Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.80K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 49

2022-06-18 17:46:18
13.5K viewsTadele Tibebu, 14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 17:45:57 አማራ ባንክ ከባንክ ባሻገር ብዙ ትምህርት አግኝተንበታል። ከዚህ በፊት ያልሞከርነው የለም ግን በተለያዩ ምክንያቶች ከሽፏል፤ ያልጀመርነው የለም ግን ወደፊት መራመድ ሳንችል ቀርተን ረግረግ ውስጥ እንደሰጠመች እህያ ገብተን ቀርተናል፤ የተጀመረው ትግል ቶሎ ያበበ ይመስልና ሳያፈራ ቶሎ ደርቋል፤ ደርቆ አልቀረም፤ ሻግቷል፤ ሻግቶ አልቀረም፤ በስብሷል፤ በስብሶ ፈራርሷል። በዐማራ ታሪክ ትግል ውስጥ እንዲህ ያለ የመክሸፍ ታሪክ ለብዙ ምዕተ ዓመታት ግዙፍ ቦታ የያዘ ይመስለኛል። ዛሬ ይሄን የመክሸፍ ታሪክ የሰበረው አማራ ባንክ ብቻ ነው። የሩቁን ትተን ከቅርቡ ስንነሳ መዐሕድ ከሽፏል፤ አሥራት ቴሌቪዥን ከሽፏል፤ አብን'ም የመክሸፍ መንገድ ላይ ይገኛል.....

ዐማራ ይጀምራል ይከሽፍበታል። የ1953ቱ የመንፈቅለ መንግሥት ሙከራ ያደረጉት መንግሥቱ ነዋይ፣ ገርማሜ ነዋይና ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ ሦስቱም ዐማሮች ናቸው። ግን ሙከራቸው ከሽፏል። የፀጥታ ሀላፊው ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ ራሳቸውን አጠፉ፡፡ ገርማሜ ራሳቸውን አጠፉ፡፡ መንግሥቱ ነዋይ ልክ እንደ በላይ ዘለቀ በስቅላት እንዲቀጡ ተፈረደበት፡፡

የጃንሆይን መንበር ያነቃነው የጎጃም የገበሬዎች ዐመፅ ነበር። ከታኅሣሡ የመንፈቅለ መንግሥት ሙከራ በኋላ የተማሪዎችን አብዮት የመሩት እንደ ተራራ የገዘፈ ታሪክ የነበራቸው የዐማራ ተማሪዎች ነበሩ። ምንም እንኳን ዐማራን ለማጥፋት በትር ሆነው ቢያገለግሉም በተማሪዎች የለውጥ እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና የነበራቸው እነዋለልኝ መኮንን፣ ጎንደር ፋሲለደስ ትምህርት ቤት፣ ደሴ የወይዘሮ ስሂን ትምህርት ቤት ዘውዳዊው ሥርዓት እንዲገረሰስ የትግል ማዕከል ሆነው አገልግለዋል።

ነገርግን ትግላቸው ገና ከጅምሩ መስመሩን ስለሳተ ከሸፈ፤ ይባስ ብሎ፣ "ማርክስ እንዳለው …፣ ኤንግልስ እንዳለው…፣ ሌኒን እንዳለው …፣ ማኦ እንዳለው …፣ ቼጉቬራ እንዳለው…፣ ሆቺሚኒ እንዳለው…፣ እስታሊን እንዳለው…፣ " ወዘተ እያሉ ዐማራ ሆነው በፀነሱት ትግል መልሰው ዐማራውን ከሰሱት። በዚህ የታሪክ ክሽፈት ውስጥ ሀገሪቱ በደርግ እጅ ወደቀች።

ለ17 ዓመት በአብዮት ስም የቀጠለው ደርግ በዐማራው ላይ የደረሰው እልቂት፣ እሥራት፣ ስደት፣ ውርደት፣ ጉስቁልና፣ የአእምሮ ጉዳት፣ የአካል ስንኩልነት፣ በአገር ሀብት ላይ፣ በእጽዋት፣ በእንስሳት፣ በአዕዋፍም ላይ የተፈፀመው ውድመት መቼም የማይረሳ፣ በዐማራ ሕዝብ መስተልይ ተቀርጾ ያለ ጉዳይ ነው።
በእብሪት፣ በድንቁርናና ስካር ናላቸው ያዞረው የደርግ አለቆች የዐማራ ልጆችን ረሸኑ። ሕግና ሥርዓት የአብዮቱን ግለት የሚያቀዘቅዙ ሂደቱንም የሚያደናቅፉ የቡርዥዋ መሣሪያ ናቸው እየተባለ ሕግ ተሽሮ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ነፃ እርምጃ ተፈቀደ። ዐማራ ልጆቹ በቀይ ሽብር እንደ ቅጠል እረገፉበት።

"ቀይ ሽብር ሞኝ ነው ጠላቱን አይለይም፣
ያገኘውን ሁሉ ያጋድማል የትም።" የተባለው በዚህ ዘመን ነው።

አሁንም ዐማራው ለውጥ በመፈለግ ትግል ጀመረ። ደርግን በመቃወም፣ መሳሪያ አንስቶ በመታገል ቀዳሚው የዐማራ ህዝብ ነበር።ለምሳሌ፣ በ1970'ዎቹ በምድረ ጎጃም ሞጣና ብቸና እነ ባምላኩ አየለ፣ የሺዋስ አያሌው፣ ውባለ ተገኑና ምቹ ውድነህ ለሕዝባቸው መብት መከበር በመምራትና በማጠናከር ረገድ የተጫወቱት ሚና ቀላል አልነበረም። ከዋና ዋናዎቹ የጎጃምን አመፅ ከመሩት ሰዎች መካከል የብቸናው ባምላኩ አየለ አንድ አይና ጀግና መሪ ስለነበር፣

"በአምላኩ አባ ጊዮን የበረሃው መናኝ
በአንድ አይኑ ፀዳቂ በሌላው ተኮናኝ" ተብሎ ተወድሷል።

ነገርግን በዐማራ ውድ ልጆች ከፍተኛ መስዋዕትነትና በሌሎችም ሕዝቦች ተጋድሎ ደርግ ቢገረሰስም ቀጥሎ በመጣው የህወሓት ሥርዓት ዐማራ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጨቋኝ፣ ተሳዳጅና የትም የሚገደል ሆነ።

እንደገና የህወሓት/ኢሕአዴግ ሥርዓትን በመጣል የዐማራ ህዝብ ቀዳሚ ነው። በ2008 ዓ.ም. የገነፈለው የዐማራ ህዝብ አመፅ ለህወሓት መውደቅ ከፍተኛ ሚና ነበረው። ነገርግን ዐማራ መስዋዕትነት የከፈለለት ትግል አሁንም ሃዲዱን ስቶ ቁልቁለት ላይ ይገኛል....

ዐማራ ትግል ይጀምራል፤ ተቋም ለመመሥረትም ይጥራል ግን ይከሽፍበታል። ዐማራ እንደዚህ ያሉ የመክሸፍ ብዙ ታሪኮች አሉት። በተጨባጭና በሚዳሰስ መልኩ ይሄን የመክሸፍ ታሪክ የሰበረው አማራ ባንክ ብቻ ነው።

አማራ ባንክንም ቢሆን ገና ከፅንሱ ለማጨናገፍ ያልተሄደበት ሙከራ የለም፤ የባንኩን ፕሮሰስ የሚያስኬዱትን ሰዎች ሳይቀር የፌስቡክ ዘመቻ ተከፍቶባቸው ብዙ ተብለዋል፤ ታምተዋል፤ ነገርግን ሰዎቹ የዋዛ ስላልነበሩ መሰናክሉን ሁሉ በጣጥሰው በአንድ ቀን ብቻ 72 ቅርንጫፎችን በመክፈት ታሪክ ሰርተዋል።

ከዚህ ባንክ የምንመራው ብዙ ቁምነገር አለ። ትግስት፣ የዓላማ ፅናት፣ እውቀት፣ ብልሃት፣ እልህ፣ ቁጭት፣ አይበገሬነት፣ ታማኝነት፣ መተባበር፣ መደጋገፍ፣ መደማመጥ፣ በመጨረሻም አሸናፊ ሆኖ መውጣት የአማራ ባንክ መገለጫዎች ናቸው።

ከዐማራ ባንክ እኩል ታቅደው የነበሩት የ" እኛ ለእኛ በእኛ" የመቶ ፕሮጀክቶች ለምሳሌ፣

1 ጣና ፔትሮሊየም
2. ዳግማዊ ምኒልክ ዩኒቨርስቲ
3.ዛግዌ የሕክምና አገልግሎቶች ማዕከል
4.ጃኖ ባንክ አክሲዮን ማህበር
5.አምደ ወርቅ ሲሚንቶ ፋብሪካና ሌሎችም ከአማራ ባንክ ልምድ ቀስመው የሀሳቡ ባለቤቶች ቢያንቀሳቅሱት እና የክሽፈትን ታሪክ ተረት ቢያደርጉት
ትውልድ ይኮራ ነበር።

ለሀሳብ ለአስተያየት በዚህ ሊንክ @Tadeletibebut
13.1K viewsTadele Tibebu, edited  14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 16:21:20
14.0K viewsTadele Tibebu, 13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 16:20:52 እንዴት ከረማችሁ? ባለፈ ጊዜ የዐማራ ጠላቱ ራሱ ነው የሚል ነገር ጽፌ በፈረንጆች may 9 ለ30 ቀን ፌስቡክ አገደኝ። ያገደበትን ምክንያት ስክሪንሻት ላይ ተመልከቱት። ከዚህ በኋላ ለድርጅቱ ኮሚቴ የቅሬታ ማመልከቻ ከአስገባሁ በኋላ 25 ፐርሰንት ብቻ ለሚሆኑት እንዲታይ ፈቅዶ 75 ፐርሰንት ለሚሆነው እንዳይደርስ አግዶኝ ቆዬ። ከምንም ይሻላል ብዬ ስለነ ብርጋዲየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ እና ስለፋኖዎች መታሰር ጽፌ ሳልጨርስ፣ በጣም በሚያስገርም ሁኔታ ስክሪንሹት ላይ እንምታዩት በፈረንጆች Nov 3/2021 ህወሓት የደሴን ከተማ ለመቆጣጠር ሞርተር መተኮሱንና የድሮን እርምጃ እንደተወሰደ
ያጋራሁትን መረጃ Hate speech ብሎ በተጨማሪ ቅጣት አካውንቴን Restricted አደረገው። በኋላ ላይ ሳረጋግጥ በተደጋጋሚ ሪፖርት ያደረገ ግሩፕ እንዳለ ገባኝ። እንደምታዩት ለማስረጃ ብዬ may 9 ቀን ስክሪን ሹት ሳደረገው ፔጁ የሚለቀቀው አንዱ 9 ቀን ሁለተኛው 39 ቀን ይቀራል ይላል።

በወሳኝ ወቅት እንዲህ ያለ ቅጣት ህመም ነው።
ታግሶ ከመጠበቅ ውጪ ምርጫ አልነበረኝም።
ቢያንስ ለታሰሩት ድምፅ መሆን ባልችል የታሰሩትን መጠየቅ ይገባል በሚል በየፖሊስ ጣቢያው፣ ከዛም ጋይንት ድረስ እየሄድኩ የታሰሩትን አህት ወንድሞች ስጠይቅ ነው የከረምኩት። በርግጥ ብዙዎቹ መፈታት ጀምረዋል። በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ።

አሁንም የታሰሩ አሉ። ለምሳሌ ያለለት ወንድዬ እና ቲና በላይ መጥቀስ ይቻላል። ያለለት ወንድዬን ዘጠኛ ፖሊስ ጣቢያ እያለ ጠይቄው ነበር። 16 ቀን ሙሉ ፍርድቤት ሳይቀርብ ፖሊስ ጣቢያ ቆይቶ ወደ ማረሚያ ቤት ተወስዷል።

ጎን ለጎን በተደጋጋሚ ለፌስቡክ ቅሬታዬን እየላክሁ ስለነበር ትናንት ማታ ላይ ቅጣቱን አንስቶታል። እንደተነሳ ያየሁት ጥዋት ላይ ነበር።

ከዚህ በተረፈ በፌስቡክ ቅጣት ምክንያት ልሳኔ ተዘግቶ ቆዬ እንጂ እኔ ምንም የሆንኩት ነገር የለም። ብዙዎቹ በinbox አንዳንዶቹ በስልክ፣ በቴሌግራም፣ በፌስቡክ ተጨንቃችሁ ደህንነቴን የጠየቃችሁኝ እህት ወንድሞች እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ያክብርልኝ

ከዚህ በኋላ መጻፌን እቀጥላለሁ፣... በዚህ አጋጣሚ የዐማራ ባንክ በይፋ ሥራ በመጀመሩ ደስታ ተሰምቶኛል፣ እንኳን ደስ ያላችሁ!
15.5K viewsTadele Tibebu, 13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 20:58:16
11.4K viewsTadele Tibebu, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 20:55:55 ብርጋዲየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከሚገኘው 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ። መጀመሪያ ታፍነው እንደተሰወሩ አዲስአበባ ብሥራተ ገብርኤል አካባቢ ታስረው እንደነበረ የታወቀ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ከአዲስአበባ ወደ ባህርዳር እንዲዛወሩ ሆነዋል።
11.7K viewsTadele Tibebu, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 20:49:11 አቡነ አብርሃም ሠላም መሆናቸውን አሁን ደውዬ አረጋግጫለሁ። አባታችን ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ አዲስ አበባ ነው የሚገኙት
11.9K viewsTadele Tibebu, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 12:32:30
18.9K viewsTadele Tibebu, 09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 12:31:55 ፋኖ ግርማ መንግሥቱን ዛሬ ረፉዱ ላይ አስረውታል። ለምን እንደታሰረ ተቋቋመ የተባለው ኮማንድ ፖስት ብቻ ነው የሚያውቀው። ጀኔራል ተፈራ ማሞ ታፍኖ ተወስዷል። ማን እንደያዛቸው እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም። የምኒልክ ብርጌድ አዛዥ ፋኖ አተነህ ድረስ፣ ፋኖ ሰለሞን አባተ (በጦርነቱ የቆሰለ)፣ ፋኖ ጌታቸው ሙጩ እና አሸናፊ አካሉ (ከዚህ በፊት ታስሮ ቶርቸር የተደረገ) ከታሰሩት መካከል ይገኙበታል። በጣም የሚያስገርመው ሰሞኑን በተካሄደው ሽልማት የታሰሩም አሉ። በጦርነቱ የቆሰሉ ሁሉ ታስረዋል። እንዲህ ያለ የጅምላ አፈሳ ምን አይነት መፍትሔ እንደሚያመጣ አላውቅም።

*በዚህ አጋጣሚ ፌስቡክ ለ30 ቀን 65 ፐርሰንት ለሚሆነው ተከታይ እንዳይደርሳቸው ስለታገደ መረጃውን copy እያደረጋችሁ ፖስት አድርጉት።

ለሀሳብ ለአስተያየት በዚህ ሊንክ @Tadeletibebut
19.7K viewsTadele Tibebu, edited  09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 22:26:48 ጠላት የክረምት ጦርነት ለማድረግ እየተዘጋጀ ባለበት ወቅት፣ አንድነትን እያጠናከሩ ከመዘጋጀት ይልቅ ሜዳልያ የሚሉት አጀንዳ አምጥተው እንዲህ ያለ ጎራ መፍጠር ዕኩይ ዓላማ እንጂ ማበረታቻ ሊሆን አይችልም። በፍፁም!! ህወሓት በራያ፣ ከሽሬ ወዲህ በሽሬላ ጦሩን እያስጠጋ፣ እዚህ ደግሞ ሁሉም እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፤ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆኖ እንዳይዘምት እርስበርሱ የሚያጣላ አጀንዳ አመጡብን! አማካሪም፥ መካሪም ያጣ ክልል!
19.8K viewsTadele Tibebu, 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ