Get Mystery Box with random crypto!

በዐማራ ላይ ዘግናኝ ሆሎካስት የፈጸመውን ኢንተርሃምዌ ሕወሓትን ከሽብርተኝነት መዝገብ ፍቀህ፣ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

በዐማራ ላይ ዘግናኝ ሆሎካስት የፈጸመውን ኢንተርሃምዌ ሕወሓትን ከሽብርተኝነት መዝገብ ፍቀህ፣ ”ዐማራን አከርካሪውን ሰብረነዋል” ያለውን አቦይ ስብሀት ከእስር ለቀህ ሲያበቃ ዘመነ ካሴን እስርቤት የምታቆይበት ምንም ምክንያት የለም። "ሀጫሉን የገደለው ነ*ፍ*ጠ*ኛ ነው" በማስባል ዐማሮችን ያስጨፈጨፉትን እነጃዋርንና በቀለ ገርባ በነፃ አሰናብተህ ሲያበቃ፣ ዘመነ ካሴን አስረህ የምታቆይበት የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ምክንያት የለም። ዐማራ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆኖ ይሄን ዘመን እንዲሻገር ከተፈገ ዘመነ ካሴን ፍቱት። በየእስር ቤቱ የታጎሩ ፋኖዎችና ልዩ ኃይሎችን ልቀቋቸው።