Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.80K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-03-28 21:58:35
16.2K viewsTadele Tibebu, 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 21:58:14 #ሼር_ፖስት! የፑቲን ሀገር ሩሲያ የአማርኛን ቋንቋ በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ልትጀምር መሆኗን አስታውቃለች። በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእስያ እና የአፍሪካ ሀገራት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ እሁድ እለት በሩሲያ-አፍሪካ አለም አቀፍ የፓርላማ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ሩሲያ የአፍሪካ ቋንቋዎችን አማርኛንና ስዋሂሊን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር እየተዘጋጀን ነው ብለዋል።

እንደሚታወቀው ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ እያስተማረች ነው። ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) መሰጠት ጀምሯል። ከጀርመን ታዋቂ ከሆኑት ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው ሀምቡርግ ዩንበርሲቲ የአማርኛ ት/ ት ማስተማር ከጀመረ መቶ ዓመት አልፎታል።

አማርኛ ቋንቋን በ2007 ዓ.ም.የአፕል የቴክኖሎጂ ማዕከል አማርኛን ከዓለም ግዙፍ ቋንቋዎች ተርታ መድቦ የቴክኖሎጂ ቋንቋ አድርጎታል። በ2008 ዓ.ም. የጎግል የቴክኖሎጂ ማዕከል የመተርጎሚያ ቋንቋ አድርጎታል። Dstv'ም የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣የኦሊምፒክ ውድድሮችን ጨምሮ የእንግሊዝ ኘሪሚየር ሊግ ፣ የስፔን ላሊጋ ፣ የጣሊያን ሴ ሪ ኤ እንዲሁም ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቋንቋ እንዲተላለፉ ከወሰነ አመት አስቆጥሯል።

አማርኛ በUS አሜሪካ የመንግስት ቋንቋም ነው። እንዲያውም በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ዳሽ የሚባለው የከተማ አውቶቢስ ላይ "እንኳን ወደ #WESTEND በደህና መጣችሁ!" የሚል ጽሁፍ ማየትም የተለመደ ነው።
16.3K viewsTadele Tibebu, edited  18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 19:50:20
18.8K viewsTadele Tibebu, 16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 19:50:14
18.0K viewsTadele Tibebu, 16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 19:49:32 ከወንዞች ማዶ ያለች ቅዱስ ምድር...#ባህርዳር። ታዋቂው ዓለም አቀፍ አሳሽ፣ የቀድሞው የአሜሪካ መርማሪ ፖሊስ፣ አሜሪካዊው ሮበርት ኮርኑክ በ1994 ዓ.ም. "The Lost Ark of The Covenant" ወይም "የጠፋው የቃልኪዳኑ ታቦት" የሚል መጽሐፍ አሳትሟል።

በዚሁ መጽሐፍ፣ "ከወንዞች ማዶ ያለች ቅዱስ ምድር" በሚል ንዑስ ስር ስለባህርዳር ከተማ፣ ስለጃካራንዳ ወኪል አስጎብኚ ምሥጋና ገናነው፣ በአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ይሰራ ስለነበረው ገበየሁ ወጋየሁ፣ ስለጭስ አባይ፣ ስለጣና ደሴቶች... በዝርዝር ጽፏል።

በዚሁ አንቀጽ ባህርዳርን እንዲህ ይገልጻታል። "የወደብ ከተማ የምትመስል፣ ንፁህና በእፅዋት የተሞላች"

ጢስ አባይን ደግሞ ፣ " ቦታው ከ1950ዎቹ የታርባን ፊልም ጋር ተመሳሳይ ነው። ወደ ፏፏቴው ስንቃረብ መሬቱ ሲርገበግብ ተሰማን፡፡ ትንሽ ከፍ ስንል በዳመና የተሸፈነ ቦታ ደረስን፡፡ ግዙፉ ፏፏቴ ወርዶ ከድንጋይ ጋር ሲላተም የሚፈጥረው ደመናማ ውርጭ ሸለቆውን ሞልቶ ዳገቱ ድረስ ይመጣል፡፡ እኔና ጆቢ (ጓደኛው) በአድናቆት ፈዘዝን፡፡ ከፏፏቴው በመቀጠል ሰፊውን የአባይ ወንዝ በጀልባ ሆነን አየነው። የግብፅና ሱዳን የህይወት ደም ስር የሆነው ይህ ወንዝ ከቀደምት ዘመን ጋር በምናባችን አገናኘን፡፡ የምንገኝበት የኢትዮጵያ ምድር በመፅሃፍ ቅዱስ የተጠቀሰው መሆኑ ታወሰኝ፡፡ 'ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ የተበተኑ ሴት ልጆቼ ቁርባኔን ያመጡልኛል" (ትንቢተ ሶፎንያስ 3፤10)፡፡ ዙሪያዬን ቃኘሁ፡፡ በወንዞች የተከፋፈለውን ለም ምድር ስመለከት ነበር የመፅሀፍ ቅዱሷን የኢትዮጵያ ምድር መርገጤ የተሰማኝ፡፡" ይላል።

ሮበርት ኮርኑክ "ቅዱስ ሃይቅ፤ ንፅህት ደሴት" በሚል አንቀጽ ስለ ጣና ደሴትም ጽፏል።

" በአረንጓዴው የጣና ውሃ መሃል ከርቀት የምትታየው ደሴት በረግረግ ስፍራ ፀሃይ ለመሞቅ የተኛ ግዙፍ ኣዞ ትመስላለች። ...የሃይቁን ስፋትና ከምድር መነጠል ስመለከት ታቦቷን ለመደበቅ ተመራጭ ስፍራ በማለት ለራሴ አድናቆቴን ገለፅኩ። በሰፊው ሃይቅ ላይ ከ45 የሚበልጡ ደሴቶች እንዳሉ ተነገረኝ። በዚያ ላይ ሃይቁን የከበበው የተራሮች ሰንሰለት በደን የተሸፈነ ነው፡፡ ከዚህ አቀማመጡ የተነሳ ታቦቷን ፍለጋ ለሚመጣ ማንኛውም ሃይል ፈታኝ መሆኑ ይታያል፡፡...."

ይቀጥልና ስለጣና ቂርቆስ፣ በገዳሙ ስለሚኖሩ መናኞች፣ ክብ ሆነው ስለተደረደሩ የመነኮሳቱ ደሳሳ ጎጆዎች፣ ስለገዳሙ አትክልትና ፍራፍሬ በዝርዝር ያትታል። በጣም ትኩረቴን የሳበው ይህ ገለጻው ነው።

"መነኮሳት ፀሐይ ስትገባ ወደ ማደሪያቸው በመግባት ሌሊት ለፀሎት ይወጣሉ። ከጓደኛዬ ጆቢ ጋር የደሴቷ ተራራ ጫፍ ላይ ድንኳን ጣልን። የአፍሪካ ጨረቃና ከዋክብት ከሰፊው ሃይቅ ጋር የሚፈጥሩትን ህብር በአድናቆት እያየን አረፍን። በገዳሙ የሚኖሩ ህፃናቱ [የቆሎ ተማሪዎች ናቸው] መጥተው ከበቡን። ምሽቱን ከኛ ጋር ሲጫወቱ አሳለፉ። ከዚያ ምሽት በፊት ለ2500 ዓመታት ጣና ቂርቆስ ፍፁም ፀጥታ የነገሰባት የፀሎትና የፅሞና ሥፍራ ነበረች። በዚህ ምሽት ግን የገዳሟን ፀጥታ የህፃናቶች ፍንደቃ ቀየረው። በጨረቃዋ ብርሃን እየተሯሯጡ ሲጫወቱና ሲሳሳቁ አየናቸው።"

ሮበርት ኮርኑክ ይቀጥላል። "ከሌሊቱ 10፡30 ሰዓት የደውል ድምፅ ሰማንና ተነሳን። የማለዳውን ሥርዓተ-ፀሎት ለመታደም ከድንኳናችን ወጣን። የምሽቱ የህፃናት ጨዋታ የሚያስታውሱ የቸኮሌት ላስቲኮች በየቦታው ተበታትነዋል። ራዲዮኖቻችን ከመነፀሩ ጋር አስቀምጠውልን ሄደዋል። ልጆቹ ከኛ ጋር ሲሳሳቁ ቢቆዩም አንድ መነኩሴ ነበር በቁጣ ያባረራቸው። ልጆቹ ወደማደሪያቸው ሲገቡ የደሴቷ ፀጥታ ሌሊቱን ተረከበ።"

ሮበርት ኮርኑክ በጣና ቂርቆስ ገዳም ስለሙሴ ታቦት፣ በኩባያ ቅርፅ ስለተፈለፈሉት መሰዊያዎች፣ አይሁዳውያን ከታቦቷ ጋር ይዘውት ስለመጡት የመሰዋዕት ማቅረቢያ...ወዘተ ከመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጋር እያነጻጸረ ለመጻፍ ሞክሯል። የቆሙበት ሥፍራ የታቦቷ ማደሪ እንደነበር ድምዳሜ ላይ ደርሷል። መጽሐፉ የጻፈው ከአክሱም እስከ ላሊበላ ከጣና ሐይቅ እስከ ግብፅ ኤሌፋንታይን ደሴት፣ እየሩሳሌምን ጭምር በማሰስ ነበር። በመጨረሻም መጽሐፉን እንዲህ በማለት ነበር ያጠናቀቀው፣

"ኦ - ኢትዮጵያ!..ልዩ አገር!.. ልዩ ህዝብ ..ልዩ ባህል!... ቃላት የማይገልፁት ድህነት ያየለባት ሆኖም ግን የሰብአዊ ደግነት ባለፀጋ አገር ናት፡፡ ምስጢራዊቷ ምድር ውስጤ የደበቀችውን ታላቅ ምስጢር ከህዝቦቿ ጋር ለመቶ አመታት ብኖር እንኳን ልረዳው አልችልም፡፡"

viva Maki Coffee - ማኪ ቡና
16.6K viewsTadele Tibebu, 16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 07:04:07
11.9K viewsTadele Tibebu, 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 07:03:53 ”ዐማራን አከርካሪውን ሰብረነዋል” ያለው አቦይ ስብሃት ለህክምና አሜሪካ ሲገባ፣ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ በአብይ አሕመድ አገዛዝ ተከልክሎ አልጋ ላይ ተኝቶ እየተሰቃዬ ይገኛል።

የሰሜን ዕዝ በተኛበት ያረዱ ሂትለራዊያን ህክምና እንዲያገኙ ፈቅደው፣ የ1ዐ8'ኛ ኮር ምክትል ኣዛዥ፣ የሰሜን ዕዝ ኦፕሬሽናል ምክትል አዛዥ፣ በመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ የእቅድ ዝግጅት መምሪያ ሃላፊ ሆኖ ሀገሩን ያገለገለን ጀግና ህክምና መከልከል "አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ" የሚያስብል ነው።

በርግጥ ኢትዮጵያ እንዲህ ናት። በ1933 ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በጎጃም የነፃነት ጥርጊያ መንገድ ከስደት ከተመለሱ በኋላ ለሆዳቸው ያደሩ፣ ኢትዮጵያን ከጥሊያን ጋር ተባብረው ከጀርባ የወጓትን ባንዳና ስደተኞችን ሲሾሙና ሲሸልሙ በአንጻሩ የዐማራ አርበኞች የድካማቸው ዋጋ የሆነው ስቅላት፣ እሥራትና ግዞት ነበር።

የጥቁ አንበሣን እና የራስ እምሩ ኃይለሥላሴን የሽምቅ ተዋጊ አርበኛ ከፋ ውስጥ አስከብቦ ከፊሉን አስገድሎ መሪዎቹን ያሲያዘው ፍቅረ ማርያም ገብረእግዚአብሔር የወለጋ ገዥ ሲሆን፣ ፀረ-ፋሽት አርበኛ በላይ ዘለቀ እና ወንድሙ እጅጉ ዘለቀ በስቅላት ተገድለዋል። ባንዳው ራስ ሥዩም መንገሻ የትግራይ ገዥ ሆኖ የአገሪቱ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ ሲሆን፣ ፊታውራሪ ኃይሉ ደጀኔ በሞት እንዲቀጣ ተደርጓል። ስደተኞችና ባንዶች በየቢሮው ተሰግስገው እጅና ጓንት በመሆን ለአገራቸው የታገሉትን አገር ወዳድ አርበኞች ጉዳይ ለማስፈፀም የነሱ ደጅጠኝ ሲሆኑ፣ እነራስ አሞራው ውብነህ ተሰማ ያምጻሉ ተብለው ተፈርተው አብዛኛውን ግዜአያቸውን ያሳለፉት በግዞት ነበር። አርበኛው ደጃዝማች ነጋሽ ወርቅነህ በግዞት አዲስአበባ እንዳሉ ሞተው ቀርተዋል። በጥሊያን የሽምቅ ውጊያን (Guerrilla warfare) ለማቀናጀት በነሐሴ ወር 1929 ዓ.ም. ሸዋ ክፍለ ሀገር ግንደበረት ላይ በተካሄደው ስብሰባ የትጥቅ ትግሉ ዋና አስተባባሪ የነበሩትን ደጃዝማች ታከለ ወልደሃዋርያት በገዛ ቤታቸው በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል።

እነዚህና ሌሎች ታዋቂ የዐማራ አርበኞች እየተፈሩና እየተጠረጠሩ ሥልታዊ በሆነ ዘዴ እንዲጠፉ ተደርገዋል። ሌሎቹ በዚህ አስነዋሪ ድርጊት ቅስማቸው ተሰብሮ በችግር እየተበሳጩ አልቀዋል። ይህ ድርጊት ያሳዘነው ያገሬው ህዝብ ሁኔታውን እንዲህ በማለት ቅኔ ቋጠረለት፤

"አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ"
11.9K viewsTadele Tibebu, edited  04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 21:10:00 አቶ ልደቱ አያሌው "የባልበበላውም ጭሬ ልበትነው ፖለቲካ" አንብቡት። ብዙ ሰው ስለጠየቀኝ በተናጠል ከሚሆን ሁላችሁም ከዚህ አውርዳችሁ በpdf አንብቡት።
10.9K viewsTadele Tibebu, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 19:22:50
13.0K viewsTadele Tibebu, 16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 19:22:48
12.8K viewsTadele Tibebu, 16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ