Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.80K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-13 16:19:43
27.6K viewsTadele Tibebu, 13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 16:19:11 እንኳን ለጽሎተ ሐሙስ በሰላም አደረሳችሁ!
ጸሎተ ሐሙስ ጌታችን ምሥጢረ ቊርባንን ከምሥጢረ ጸሎት ጋር አዋሕዶ የገለጠበት ዕለት ነው። ትህትና!
25.4K viewsTadele Tibebu, 13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 10:26:56
29.1K viewsTadele Tibebu, 07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 14:03:49
15.4K viewsTadele Tibebu, 11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 14:03:44 ያው የሚጠበቅ ነው። የአብይ አሕመድ አገዛዝ
ስልኬን ጠልፈው መከታተል ጀምረዋል። የእስር ማዘዣም አውጥተዋል። እኔ ብቻ ሳልሆን አጅግ በጣም ብዙ ልጆች የእስር ማዘዣ አውጥተው ማደን ጀምረዋል።
የምታገለው ለዐማራ ህዝብ እስከሆነ ድረስ የሚያስደነግጠኝ ሆነ የሚያስፈራኝ አንዳች ነገር የለም።
15.4K viewsTadele Tibebu, 11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 21:05:32
9.8K viewsTadele Tibebu, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 21:05:07 #ሼር_ፖስት! ይህ የ11 ዓመት ህፃን ትናንት መራዊ ከተማ የአብይ አሕመድ ወታደሮች ተኩሰው ሁለት ቦታ ላይ አቁስለውት ነበር። ህፃኑ አምላክ እንደሻው ይባላል። እናት በደም የጨቆዬ ልጇን ወደ ባህርዳር ፈለገ ህይወት ይዛ መጣች።
ሃኪሞችም ሕይወቱን ለማትረፍ እርብርብ አድርገው ነበር። ነገርግን አንጀቱ ወጥቶ ስለነበር
መታደግ አልቻሉም። ህፃኑ የእናቱን ዐይን እያየ "እናቴ..."እያለ እየቃተተ ጥሏት ሂዷል። እናትም "አለሁልህ ልጄ" እያለች በማልቀስ ለማስታመም ብትሞክርም እቅፏ ላይ አርፏል። ክስተቱ ሕወሓት በደምቢዶሎ አንዲትን እናት ልጇን ገድለው ከሬሳው ላይ አስቀምጠው እንዳስለቀሷት ያለ ነው። እነኚህ እናትም በግፈኞች ልጇን ተነጥቃ ከልጇ ሬሳ አጠገብ አንገቷን ደፍታ አልቅሳለች። ግፈኞችም፤ ከግፈኞች ጋር የተባባራችሁም ለፍርድ የምትቀርቡበት ግዜ ሩቅ አይደለም። የዐማራ እናቶች ዕንባ ከጉራፈርዳ እስከ ማይካድራ፣ ከወለጋ እስከ መራዊ፣ ከባህርዳር እስከ ቆቦ፣ ከወልዲያ እስከ ደብረብርሃን ፈሶ አይቀርም። ትግልን መራራ የሚያደርገው እና እንደ ችቦ የሚያቀጣጥለው እንደዚህ ያለው ልብ የሚነካ ታሪክ ነው።
9.8K viewsTadele Tibebu, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 14:17:47
17.7K viewsTadele Tibebu, 11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 14:17:33 #ሼር_ፖስት! ተቃውሞው በአራቱ ኃያላን ክፍላተ ሀገሮች ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። ለህዝቡ ሰላማዊ ተቃውሞ የአብይ አሕመድ ምላሽ ተኩሶ መግደል ሆኗል። አስካሁን ባለው መረጃ በቆቦ፣ በጃዊ፣ በመራዊ፣ በደጀን፣ በኮምቦልቻ፣ በደብረሲና እና በደብረብርሃን ከ20 በላይ ንጹሀን ዐማሮች በአብይ አሕመድ ወታደሮች ተገድለዋል፤ ሌሎችም ቆስለዋል። አብዛኞች የተገደሉት በአደባባይ ለተቃውሞ በወጡበት ሲሆን፣ በመራዊ እና በደጀን ግን ቤት ለቤት የተፈጸሙ ግድያዎች ናቸው። በትናንትናው ዕለት መራዊ ከተማ አባተ መስፍን የሚባል የ5 ልጆች አባትና ነጋዴ በአገዛዙ ወታደሮች በጥይት ተደብድቦ በግፍ የተገደለው ከቤቱ በር ላይ ነው። በዛሬው ቀን በኮምቦልቻ ለሁለተኛ ቀን በቀጠለው ሰላማዊ ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ10 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። በዛሬው ቀን ሸዋ ደብረሲና ከተማ "ገዛኸኝ" የተባለ ወጣት ፋኖ በአካባቢው ፖሊስ ተገድሏል።

-በዛሬው ቀን ሞጣና ባህርዳር ዓድማ ላይ ናቸው። ኮምቦልቻና መካነ ሠላም ወደ አደባባይ ወጥተዋል። ደብረብርሃን በከተማዋ ዙሪያ ጠባሴ አካባቢ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ነው ያረፈደው። የሞቱ ሰዎች እስካሁን ቁጥራቸው አልታወቀም።

ባጠቃላይ በአራቱ ኃያላን ክፍላተሀገር እስካሁን የነበረው እንቅስቃሴ የመነቃቃት ምዕራፍ (Revival) ነው። ምክንያቱም የአብይ አሕመድ አገዛዝ በዐማራው ላይ እያደረሰ ያለውን የጋራ ጭቆናን ለማሸነፍ የጋራ መነቃቃት (collective consciousness) ሊገነባ ይገባል። እስካሁን በመጣንበት የትግል ምንጣፍ የአብይ አሕመድ አምባገነን አገዛዝ ዐማራን የሚጨቁን፣ የሚገድልና የሚያፈናቅል፣ ብቻ ሳይሆን ከምዕራባውያን ጋር ተባብሮ ከነሃይማኖታዊ ቅርሳችን ሊያጠፋን የተነሳ መሆኑን ሁሉም በጋራ የተስማማበት ሆኗል። ለአንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ የትግሉ ዋና አስኳል ሕዝቡንና ግዛቱን መጠበቅ (making the people and its territory congruent)፣ ከጭቆና ቀንበር ነጻ ለመውጣት፣ የጋራ ሥርዓትን ለመመስረት፣ የጋራ መብቶችና ጥቅሞችን ለማረጋገጥ መሆኑን በአዕምሮ ውስጥ ማስረጽ (imagined community) ከተቻለ ለገቢር እንቅስቃሴው አጋዥ ኃይል ይሆናል።

አሁን ከመነቃቃት ምዕራፍ (Revival) ወደ
ተደራጀ እንቅስቃሴ (collective action) መግባት ተጀምሯል። እንዲህ ያለ እንቅስቃሴ ባለቤት ያለው፣ በስትራቴጂክና በታክቲክ የሚመራ፣ በጠንካራ የውስጥ ትብብር (internal ally) እና በጠንካራ የውጭ ትብብር (external ally) የሚታገዝና ዘርፈ ብዙ አደረጃጀት ኖሮት የሚቀጥል የትግል ስልት ነው።

ከመነቃቃትና ከተደራጀ እንቅስቃሴ በኋላ ሦስተኛው ሥልጣንን የመቆናጠጥ ምዕራፍ (Ascending to Power) ይሆናል። ምክንያቱም ሕወሐትና ኦህዴድ ብልፅግና የራሳቸውን ፍላጎትና ጥቅም ለማራመድ፣ ዐማራውን ለሥቃይ፣ ዝርፊያና ጥቃት ያጋለጡት "ሥልጣን" ላይ ሆነው ነው። ስለዚህ ሥልጣን መጨበጥ ማለት እነዚህን ችግሮች በማስወገድና ከሥልጣን በሚገኘው ጥቅም የህዝባችንን በህይወት የመኖር መብቱን ማስከበር፤ ኢኮኖሚውያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ ማለት ነው።

እናም መነቃቃትና የተደራጀ ትግል ብቻውን ግብ አይደለም። ዐማራ ወደ ሥልጣን ካልመጣ በስተቀር ችግሮቹን በዘላቂነት መፍታት አይችልም። ዐማራ የጎደለው ነገር ቢኖር ሥልጣን ነው። በሥልጣን ማጣት ምክንያት ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጥቅሙን ማስጠበቅ አልቻለም፡፡ እየደረሰበት ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ማስቆም አልቻለም። ምክንያቱም እስከዛሬ የምኒልክን ቤተ መንግሥት እየተፈራረቁ የነገሡበት የትግራይና የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው።

ለምሳሌ፣ ህገ መንግሥቱን ያረቀቁትና ሥልጣን የያዙት ዐማራ ጠል የሆኑት ሕወሓት እና ኦነግ ናቸው።ሁለቱም የምኒልክን ቤተመንግሥት ከተቆጣጠሩ በኋላ ነበር በዐማራው ላይ መልክዓምድራዊ ለውጥ (Demographic Change) የሰሩበት። ዐማራው ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር የነበረውን ማኅበራዊ መተማመን (Social Capital) የሸረሸሩበት። በመጨረሻም ግንባር ፈጥረው ጅምላ ግድያ (Genocide)፣ ሳይንሳዊ ጦርነት (Bioterrorism) እና ትውልድ የማምከን ሥራ የሰሩበት። ይህ ሁሉ የሆነው ዐማራው ከሥልጣን በመገለሉ ምክንያት ነው። ደርግን በፕሬዝዳንትነት የመራው መንግሥቱ ኃይለማርያም ኦሮሞ ነው። ኢሕአዴግን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመራው የትግራዩ መለስ ዜናዊ ነው። አሁን ደግሞ የኦህዴድ ብልፅግናን እየመራው ያለው አብይ አሕመድ የበሻሻ ኦሮሞ ነው።

ስለዚህ የዐማራን ህዝብ ብሎም የኢትዮጵያን ህዝብ መከራና ሰቃይ ለማስተካከል ከተፈለገ ዐማራ ሥልጣንን መጎናጸፍ (ascendance) አለበት። ሥልጣን ከያዘ በኋላ ሥልጣንን ማጠናከር (consolidation)፣ ቅቡልነትን መጎናጸፍ (legitimization) እና ስልጣንን መግራትና ማቆየት (preservation) በቀጣይ የሚመጡ የትግል ምዕራፎች ናቸው። የዐማራ ትግል አሁን ያለበት ቁመና ከመነቃቃት ምዕራፍ አልፎ ከፊል የተደራጀ እንቅስቃሴ (collective action) እንጂ ገና ሙሉ አልሆነም። ከላይ እንደጠቀስኩት ወደ ሥልጣን ለመምጣት የተነቃቃውን የሕዝባችን ማህበራዊ ንቅናቄ (social movement) በተደራጀ መልኩ መምራት ያስፈልጋል። ለዚህ እንቅስቃሴ የአብይ አሕመድ አገዛዝ ምስጢራዊ መዋቅሩን (Deep State) በመጠቀም የኃይል ምላሽ (securitized solution) መስጠቱ አይቀርም። ነገርግን ያለአንዳች መሰዋእትነት የተደፋ የድል አክሊል ስለመኖሩ ሰምተን አናውቅም።
17.5K viewsTadele Tibebu, edited  11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 10:36:27
17.3K viewsTadele Tibebu, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ