Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.80K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-10 10:36:17
17.3K viewsTadele Tibebu, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 10:35:42 #ሼር_ፖስት! በዛሬው ቀን ደሴ፣ እንጅባራ፣ ቢቸና፣ ፍኖተሰላም የአብይ አሕመድ አገዛዝ በልዩ ኃይል ላይ ያሳለፈውን ህገወጥ ውሳኔ ተቃውመዋል። ከጦሳ ተራራ፣ ደሴ ከተማ የተላለፈው መልእክት፦

-አባቶቻችን ወዳቀኗት አዲስአበባ ለመግባት የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም!
-በላባችን የሠራነው ቤታችን በአማራነታችን ፈርሷል!
-ታሪክ አለን፤ ታሪክ እንሠራለን!
-ኢትዮጵያ ሆይ ብረሳ ቀኜ ትርሳኝ፤ ሳላስብሽ ብቀር
ምላሴ ከትናጋዬ ትጣበቅ!
➢ የአብይ አሕመድ ቃላት ፍቺዎች፡-

-ብልጽግና - ውድቀት
-አገድነት -ሀገር መፍረስ
-ህግ ማስከበር -ህግ መጣስ
-ዴሞክራሲ -አምባገነን
-ሠላም -ጦርነት
-ፍትሕ -ፍጹም የፍትሕ እጦት
-ወንድማማችነት -ልዩነት፤ ገፊነት

➢ ብአዴን ሆይ፦ የአማራን ሕዝብ ፋኖን አደራጅልኝ፤ አስታጥቅልኝ አለህ እንጂ በትንልኝ አላለህም!


#ቢቸናዎች
-ኢትዮጵያዊነት በስብከት ሳይሆን በተግባር ይገለጽ፣
-ከዐማራ የፀዳች አገር አንፈልግም!

- አርበኛ ዘመነ ካሴ የትግላችን መነሻም መዳረሻም ነው።
-መከላከያ ሰራዊታችን በአማራ ልዩ ሀይል ላይ ከመተኮስህ በፊት ጥቅምት 24ን አስታውስ!

-ወልቃይት፣ ራያ፣ ደራና መተከል የማንደራደርባቸዉ ርስቶቻችን ናቸው።

-አማራነት መዳረሻው ጽኑ ኢትዮጵያዊነት ነው!

-የአማራ ልዩ ሀይልና ፋኖ ለኢትዮጵያ አንድነት የጀርባ አጥንት እንጅ ስጋት አይደሉም! ...እያሉ ናቸው።
17.1K viewsTadele Tibebu, 07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 20:29:53
20.3K viewsTadele Tibebu, 17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 15:30:50
8.0K viewsTadele Tibebu, 12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 15:30:40 #ሼር_ፖስት! ይህ ዛሬ ጎጃም ጅጋ ከተማ የሆነ ነው። እንዳጋጣሚ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ "ከልዩ ኃይሉ ጎን ነን" እያለ ነበር። እነዚህ ልዩ ኃይሎች ደግሞ እንዳጋጣሚ ጅጋ ከተማ ደረሱ። በዚህ ቅፅበት ህዝቡ ዙሪያቸውን ከቦ እየጨፈረ ጀግንነታቸውን በህብረት አስተጋባ። "እህል ውሃ ሳትቀምሱ ከጅጋ ከተማ አትወጡም" ተብለው ምሳ ተጋብዘው፣ ከህዝቡ ጋር ተወያይተው በክብር ተሸኝተዋል። የህዝብ ልጅ ስትሆን እንደዚህ ትከበራለህ። ህዝብ ቀድሞ ይሞትልሃል። ያለውን ይሰጥሃል። ከምንም በላይ ለአንድ ሠራዊት የሞራል ድጋፍ፣ የህዝብ አክብሮትና ፍቅር ከታጠቀው መሳሪያ በላይ ነው። ለልዩ ኃይሎቻችን የማያቋርጥ ድጋፍ በተናበበ መልኩ መቀጠል ይኖርበታል።
8.1K viewsTadele Tibebu, edited  12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 14:33:39
10.2K viewsTadele Tibebu, 11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 14:33:04 #ሼር_ፖስት! ህዝቡ ለአማራ ልዩ ኃይል እያሳዬው ያለው ድጋፍና ፍቅር ልብ ይነካል። ዱርቤቴ ላይ ወጣቱ በዳርና በዳር ቆሞ በመሀል በክብር ሲያሳልፋቸው ዕንባ የሚተናነቃቸው ልዩ ኃይሎች ታይተዋል። በተለያዩ አካባቢዎች "መዳኛችን እናተ ናችሁ፤ በጦርነቱ አላሳፈራችሁንም። ዛሬም በናተ እንኮራለን። ጀግኖቻችን" የሚል አድናቆት እየጎረፈላቸው ነው። ልዩ ኃይሉ ከህዝቡ በሚቸራቸው ሙገሳና ድጋፍ "ከህዝባችን በፊት ቀድመን እኛ እንሰዋለታለን" እያሉ ናቸው። በዚህ አጋጣሚ ስንቅና ሎጂስቲክ ተቋርጧል። ደሞዝም አልተከፈላቸውም። ስለዚህ ሁላችንም በያሉበት ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ድጋፍ ማድረግ አለብን።

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut
10.1K viewsTadele Tibebu, edited  11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 13:54:44
10.9K viewsTadele Tibebu, 10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 13:53:56 በጎንደር ከተማ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል። በሰልፉ የሚከተሉት መልዕክቶች በደማቁ ተላልፈዋል!

1.አንቀፅ 39 ሳይፈርስ ልዩ ሀይላችን አይፈርስም

2. በዓለም አቀፍ መድረክ ፊት የተደረገ የሰላም
ስምምነት በጓዳ አይቀየርም!

3. የፕሪቶሪያውን ስምምነት በጓዳ ውል መቀየር ውጤቱ ሃገራዊ ውድቀት ማስከተል ነው!

4. በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት አሸባሪው ትህነግ ትጥቅ ይፍታ!

5. ጠላት ወያኔ ለዘር ማጥፋት እየተዘጋጀ ባለበት ሁኔታ ልዩ ሃላችንን ትጥቅ ማስፈታት መንግስታዊ ክህደት ነው!

6. ለኢትዮጵያ ህልውና ዋጋ የከፈሉ ሁሉ ስለ ሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም የማወቅ መብት አላቸው!

7. ዛሬም እንደትናንቱ የምንመካው በእውነት ፣ በፍትሐዊነት እና በህዝባችን አቅም ነው!

8. በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ እየተፈጸመ ያለው ዘር-ተኮር ጥቃት ግቡ ሃገር ማፍረስ ነው! አዲስ አበባ የኢትዮጵያ አንድነት የስበት ማዕከል ናት!

9. የወልቃይት እና የራያ አማራ ማንነት ጥያቄን “የርስት ማስመለስ” ብሎ በመፈረጅ አማራን ማሸማቀቅ አያቻልም!

10. የወልቃይት-ጠገዴ-ጠለምት የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍጹም ፍትሐዊ እና ሕጋዊ ነው!

11. መንግስት የግጭት ፕሮጀክቶችን አቁሞ የልማት ፕሮጀክቶችን ይጀምር!

12. መላ ኢትዮጵያውያንን ያጎሳቆለው ፖሊሲ አመጣሽ የኑሮ ውድነት መፍትሄ ሊፈለግለት ይገባል፡፡

13. የኢትዮጵያ ዋነኛ ችግር ወያኔ የተከለው መዋቅር እና ህገ-መንግስት ነው!

14. ህዝብ ያላመነበትንና ለምክር ቤት ያልቀረበን ውሳኔ አንቀበልም

15. መከላከያ ወደ ልዩ ሀይላችን ከመተኮስህ በፊት ጥቅምት 24ን አስታውስ ።

16. የሶማሌ ህዝብና አስዳዳሪው ሙስጦፌ ስለ ኢትዮጵያ እየከፈላችሁት ላለው ዋጋ ክብር ይገባችኋል ።
10.9K viewsTadele Tibebu, 10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 09:59:05
13.9K viewsTadele Tibebu, 06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ