Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.80K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-03-25 19:22:12 የዛሬ 5 ዓመት ደብረ ዳሞ ላይ እንዳየሻቸው ያሉ ሴት መነኮሳት ተደፍረዋል ስልሽ ሰውነቴን እየሰቀጠጠኝ ነው።

በመሃል ሜዳ መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ቀበሌ 03 አንዲት የ20 ዓመት ሴት በሦስት የትግራይ ሰዎች የተደፈረችው የ80 ዓመት አባቷን አውጥተው ውጪ ግንድ ላይ አስረው እና የ2 ዓመት ሕፃን ልጇ ፊት ላይ ነው። አስቢው እንግዲህ...አባትሽ አይኑ እያዬ ስትደፈሪ፣ ህፃን ልጅሽ እይኗ እያየና እያለቀሰች ስትደፈሪ? አየሽ ፅጌረዳ ከአንቺ ላይ ያለው ቁስል ከዐማራ ሴቶች ላይ አለ። ህመሙ የሁላችንም ነው። ጦርነቱ የእብሪተኞችና የቁማርተኞች ነው። እነሱ ምንምን አልሆኑም፣ የድሃ ልጆች ግን አለቁ። እነሱ ተደራደሩ የድሃ ልጆች ግን አካለ ጎደሉ ሁነው ቀሩ። ዛሬ አንቺ በሰው ሸክም የምትንቀሳቀሽ አካል ጉዳተኛ ሆነሻል፣ የሕወሓት ልጆች ግን አውሮፓ እየተማሩ ናቸው። አሁንም መፍትሔው በኢትዮጵያ የዘረኝነት ፖለቲካ በህግ እንዲታገድ መታገል ነው። እንደ በርሊን ግንብ አለያይቶ የሚያናክሰንን ሕገመንግሥት ተብዬ ቀዳዶ መጣል ነው። አሁንም በየሚዲያው እየወጡ የሚፎክሩትን ሁላችንም "በቃችሁ!" ማለት ነው። በፅጌረዳና በኢክራም 'ይብቃ!' ማለት አለብን።

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut
11.4K viewsTadele Tibebu, edited  16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 19:22:12 #ሼር_ፖስት ይድረስ ለፅጌረዳ አብርሃ
======================
ፅጌ ደህናነሽ ብዬ እንዳልጀምር ደህና አይደለሽም። ደብረ ዳሞን ተራራ የወጡ እግሮችሽ ተቆርጠው ክራንች ላይ ተቀምጠሽ በመቀሌ ጎዳና "ተረስተናል" ከሚሉት የጦር ጓደተኞች መካከል አየሁሽ። አወ...ደህናማ አይደለሽም፣ ሁላችንም ደህና አይደለንም ፅጌ።

ታስታውሺ እንደሆነ..የዛሬ 5 ዓመት ደብረ ዳሞ ገዳም ነበር የተገናኘነው፣ እንዲያውም ዐፄ ልብነ ድንግል የተቀበረው እዚሁ ገዳም እንደሆነ ነግሬሽ ነበረ።አምባገነኖች በፈጠሩት ጦርነት ውስጥ ተሳትፈሽ እግሮችሽን በማጣትሽ አዝኛለሁ።ፅጌ እንዲህ አለያይተው የሚያቋስሉን ፖለቲከኞች ናቸው።"ጦርነት ባህላዊ ጨዋታ ነው" የሚሉ እብሪተኞች ናቸው።

ዐማራና ትግራይ የሴም ልጆች እንደሆኑ ይታወቃል። ቅድመ አያታችን ሴም ነው። አቺናኔ የሴም የልጅ ልጆች ነን። በአማርኛ "ለሁሉም ጊዜ አለው" ብዬ ብጠይቅሽ በትግርኛ፣ "ንኹሉ ጊዜ አለዎ" ብለሽ እንደምትመልሽልኝ እርግጠኛ ነኝ። በዚህ መካከል ምንም ልዩነት የለም። ቋንቋችን ሴማዊ ፤ የዘር ግንዳችን ከሴም።

አየሽ ፅጌ... ዐማራና ትግሬ እንዲህ ብዙ ሺህ ዓመታት ጒንጒን ማንነት ያላቸው፣ በማይፈታ መልኩ የተጋመዱ ናቸው። በባህል የተሰበጣጠሩ፣ በቋንቋ የተወራረሱ፣ በደም ጥልቀትና በሥጋ ልደት የተሳሰሩ፣ በአንድ እናትና በአንድ አባት ጉያ፤ በአንድ ቤት ውስጥ አብረው ያደጉ ሕዝቦች ናቸው። ነገርግን ሕወሓት ዐማራን ብቻ ነጥሎ "የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት" በማለት ፈረጀው። መለስ ዜናዊ ስለትግራይ ወርቅነቱ ሲመሰክር ዐማራን ግን አከርካሪውን ሰብረው እንደጣሉት በአደባባይ ተናገረ። እንዲህ እያሉ በመካከላችን የሚያለያይ የባቢሎን ግንብ ገነቡ።

የዐፄ ይኩኖ አምላክ አባት ተስፋ ኢየሱስ፤ አያቱ እድም አሰገድ የአክሱም ልዑላን ልጆች መሆናቸው ተዘነጋ። እነ ዐፄ ዘርዓያዕቆብ፣ እነ ዐፄ ዓምደ ፅዮን ንግሥናቸውን የፈፀሙት አክሱም ፅዮን ነበር። ዐፄ ልብነ ድንግል እና ባለቤታቸው እቴጌ ሰብለ ወንጌል የተቀበሩት ደብረ ዳሞ ገዳም ነበር።
ዐማራና ትግሬ ለመጀመሪያ ግዜ በጃንደረባው "ባኮስ" የክርስትና ሃይማኖት የተሰበከላቸው፣ ለመጀመሪያ ግዜ በካህኑ "ሕዝበ ቀድስ" አንድ ላይ የተጠመቁ ሕዝቦች ነበሩ። ገድለ ተክለ ሃይማኖት እንዲህ ይላል፣ "የትግሬና የአምሐራ ሰዎች በሕዝበ ቀድስ ቃል አምነው ፍጹማን ክርስቲያኖች ሆኑ። ደጋጎቹ ነገሥታት አብርሃና አጽብሃ በነገሡበት ዘመን።"

ምን ይሄ ብቻ በአንድ ቤተ መቅደስ አብረው ቀድሰዋል፤ በአንድ ቤተክርስቲያን አብረው አስቀድሰዋል። ዐማሮች አክሱም ፅዮን፣ ትግሬዎች ላሊበላ እየመጡ ተሳልመዋል። በ1708 ዓ.ም ደምቢያ ውስጥ ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን ተሰርታ ስትመረቅ የዐማራና የትግሬ ሰዎች በአንድ ላይ ዘምረዋል። የዐፄ ዮስጦስ ዜና መዋዕል እንዲህ ይላል፣ "....የጥምቀት እለት ታቦተ ልደታን አገቡ ነጋሪት እየተመታ መድፍ እየተተኰሰ በይባቤ በማኅሌት። የትግሬ መኳንንት ወይዛዝርት በአገራቸው ዘፈን እየዘፈኑ። ተከዜ ወዲህ ያለ ዐማሮች በዐማራ ዘፈን እየዘፈኑ"

የቤተ አምሐራዋን ተድባበ ማርያም፣ ጣና ቂርቆስን፣ የቤጌምድሩን ጃን ሚካኤልን፣ የጎጃሞችን መርጡለ ማርያምንና ደብረ ወርቅን የተከሉት አብርሃ ወአጽብሐ ናቸው። በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዋግና በላስታ አካባቢዎች ብልባላ ቂርቆስን፣ ብልባላ ጊዮርጊስን፣ አርባዕቱ እንስሳን እና ሳርዛና ሚካኤልን ያሳነጻቸው ዐፄ ካሌብ ነው። በ862 ዓ.ም. ሐይቅ እስጢፋኖስ የተመሠረተው በአክሱም ንጉሥ ዐፄ ድልነዐድ ነው። ወደ ጣና ሐይቅ በመምጣት የማንዳባን ገዳም የመሠረቱት አቡነ ያሳይ የትግራይ እንደርታ ተወላጅ ናቸው። በጣና አካባቢ መጀመሪያ ካስተማሩት ሰባቱ ከዋከብቶች መካከል አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን ትውልዳቸው ትግራይ አዲ ሀገራይ ነው። በግራኝ የፈራረሰችውን አክሱም ፅዮን መልሶ ያሳነጻት ዐፄ ፋሲል ከጎንደር አክሱም ተጉዞ ነው። በ505 ዓ.ም. የተወለደው ቅዱስ ያሬድ ምልክት የሌለው ድጓ የጻፈው ጣና ቂርቆስ ውስጥ ነው።

.... ግን ምን ያደርጋል በመካከላችን የተዘራብን የሚያካክድ የታሪክ ሐተታ እንጂ እንዲህ ያለው የሚያፋቅር ታሪክ አይደለም። ሕወሓት የትግራይን ሕዝብ ሞቢላይዝ ለማድረግ የሐሰት ታሪክ በመጻፍ (the falsification) እና ታሪክን በማዛባት (manipulation of history) ዐማራውን ነጥሎ ነው የከሰሰው። አንድነትን፣ አብሮነትን ከመስበክ ይልቅ ዘረኝነትን (Racism)፣ እና አውራጃዊነትን (Provincialism) ሲዘራ ነው የኖረው። በግራኝ የተከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስ የትግራዩ አዛዥ ሮቤል እና የጎጃሙ ዐማራ ራስ ወሰን ሰገድ በአንድ ላይ ተዋግተው በአንድ ጉድጓድ ተቀብረው ነበር። ሕወሓት ግን ነጣጥሎ አታኮሰን።

እናም ፅጌ ከተከዜ ወዲህና ወዲያ ማዶ አድርገው የሚያላቅሱን ገዥዎች እንጂ ዐማራና ትግሬ የአንድ ቤተሰብ የሴም ልጆች ናቸው። በጦርነቱ የተጎዳነው ሁለታችንም ነው።
ዛሬም ሳይሆን በፊትም። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴና ደርግ በትግራይ ላይ አደረሱት ከሚባለው በደል በላይ በዐማራው ላይ አድርሰዋል። ዐፄ ኃይለሥላሴ ለጎጃም ዐማራ ችግር ዳቦ ከሰማይ በአውሮፕላን አልጣሉለትም። የወረደው ቦንብ ነው። ደርግ ለጎጃም የብቸና ሕዝብ ተቃውሞ ምላሹ የብቸናን ሕዝብ ከምድረ ገጽ ማጥፋት ነው። በናፓልም እሳት ነው ያቃጠላቸው። ከሃውዜን የበለጠ ሕዝብ በብቸና ተጨፍጭፏል።

በ1966 ድርቅ በትግራይ ላይ ከደረሠው አደጋ በወሎ ያለቀው ህዝብ ይበልጣል.. ፅጌ። የ1965/67'ቱን አሠቃቂ ድርቅ፣ ረሃብና እልቂት በተመለከተ ጆናታን ዲምቢልቢ የተባለው ጋዜጠኛ የተደበቀውን ረሃብ "The hidden Hunger" በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን ፊልም በቴምስ ቴሌቪዥን ላይ በማቅረብ አሰቃቂውን የወሎ ዐማራ ያጽም ምስልና ምጽዋት ሲለምኑ የሚያሳየውን አሳዛኝ ትርኢት ለዓለም ከማሳየቱም በላይ ፊልሙን ሲጀምር "በምዕራብ አፍሪቃ ከብቶች ሲያልቁ በኢትዮጵያ ግን ሰዎች እያለቁ ነው።" በማለት የዓለምን ሕዝብ በየቤቱ ገብቶ ልቡን ሰብሮታል። ይህን ፊልም ብታይው ደም ዕንባ ታለቅሻለሽ። ግን ዐማራ ልዩ ተጠቃሚ ይመስል በጨቋኝነት ተፈረጀ። በተምቤን ቆላ የምትኖር አንዲት የትግራይ እናት እና በመንዝ ተራራ የምትኖር አንዲት የዐማራ እናት ሕይወት ተመሳሳይ ነው። ነገርግን ዐማራ በጨቋኝነት ተፈርጆ ላለፉት 50 ዓመታት ተዘመተበት። የመከራ ዶፍ ወረደበት። ጫካ መንጥሮ፣ ገደል ቆፍሮ በልፋት ድካሙ በሚኖረው ሚስኪን ህዝብ ላይ ከግራ ቀኝ እሳት ተወረወረበት።

....አሁንም በጦርነቱ የተጎዳነው ሁለታችንም ሆኖ ሳለ ሕወሓት የትግራይ ሕዝብ ብቻ እንደተጎዳ ለማስመሰል የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም። ነገርግን ከትግራዊቷ ፅጌረዳ ላይ የደረሰው ቁስል ከዐማራዊቷ ኢክራም ላይ ደርሷል። የአጣዬ ከተማ ነዋሪ የሆነች የ14 ዓመት ታዳጊ ኢክራም በቡድን እየተፈራረቁ ደፍረዋታል። ፅጌረዳ? አንቺ ላይ ያለው የጭን ቁስል ኢክራም ላይ አለ። በዋግኽምራ ዞን በሰቆጣ ወረዳ "ጭላ" ቀበሌ ልትወልድ ሳምንት የቀራትን ነፍሰጡር ሴት ተደፍራ ልጇ ከሆድዋ ላይ እንደሞተ ስነግርሽ በተሰበረ ልብ ነው። ሰሜን ጎንደር ደባርቅ ወረዳ የአስር ቀን አራስ እናትን መሬት ላይ ጥለው ለአራት ከደፈሯት በኋላ አራሱን ጨቅላ "የዐማራ ልጅ አድጎ በኋላ ስለሚወጋን" በማለት ሽንት ቤት እንደጣሉት ስነግርሽ በሃዘኔታ ነው።
11.2K viewsTadele Tibebu, edited  16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 21:40:32
10.4K viewsTadele Tibebu, 18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 21:40:21 የአዲስአበባ ፖሊስ የካህኑን ግድያ ለማስተባበል ሞክረዋል። ይህ ወንጀልን መካድ (Denial) ይባላል። ህዝብ ይመራሉ፣ ፍትሕ ርትዕ ያሰፍናሉ የተባሉ የፀጥታ ተቋማት እነዲህ በአደባባይ ህዝቡን ለመዋሸት ሲሞክሩ አለማፈራቸው ይገርማል። ማንስ ያምነናል ብለው ነው? ምንም ቢሆን እንደ ጲላጦስ "ከደሙ ንፁህ ነኝ" ብለው 30 ጊዜ እጃቸውን ቢታጠቡ ከደሙ ሊነፁ አይችሉም።
10.4K viewsTadele Tibebu, 18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 22:14:12
4.3K viewsTadele Tibebu, 19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 22:14:05 በዐማራ ላይ ዘግናኝ ሆሎካስት የፈጸመውን ኢንተርሃምዌ ሕወሓትን ከሽብርተኝነት መዝገብ ፍቀህ፣ ”ዐማራን አከርካሪውን ሰብረነዋል” ያለውን አቦይ ስብሀት ከእስር ለቀህ ሲያበቃ ዘመነ ካሴን እስርቤት የምታቆይበት ምንም ምክንያት የለም። "ሀጫሉን የገደለው ነ*ፍ*ጠ*ኛ ነው" በማስባል ዐማሮችን ያስጨፈጨፉትን እነጃዋርንና በቀለ ገርባ በነፃ አሰናብተህ ሲያበቃ፣ ዘመነ ካሴን አስረህ የምታቆይበት የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ምክንያት የለም። ዐማራ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆኖ ይሄን ዘመን እንዲሻገር ከተፈገ ዘመነ ካሴን ፍቱት። በየእስር ቤቱ የታጎሩ ፋኖዎችና ልዩ ኃይሎችን ልቀቋቸው።
4.3K viewsTadele Tibebu, edited  19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 13:12:17
12.7K viewsTadele Tibebu, 10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 13:11:55 #ሼር_ፖስት! ይደንቃል ...ሕወሓት ከሽብርተኝነት መሰረዙን ሰማን... ሕወሓት 7,003 የሚሆኑ ዐማሮች በጦርነቱ ምንም አይነት ተሳትፎ ሳይኖራቸው ህጻናት፣ ነፍሰጡሮች፣ አጥቢ እናቶች፣ አቅመደካሞችን፣ አረጋዊያንን፣ የሀይማኖት አባቶችንና አካል ጉዳተኞችን መስማት የተሳናቸውን፣ ማየት የተሳናቸውን፣ የመንቀሳቀስ እክል ያለባቸውን፣ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ሳይቀር ያለርህራሄ ጨፍጭፏል ግን ከደሙ ነፃ ነው ተብሏል።

ሕወሓት፣ 18,496 ዐማሮች ሴቶች፣ ህጻናት፣ እመጫት እናቶች፣ የአካል ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካማ ሽማግሌዎች ብሎም የሀይማኖት አባቶችን ጭምር ምግብ እና ገንዘብ አምጡ፤ ትጥቅ ደብቃቹሀል፤ መከላከያን ሸሽጋቹሀል፤ የፋኖ፣ የሚኒሻና የአመራሮችን ቤት ጠቁሙ በማለት በእርግጫና በመሳሪያ ሰደፍት ምት፣ የፊጥኝ አስረው በጩቤ በመተልተል፣ ጥይት ተኩሶ በማቁሰል፣ አስሮ በመጎተት፣ "ዐማራ፣ ዐማራ ምንድነው? ዐማራ አ*ህ*ያ ነው?" እያለ በተደጋጋሚ ባደረሰባቸው ጥቃት ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ገና ቁስላቸው ሳይደርቅ ሕወሓት
ከሽብርተኝነት መዝገብ ተሰርዟል።

-በሕወሓት፣ 1968 ዐማሮች.. ህጻናት፣ እመጫት እናቶች እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች የትዳር አጋር እንዲሁም መነኩሴዎች ሳይቀር ተገደው ተደፍረዋል፣ ከነዚህ መካከል 29'ኙ ወንዶች ግብረሰዶም ተፈጽሞባቸዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በምርመራው እንዳረጋገጠው፣ ጭና ቀበሌ አንድን አባት ከገደሉ በኋላ የ7 ዓመት ሕፃን ልጃቸውንም “ይህ አድጎ ነው የሚወጋን" ብለው በእናቱ ፊት በጥይት ተኩሰው ገድለውታል። ሕወሓት ግን ሽብርተኛ አይደለም ተብሏል።

-በሸዋሮቢት ከተማ የቀበሌ 02 ነዋሪ የሆኑ ዓለም በቃኝ ብለው ሥጋቸውን እና ነፍሳቸውን ለፈጣሪ የሰጡ የ85 ዓመት መነኩሴ በተኙበት በውድቅት ሌሊት አንድ የትግሬ ወ*ን*በ*ዴ በር ሰብሮ ከገባ በኋላ በጥፊ መታት እማሆይ መሬት ላይ ሲወድቁ ደግሞ ይህ ሰው መሳይ የትግሬ አ*ው*ሬ ጭንቅላቸውንና ሆዳቸውን ደጋግሞ እረገጣቸው። በዚህ አላበቃም አስገድዶ ደፈራቸው፤ ምንኩስናቸውን አረከሰው። እማሆይ ከተደፈሩ በኋላ በማግሥቱ ሙሉ ቀን በማህጸናቸው ደም ሲፈሳቸው ዋለ። እኚህ እናት ዛሬ የምንኩስና ቆባቸውን አውልቀው ዘመድ እንደሞተበት ሰው ጥቁር ማቅ ለብሰው የሞት ቀናቸውን የሚጠባበቁ አዛውንት ሆነዋል። ሕወሓት ግን ከሽብርተኝነት ተሰርዟል።

በሕወሓት በተወረሩ በስምንቱም ዞኖች ማለትም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ወሎ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በዋግኽምራ ብሔረሰብ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በሰሜን ጎንደር፣ በደቡብ ጎንደር፣ በጥቅሉ፦

-594,943 የግለሰቦች ቁስ በሳር፣ በቆርቆርና በብልኬት የተሰሩ ቤቶችን ጨምሮ አውድሟል፤ ዘርፏል።

- 1156 ቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሦስት ዩኒቪርሲቲዎች ወልዲያ፣ ወሎና መቅደላ አምባ
እና 55 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን ጨምሮ አውድሟል፤ ዘርፏል።

-በሁሉም የተወረሩ አካባቢዎች 184 የሚደርሱ ኢንዱስትሪዎች ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን፣ 666 የሚሆኑት በከፊል ወድመዋል። በጥቅሉ 824 የሚደርሱ ብረታብረትና እንጨት፣ የጨርቃጨርቅና የቆዳ፣ የአግሮ ኢንዱስትሪና ኬሚካልና የግንባታ ግብዓት ኢንዱስሪዎች በሕወሓት ሙሉ በሙሉና በከፊል ወድመዋል።

- በኢንቨስትመንት ዘርፎች በኢንዱስትሪ፣ ንግድ፣ ግብርና፣ ማህበራዊ እና ሌሎች 1775 ኢንቨስትመንት አውድሟል፤ ዘርፏል።

- በቱሪዝም ዘርፍ ሕወሓት 868 ቅርሶች ላይ ውድመት አድርሷል፤ ከዚህም ውስጥ 457 ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ሲሆኑ፣ 190 የክርስትናና የእስልምና እምነት ተቋማትን ዘርፏል፣ አቃጥሏል፣ አውድሟል። ዐፄ ምኒልክ ከጅቡቲ እና ከፈረንሳይ መንግስታት ጋር ግንኙነት ያደረጉበት የስልክ ቀፎ፣ በአድዋ ጦርነት ጊዜ ያገለገሉ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች፣ በ1890 ከፈረንሳይ መንግሥት የተበረከተው መድፍ፣ በኢትዮ-ጥልያን ጦርነት ጊዜ በኢትዮጵያዊያን የተማረከው የአየር መቃወሚያ፣ ዳግማዊ ምኒልክ አድዋ ላይ የተዋጉበት የጦር ጎራዴ ከደሴ ሙዝየም ሰርቆ ወስዷል።

-በስምንቱም ዞኖች 653 የተለያዩ የጤና ተቋማትን 297 ጤና ኬላዎችን፣ 272 ጤና ጣቢያዎችን፣ 30 የመጀመሪያ እና ጠቅላላ ሆስፒታሎችን፣ አንድ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ 25 የግል ክሊኒኮችንና 21 ፋርማሲዎችን፣ 4 የደም ባንኮችን፣ አንድ የኦክስጅን ማምረቻ፣ አንድ የጤና ተቋም፣ በክልሉ ብቸኛ የሆውን የዐማራ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የደሴ ቅርንጫፍ ዘርፏል፤ አውድሟል።

- በ8 ዞኖች 37,516 እንስሳቶች በጥይት ገድሏል፣ 174,708 ዘርፎ ወስዷል፣ አርዶ የበላቸውና ትራፊያቸውን ወደ ሜዳ ለውሻ ለአራዊት የጣላቸው 92,944 ሲሆን፣ በጥቅሉ 305,168 የእንስሳት ቁጥር አውድሟል።

በጥቅሉ ሕወሓት በቤተሰብ ጥሪት፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት፣ የግል ድርጅቶች፣ እንዱሁም የመሰረተልማት አውታሮች ላይ ባደረሰው መጠነ ሰፊ ጉዳት በጥቅሉ ሲተመን 291,816,377,952.78 (ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ አስራ ስድስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ሦስት ብር) ነው። ግን ከሽብርተኝነት ተሰርዟል።

ወዳጄ...አየህ አይደል ኢትዮጵያ በዐማራ ኪሳራ የቆመች ሀገር ናት። ዐማራን በጨቋኝነት የፈረጀው ህገመንግስት እንዲቀየር 5 ዓመት ሙሉ ጠይቀህ ምላሽ የሰጠህ የለም።ከጉራፈርዳ እስከ ማይካድራ ለፈሰሰው የዐማራ የደም ተጠያቂ የለም።
12.2K viewsTadele Tibebu, edited  10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 19:35:02
9.5K viewsTadele Tibebu, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 19:34:49 በጣም አስደንጋጭ ነው። ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር ማረፋቸውን ሰማሁ። ብፅዕነታቸው ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አንብሮተ ዕድ ከሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ነበሩ። ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ነበሩ። ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል።

በረከታቸው ይደርብን።
9.5K viewsTadele Tibebu, 16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ