Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! ይህ የ11 ዓመት ህፃን ትናንት መራዊ ከተማ የአብይ አሕመድ ወታደሮች ተኩሰው ሁለት | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! ይህ የ11 ዓመት ህፃን ትናንት መራዊ ከተማ የአብይ አሕመድ ወታደሮች ተኩሰው ሁለት ቦታ ላይ አቁስለውት ነበር። ህፃኑ አምላክ እንደሻው ይባላል። እናት በደም የጨቆዬ ልጇን ወደ ባህርዳር ፈለገ ህይወት ይዛ መጣች።
ሃኪሞችም ሕይወቱን ለማትረፍ እርብርብ አድርገው ነበር። ነገርግን አንጀቱ ወጥቶ ስለነበር
መታደግ አልቻሉም። ህፃኑ የእናቱን ዐይን እያየ "እናቴ..."እያለ እየቃተተ ጥሏት ሂዷል። እናትም "አለሁልህ ልጄ" እያለች በማልቀስ ለማስታመም ብትሞክርም እቅፏ ላይ አርፏል። ክስተቱ ሕወሓት በደምቢዶሎ አንዲትን እናት ልጇን ገድለው ከሬሳው ላይ አስቀምጠው እንዳስለቀሷት ያለ ነው። እነኚህ እናትም በግፈኞች ልጇን ተነጥቃ ከልጇ ሬሳ አጠገብ አንገቷን ደፍታ አልቅሳለች። ግፈኞችም፤ ከግፈኞች ጋር የተባባራችሁም ለፍርድ የምትቀርቡበት ግዜ ሩቅ አይደለም። የዐማራ እናቶች ዕንባ ከጉራፈርዳ እስከ ማይካድራ፣ ከወለጋ እስከ መራዊ፣ ከባህርዳር እስከ ቆቦ፣ ከወልዲያ እስከ ደብረብርሃን ፈሶ አይቀርም። ትግልን መራራ የሚያደርገው እና እንደ ችቦ የሚያቀጣጥለው እንደዚህ ያለው ልብ የሚነካ ታሪክ ነው።