Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! የፑቲን ሀገር ሩሲያ የአማርኛን ቋንቋ በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ልትጀምር መ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! የፑቲን ሀገር ሩሲያ የአማርኛን ቋንቋ በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ማስተማር ልትጀምር መሆኗን አስታውቃለች። በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የእስያ እና የአፍሪካ ሀገራት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ እሁድ እለት በሩሲያ-አፍሪካ አለም አቀፍ የፓርላማ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ሩሲያ የአፍሪካ ቋንቋዎችን አማርኛንና ስዋሂሊን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር እየተዘጋጀን ነው ብለዋል።

እንደሚታወቀው ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ እያስተማረች ነው። ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) መሰጠት ጀምሯል። ከጀርመን ታዋቂ ከሆኑት ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው ሀምቡርግ ዩንበርሲቲ የአማርኛ ት/ ት ማስተማር ከጀመረ መቶ ዓመት አልፎታል።

አማርኛ ቋንቋን በ2007 ዓ.ም.የአፕል የቴክኖሎጂ ማዕከል አማርኛን ከዓለም ግዙፍ ቋንቋዎች ተርታ መድቦ የቴክኖሎጂ ቋንቋ አድርጎታል። በ2008 ዓ.ም. የጎግል የቴክኖሎጂ ማዕከል የመተርጎሚያ ቋንቋ አድርጎታል። Dstv'ም የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣የኦሊምፒክ ውድድሮችን ጨምሮ የእንግሊዝ ኘሪሚየር ሊግ ፣ የስፔን ላሊጋ ፣ የጣሊያን ሴ ሪ ኤ እንዲሁም ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎችን በአማርኛ ቋንቋ እንዲተላለፉ ከወሰነ አመት አስቆጥሯል።

አማርኛ በUS አሜሪካ የመንግስት ቋንቋም ነው። እንዲያውም በአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት አሌክሳንድሪያ ዳሽ የሚባለው የከተማ አውቶቢስ ላይ "እንኳን ወደ #WESTEND በደህና መጣችሁ!" የሚል ጽሁፍ ማየትም የተለመደ ነው።