሉ አውቃለሁ፣ በአይኔም ያየሁት ነገር ነው። ግን በዛሬው ሽልማት አልተካተቱም።

ይህ ተጎጂ ቤተሰቦችን ከሃዘናቸው በላይ ማሳዘን ነው። በእነዚህ ሀዘንተኞች ላይ የደረጃ ምደባ ማውጣት ትክክል አይደለም ያልኩት ለዚህ ነው። ከጥቅሙ ይልቅ ፋኖን ለመከፋፈል የተደረገ ድራማ ነው የሚመስለው።

ሌላው በሽልማቱ በወቅቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ዘርፈው ከአገር ለመውጣት ሲዘጋጁ የነበሩትን ሁሉ "በሕግ ማስከበር እና በህልውና ዘመቻው የተሳተፉ" ተብለው የተሸለሙ አሉ። ይህም ማለት በላይ ዘለቀን በስቅላት ባንዳውን ለሹመት እንደማለት ነው።

ለሀሳብ ለአስተያየት በዚህ ሊንክ @Tadeletibebut
22.3K viewsTadele Tibebu, edited  12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 19:37:06 ዐማራ ማሸነፍ ያቃተው ፊት ለፊት የሚመጣው ጠላቱን ሳይሆን፣ እንደ ጥገኛ ተዋህስያን በውስጡ ተለጥፎ የሚኖረውን ሆዳሙን ዐማራ ነው። ይህ ኃይል ከህወሓት በላይ ለፕሮፌሰር አስሥራት ወልደየስ ጠላት ነበር። መዐሕድንም አፍርሷል። ዛሬም አብንን ውስጥ ውስጡን እየቦረቦረ እያፈረሰው ይገኛል። የዐማራ ህዝብ መከራ የሚረዝመው በጠላቶቹ ብርታት ሳይሆን፣ በሆዳሙ ዐማራ ይሁዳዊነት ነው።
25.2K viewsTadele Tibebu, edited  16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 21:35:53
39.0K viewsTadele Tibebu, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 21:35:52
35.7K viewsTadele Tibebu, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 21:15:47 እነዚህ የወልድያ ተመራቂዎች ናቸው። ከዚህ ውጪ ምርጫ የለም። መሰልጠን፤ መዘጋጀት፤ መደራጀት ማለት "ከዚች ምድር እናጠፋቸዋለን" (We Will Erase You From This Land) በሚል፣ የዘር ማፅዳት (Ethnic Cleansing) እና የጦር ወንጀል (War Crimes) እየተፈፀመበት ያለውን ዐማራን መታደግ ነው።

ፋኖ ደግሞ እንኳን ለራሱ አገር ተወረረች በተባለ ጊዜ ሁሉ መደበኛ ስራውን ወደ ጎን በመተው “እምቢ ለሃገሬ” ብሎ ህይወቱን የገበረ በሰላም ግዜ አራሽ፤ በጭንቅ ጊዜ ተኳሽ ነው። ፋኖነት በዘመናት መለዋወጥ የማይደበዝዝ ፤ በስርዓት መቀያየር የማይሸረሸር የነፃነት አርማ ነው።

ፋኖ የተከበረና የሀገር አደራ የተቀበለ ከ1928 ዓ.ም የጣሊያን ወረራ በኋላ ሀገርን ነፃ ያወጣ የጀግኖች መጠሪያ ነው፡፡ ከእኔ በላይ ለሀገር ለህዝብ ብሎ ያለፈ ትውልድ ነው።
30.4K viewsTadele Tibebu, 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 10:44:53
30.2K viewsTadele Tibebu, 07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ