Get Mystery Box with random crypto!

እነዚህ የወልድያ ተመራቂዎች ናቸው። ከዚህ ውጪ ምርጫ የለም። መሰልጠን፤ መዘጋጀት፤ መደራጀት ማለት | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

እነዚህ የወልድያ ተመራቂዎች ናቸው። ከዚህ ውጪ ምርጫ የለም። መሰልጠን፤ መዘጋጀት፤ መደራጀት ማለት "ከዚች ምድር እናጠፋቸዋለን" (We Will Erase You From This Land) በሚል፣ የዘር ማፅዳት (Ethnic Cleansing) እና የጦር ወንጀል (War Crimes) እየተፈፀመበት ያለውን ዐማራን መታደግ ነው።

ፋኖ ደግሞ እንኳን ለራሱ አገር ተወረረች በተባለ ጊዜ ሁሉ መደበኛ ስራውን ወደ ጎን በመተው “እምቢ ለሃገሬ” ብሎ ህይወቱን የገበረ በሰላም ግዜ አራሽ፤ በጭንቅ ጊዜ ተኳሽ ነው። ፋኖነት በዘመናት መለዋወጥ የማይደበዝዝ ፤ በስርዓት መቀያየር የማይሸረሸር የነፃነት አርማ ነው።

ፋኖ የተከበረና የሀገር አደራ የተቀበለ ከ1928 ዓ.ም የጣሊያን ወረራ በኋላ ሀገርን ነፃ ያወጣ የጀግኖች መጠሪያ ነው፡፡ ከእኔ በላይ ለሀገር ለህዝብ ብሎ ያለፈ ትውልድ ነው።