Get Mystery Box with random crypto!

አንደኛ ተሸላሚ የሚባል ነገር የለም፤ ትክ የሌላትን ነፍሱን ለመስጠት የዘመተ ሁሉ ለኔ የወርቅ ሜዳ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

አንደኛ ተሸላሚ የሚባል ነገር የለም፤ ትክ የሌላትን ነፍሱን ለመስጠት የዘመተ ሁሉ ለኔ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ነው። አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ሦስተኛ እያሉ ደረጃ ማውጣት ምን ማለት ነው? በዚህ የህልውና ዘመቻ በሺህ የሚቆጠር ሰው ሞቶአል፣ ቆስለዋል፣ የአካል ጉዳተኛ ሆነዋል፣ አሁንም ከቁስላቸው ያላገገሙ፣ በቦንብ ፍንጣሪ አይናቸው ጠፍቶ በሰው የሚመሩ፣ እግራቸው ተቆርጦ በሰው ድጋፍና በክራንች የሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች፣ ልዩ ኃይልና ሚኒሻዎች አሉ። በእነዚህ መካከል የወርቅ፣ የብር፣ የንስሐ ሽልማት እያሉ ደረጃ ማውጣት ትክክል አይደለም። ምሥጋና ማቅረብና የተጎዱትን ለመርዳት ምን እንደታሰበ ማሳወቁ ብቻ በቂ ነበር።

ሌላው ሽልማቱ በጥናት ላይ የተመረኮዘ ስለመሆኑ ጥርጣሬ አለኝ። እንደማየው ከሆነ በቴሌቪዥንም ሆነ በፌስቡክ የተወራላቸው ሰዎች፣ ተደጋጋሚ ድጋፍና እገዛ ያገኙ ሰዎች ናቸው ሽልማቱ ላይ ያየኋቸው። ጀብዱ የፈፀሙ ግን የሚዲያ ሽፋን ያላገኙ፣ ጀብዱ ፈጽመው ልጃቸውን ጥለው የሞቱ ግን ድጋፍ ያልተደረገላቸው፣ አንዳንዶቹ ስማቸው ያልተመዘገበ ግን በራሳቸው ፍቃድ ዘምተው ታሪክ የሰሩ እንዳሉ አውቃለሁ።

በዚህ ሽልማት ቢያንስ ሚስቶቻቸው ይገኛሉ ብዬ ጠብቄ ነበር ግን የተጋበዙ ሰዎች አስቀድሞ የሚዲያ ሽፋን የነበራቸው ናቸው። ያለጥርጥር 12 እና ከዛ በላይ ጠላት ረፍርፈው የሞቱ እንዳሉ አውቃለሁ፣ በአይኔም ያየሁት ነገር ነው። ግን በዛሬው ሽልማት አልተካተቱም።

ይህ ተጎጂ ቤተሰቦችን ከሃዘናቸው በላይ ማሳዘን ነው። በእነዚህ ሀዘንተኞች ላይ የደረጃ ምደባ ማውጣት ትክክል አይደለም ያልኩት ለዚህ ነው። ከጥቅሙ ይልቅ ፋኖን ለመከፋፈል የተደረገ ድራማ ነው የሚመስለው።

ሌላው በሽልማቱ በወቅቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ዘርፈው ከአገር ለመውጣት ሲዘጋጁ የነበሩትን ሁሉ "በሕግ ማስከበር እና በህልውና ዘመቻው የተሳተፉ" ተብለው የተሸለሙ አሉ። ይህም ማለት በላይ ዘለቀን በስቅላት ባንዳውን ለሹመት እንደማለት ነው።

ለሀሳብ ለአስተያየት በዚህ ሊንክ @Tadeletibebut