Get Mystery Box with random crypto!

እንዴት ከረማችሁ? ባለፈ ጊዜ የዐማራ ጠላቱ ራሱ ነው የሚል ነገር ጽፌ በፈረንጆች may 9 ለ30 | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

እንዴት ከረማችሁ? ባለፈ ጊዜ የዐማራ ጠላቱ ራሱ ነው የሚል ነገር ጽፌ በፈረንጆች may 9 ለ30 ቀን ፌስቡክ አገደኝ። ያገደበትን ምክንያት ስክሪንሻት ላይ ተመልከቱት። ከዚህ በኋላ ለድርጅቱ ኮሚቴ የቅሬታ ማመልከቻ ከአስገባሁ በኋላ 25 ፐርሰንት ብቻ ለሚሆኑት እንዲታይ ፈቅዶ 75 ፐርሰንት ለሚሆነው እንዳይደርስ አግዶኝ ቆዬ። ከምንም ይሻላል ብዬ ስለነ ብርጋዲየር ጄኔራል ተፈራ ማሞ እና ስለፋኖዎች መታሰር ጽፌ ሳልጨርስ፣ በጣም በሚያስገርም ሁኔታ ስክሪንሹት ላይ እንምታዩት በፈረንጆች Nov 3/2021 ህወሓት የደሴን ከተማ ለመቆጣጠር ሞርተር መተኮሱንና የድሮን እርምጃ እንደተወሰደ
ያጋራሁትን መረጃ Hate speech ብሎ በተጨማሪ ቅጣት አካውንቴን Restricted አደረገው። በኋላ ላይ ሳረጋግጥ በተደጋጋሚ ሪፖርት ያደረገ ግሩፕ እንዳለ ገባኝ። እንደምታዩት ለማስረጃ ብዬ may 9 ቀን ስክሪን ሹት ሳደረገው ፔጁ የሚለቀቀው አንዱ 9 ቀን ሁለተኛው 39 ቀን ይቀራል ይላል።

በወሳኝ ወቅት እንዲህ ያለ ቅጣት ህመም ነው።
ታግሶ ከመጠበቅ ውጪ ምርጫ አልነበረኝም።
ቢያንስ ለታሰሩት ድምፅ መሆን ባልችል የታሰሩትን መጠየቅ ይገባል በሚል በየፖሊስ ጣቢያው፣ ከዛም ጋይንት ድረስ እየሄድኩ የታሰሩትን አህት ወንድሞች ስጠይቅ ነው የከረምኩት። በርግጥ ብዙዎቹ መፈታት ጀምረዋል። በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ።

አሁንም የታሰሩ አሉ። ለምሳሌ ያለለት ወንድዬ እና ቲና በላይ መጥቀስ ይቻላል። ያለለት ወንድዬን ዘጠኛ ፖሊስ ጣቢያ እያለ ጠይቄው ነበር። 16 ቀን ሙሉ ፍርድቤት ሳይቀርብ ፖሊስ ጣቢያ ቆይቶ ወደ ማረሚያ ቤት ተወስዷል።

ጎን ለጎን በተደጋጋሚ ለፌስቡክ ቅሬታዬን እየላክሁ ስለነበር ትናንት ማታ ላይ ቅጣቱን አንስቶታል። እንደተነሳ ያየሁት ጥዋት ላይ ነበር።

ከዚህ በተረፈ በፌስቡክ ቅጣት ምክንያት ልሳኔ ተዘግቶ ቆዬ እንጂ እኔ ምንም የሆንኩት ነገር የለም። ብዙዎቹ በinbox አንዳንዶቹ በስልክ፣ በቴሌግራም፣ በፌስቡክ ተጨንቃችሁ ደህንነቴን የጠየቃችሁኝ እህት ወንድሞች እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ያክብርልኝ

ከዚህ በኋላ መጻፌን እቀጥላለሁ፣... በዚህ አጋጣሚ የዐማራ ባንክ በይፋ ሥራ በመጀመሩ ደስታ ተሰምቶኛል፣ እንኳን ደስ ያላችሁ!