Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.57K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 43

2022-09-04 18:36:27
13.8K viewsTadele Tibebu, 15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 18:36:23
13.8K viewsTadele Tibebu, 15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 18:35:50 ዐማራነት ስንል ሰው-ነት፣ ህግነት እና ህገመንግስትነት ማለታችን ነው። ይህን ስንል ዐማራ፣ የተጎዳ ሰው ሲያገኝ እኔን ይድፋኝ ብሎ የሰውን ችግር እንደራሱ የሚያይ የሞራል ልዕልና ያለው ህዝብ ነው።

"እንኳን ሰው ወፍ አለምዳለሁ" የሚል እንግዳ ተቀባይ (hospitable)፣ ለሃይማኖቱ ቀናኢ፣ ሠላማዊ፣ ፍቅር፣ ለጋሽ፣ ቸር፣ አቃፊ፣ አልቦና ጠምቆ የሚያጠጣ፣ አምርቶ አገር የሚቀልብ፣ ፈትሎና ሸምኖ አገር የሚያለብስ በጣም የዳበረ ባህል (rich culture) ያለው ህዝብ ነው። እንኳን ለሀገርና ለወገን ደሙን እያፈሰሰ አጥንቱን እየከሰሰ ላለ ሠራዊት ቀርቶ በዐማራ ባህል መሽቶበት ማረፊያ የጠየቀ እንግዳ ወይም መንገደኛ የእግዚአብሔር እንግዳ ነው። የደከመው ያርፍበታል፣ የተጠማ ይጠጣበታል፣ የተራበ ይበላበታል፣ የታረዘ ይለብስበታል፣ የተከዘ ይጽናናበታል። ከአልጋ ወርዶ፣ እልፍኝ ለቆ እንግዳ መቀበል የዐማራ ህዝብ ማህበራዊ ቅርሱ ነው። ዶናልድ ሌቪን Wax and Gold በተባለው መጽሐፉ ስለ ዐማራ እንግዳ ተቀባይነትና አክባሪነት ሚከተለውን ጽፏል፣

"በዐማራ ዘንድ የእግዜር እንግዳን ተቀብሎ ከራስ በላይ አስተናግዶ ማሳደር የተለመደ ማኅበራዊ መገለጫ ነው። የእግዜር እንግዳ ሲመጣ እግሩን ይታጠባል፤ ቡና ይጠጣል፤ ጠላ ይጠጣል፤ ጥሩ ምግብ ይበላል፤ በባለቤቶቹ መኝታ ላይ ተነጥፎለት እስከመተኛት መስተንግዶ ይደረግለታል። እሱ ብቻ ሳይሆን የጭነት ወይም የኮርቻ ከብት ይዞ እንደሆን እንክብካቤን ያገኛሉ። እንግዳ ወዳድ በመሆናቸው 'ብሉ እንጅ፤ ጠጡ እንጅ' የሚሉ አገላለጾችን ይጠቀማሉ። ይሄ መስተንግዶ ለዘመድ፣ ለወዳጅ ለጓደኛ ለማንኛውም ሰው ሊደረግ የሚችል ነው። (Wax and Gold፣ 246)

ዐማሮች እጅግ በጣም እንግዳ ወዳድ በመሆናቸው ሲያስተናግዱ እንግዳ በልቶ የጠገበ፤ ጠጥቶ የረካ ስለማይመስላቸው በፈገግታ፣ በትህትና፣ በፍቅርና በአክብሮት "አፈር ስሆን፣ ብሉ እንጅ፣ ጠጡ እንጅ" የሚል አገላለጽ ይጠቀማሉ። ይህም የመንፈሳዊ ሥልጣኔ (moral civilization) መገለጫ ነው።

የዛሬ ዓመት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ሲወጣ የዐማራ ሕዝብ እጅ እየነሳ፣ እያጎረሰ፣ እየዳበሰ፣ ሲቀበላቸው እንባቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ሲያለቅሱ አይተናል።

ዐማራ ጀግናን ማጀገን ያውቅበታል እና ክብር ለሚገባው ክብር ሰጥቷል፡፡ ፍቅር ለሚገባው ፍቅር አሳይቷል፡፡ በመከራውም ቀን አብሮት ሊዘልቅ ቃሉን አጽንቷል፡፡ ዐማራ በልኩ ተገኘ። ደግነቱን አሳዬ፡፡ ጀግናው ወታደርም ስለ ፍቅር አንጀቱ ተላወሰ፡፡ እንባ ከዓይኖቹ አፈሰሰ፡፡

በወቅቱ አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል በውስጥ መስመር እንዲህ የሚል መልእክት ነበር የላከልኝ፤

"የደቡብ ተወላጅ ነኝ። በትግራይ ምድር ለግዳጅ ከ6 ወር በላይ ቆይቻለሁ። በእነዚህ ወራቶች ራሱ ህዝቡ ወግቶናል፣ በውሃ እና በምግብ ላይ መርዝ እየጨመሩ ገድለውናል። በተሳሳተ መንገድ እየመሩ አስከብበውናል። ከዛ ሁሉ ከባድ ትግል ወጥተን ወደ አማራ ክልል ስንገባ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በመንገድ ዳር ቆሞ እያጨበጨበ ተቀበለን። ምሳ ወይንም ቁርስ ልንበላ በወረድንበት ሁሉ ህዝቡ በየቤቱ እንጀራ እያዋጣ ነው የመገበን። በትግራይ ምድር ከባዱን ፈተና ያሳለፉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ውስጣቸው ተነክቶ ሲያለቅሱ አይቻለሁ። በርግጥ ቢያለቅሱ አይገርምም። ከኋላው ሲወጋ የነበረ ሠራዊት፣ እንኳን ደህና መጣችሁ፣ አፈር ስሆን፣ በሞቴ ብሉልኝ ጠጡልኝ
ሲባል ባያለቅስ ነበር የሚገርመው። ባጠቃላይ የዐማራ ህዝብ ላደረገልን አቀባበል፣ ግብዣና ላሳየን ፍቅር እኔና ጓደኞቼ ማመስገን እንፈልጋለን። ይሄን መልእክት አደራ አድርስልን"

ዐማራ ዛሬም ለወገን ጦር ደጀንነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ሩሲያዊው እስክንድር ቡላቶቪች እንዳለው "ዐማራን እግዚአብሔር ይሁነው"
13.6K viewsTadele Tibebu, edited  15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 08:09:01
12.6K viewsTadele Tibebu, 05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 08:08:56
12.7K viewsTadele Tibebu, 05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 08:08:41 #ሼር_ፖስት ሌላኛው የአዲስ አመት መምጣቱን የሚያበስረው እንግጫ ነቀላና ከሲኝ አጨዳ በዓላት ደግሞ ደረሰ። ይህ በዓል በጎጃም በየዓመቱ ከዻጉሜ 1 ቀን እስከ መስከረም 1 ቀን በድምቀት የሚከበር በዓል ሲሆን፣ ልጃገረዶችና ጎረምሶች የአዲስ ዓመት መግባትን ለማብሰር የሶሪት አበባ ፣ የአደይ አበባና የከሲኝ ቅጠል ለቤተዘመዶቻቸው በማበርከትና በመጨፈር መልካም ምኞታቸውን ጭምር የሚገልፀበት ባህላዊ ስነ ስርዓት ነው።

እንግጫ የሳር አይነት ነው። ልጃገረዶች ወንዝ ወርደው እንግጫ ይቆርጣሉ። በዚያው ቀን ማምሻ የቆረጡትን እንግጫ በአደይ እና በሶሪት አበባ ይጎነጉኑታል። ሲነጋ ሊጃገረዶቹ ከያሉበት ተጠራርተው በመሰባሰብ በየሰው ቤት እየዞሩ የተጎነጎነውን እንግጫ የቤቱ ምሰሶ ላይ በማሰር አዲሱን አመት ያበስራሉ። ስጦታውም ከቤተ ክርስቲያኑ አምድ ላይ ይታሰራል፡፡ ይህ ባህላዊ ክዋኔ በዜማና በጭፈራ የታጀበ ነው።

የቅዱስ ዮሀንስ ያልዘፈነች ቆንጆ
ቆማ ትቀራለች እንደ ሰፈር ጎጆ

እቴ አደይ አበባ ነሽ
ውብ ነሽ ውብ ነሽ

ይህንን ዜማ ልጃገረዶች እንግጫውን እየነቀሉ ያዜማሉ። ይህንን ዜማ ሲሰሙ የአካባቢው ጎረምሶች ወደ ልጃገረዶቹ ይመጣሉ። ይህኔ ታዲያ ዜማው ይቀየራል።

እንግጫችን ደነፋ፣
ጋሻውን ደፋ

እንግጫዬ ነሽ ወይ
እሰይ እሰይ

የቅዱስ ዮሀንስ የመስቀል የመስቀል
የላክልኝ ድሪ ሰላላ መላላ
መልሰህ ውሰደው ጉዳይም አይሞላ

ይህንን ዜማ ሲሰማ ለወደዳት ልጃገረድ ማተብ ያስርላታል።

ከእንግጫ ነቀላ በተጓዳኝ ከነሐሴ እኩሌታ ጀምሮ የሚከበረው በዓል ከሴ አጨዳ ነው፡፡ ከሴ ጥሩ ሽታ/መዓዛ ያለው ተክል ወይም ቁጥቋጦ መጠሪያ ስም ነው፡፡ የከሴ አጨዳ የፆመ ፍስለታን መፈታት ምክንያት በማድረግ ነሐሴ 16 ጀምሮ የተክሉን ቅርጫፎች በመቁረጥ ዝማሬ እያሰሙ ለቤተሰብ፣ ለጎረቤት እና ለቤተ ክርስቲያን እንኳን አደረሳችሁ በማለት ስጦታ የሚያበረክቱበት በዓል ነው፡፡ የበዓሉ ስያሜም ከተክሉ ስምና ነሐሴ 16 ላይ ካለው ክዋኔ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ እንኳን አደረሳችሁ!
12.3K viewsTadele Tibebu, edited  05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:16:43
11.7K viewsTadele Tibebu, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:16:12 #ሼር_ፖስት ኮሜዲያን እሸቱ መለሰን አመስግኑልኝ። በውነቱ የሥራህው ሥራ ድንቅና አርአያ የሚሆን ነው። እሸቱ በቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ስም ለተቋቋመ ገዳም የእርሻ ትራክተር አበርክቷል። ይህ ገዳም አዊ ዞን ከዳንግላ ከተማ ምዕራብ አቅጣጫ 18 ኪ.ሜ ጉዞ በኋላ ወንደፋይ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል። ወለተ ጴጥሮስ አንድነት ገዳም በዐፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት በጻዲቋ ወለተ ጴጥሮስ የተመሰረተች ጥንታዊትና ታሪካዊት ገዳም ናት፡፡ እሸቱ ላደረግህው መልካም ሥራ እናመሰግናለን
11.8K viewsTadele Tibebu, edited  18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 19:45:11
15.3K viewsTadele Tibebu, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 19:45:06
15.0K viewsTadele Tibebu, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ