Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.80K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-20 07:50:30
16.3K viewsTadele Tibebu, 04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 07:50:20
15.9K viewsTadele Tibebu, 04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 07:49:58 ገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል በጣም ይደንቀኛል። በፍፁም አምኖ የሄደ ሰው ድኖ ይመለሳል፣ እኔ ራሴ 'ሳይነስ' እያስቸገረኝ ለዓመታት ቆይቶ ነበር። እንደ መፍትሄ የምወስደው የእስፖርት እንቅስቃሴና 'አልመታሚን' የሚባል መድሀኒትን ነበር። አንድ ቀን የሆነች ልጅ "ታዴ እኔን የተሻለኝ አቡነ ሐራ ድንግል ፀበል ተጠምቄ ነው ሂድና ተጠመቅ" አለችኝ። ከዛም ሄድኩኝ። ፀበሉን ጠጣሁ፣ እምነቱን ተቀባሁ። እግዚአብሔር ይመስገን ሳይነስና እኔ ከተለያዬን አንድ አመት አለፈኝ። የዛሬ 2 ወር አካባቢ አንድ ልማት ባንክ የሚሰራ ጓደኛዬ ምሳ ልንበላ ተቀጣጥረን ልክ እንደኔ እንደበፊቱ አይኑን እያሸው አየሁት። ምድነው ስለው "ሳይነስ አሰቃይቶ ሊገለኝ ነው" አለኝ። እንኳን መጥፎ ሽታ ከቤት ወጥ እየተሰራ ሲቸተኝ ይነሳብኛል፣ ሽቶ ስቀባ ከላይ ከላይ ያስነጥሰኛል፣ አይኔን ስለሚበላኝ እኔም ስለማሸው እንደምታየው ጠቁሯል፣ ወደጆሮ አልፎ ያሳክከኛል በጣም ነው የተቸገርኩት" አለኝ። እኔም ፈገግ ብዬ በፍፁም እምነት አቡነ ሐራ ድንግል ሂድና እምነቱን ቀባው ፀበሉን ጠጣ አልኩት። በሳምንቱ ሄደ። በወሩ "ታዴ ላገኝህ እፈልጋለሁ" ብሎ አገኘኝ። ከዛ ሳቅ...ሳቅ እያለ "ዳንኩኝ እኮ" አለኝ። "አንተ እንዳልከኝ አደረግሁ፣ ፀበሉን ጠጣሁ፣ እምነቱን ተቀባሁ በሳምንቱ ድራሹ ጠፋ። አሁን ምንም ቢሸተኝ አይነሳብኝም። ወር ሆነኝ" አለኝ። እኔም እንደሚፈወስ እርግጠኛ ነበርኩ። ወደዚህ ያመጣሁት የማታውቁ እንድታውቁ፣ የሰማችሁ እንድታሰሙ፣ በህመም የሚሰቃዩትን እንድትነግሯቸው ነው።

አቡነ ሐራ ድንግል ገዳም በፍፁም ልቡ አምኖ ሄዶ ሳይድን የተመለሰ ሰው አላውቅም። በ2004 ዓ.ም. ከ11 ዓመት በላይ ዓይነስውር ዲዳ የነበረ ሰው ዓይኑ እንደበራለት፣ አንደበቱ እንደተከፈተለት አውቃለሁ። በወቅቱ መነጋገሪያ ሆኖ መጽሔትና ጋዜጦች የሰውየውን ምስል ይዘው ወጥተው ነበር። ፎቶውን ከስር አስቀምጬዋለሁ።

አቡነ ሐራ ድንግል ገዳም ከባህር ዳር ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ላጉና ቀበሌ ይገኛል። ገዳሙ የተመሰረተው በ1574 ዓ.ም በፃድቁ በአቡነ ሐራ ድንግል ነው። በቦታውም ፃድቁ አቡነ ሐራ ለ49 አመታት ያህል ሲፀልዩበት ኑረዋል፡፡ በ1626 ዓ.ም በዐፄ ሱስኒዮስ ዘመነ መንግስት የኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በዐፄ ፋሲል እና በፃድቅ በአቡነ ሐራ በቦታው ላይ ተተክላለች፡፡ በትግራዩ ዐፄ ዮሐንስ አራተኛም አቡነ ሐራ ድንግል መቃብር ላይ ለፃድቁ ለአቡነ ሐራ ድንግል መታሰቢያ ሲባል የራሳቸው የፃድቁ ቤተ ክርስቲያን ተመስርቷል፡፡ ንጉሱ ዐፄ ዮሐንስ በራሳቸው ላይ ነቀርሳ ወጦባቸው ሲታመሙ በአካባቢው የሚፈወስ ቦታ አለ ተብለው ሰለተነገሩ ቦታውን በማፈላለግ መጥተው በፀበሉ ተጠምቀው በእምነቱ ቢቀቡ ሰለዳኑ የፃድቁን ቤተክርስቲያን እንደ አሰሩ ይነገራል፡፡

በዚህ ገዳም በየአመቱ ጥር 11 ቀን የአቡነ ሐራ ድንግልን የእረፍት ቀን፣ የካቲት 16 ቀን የእመቤታችን ማርያምን የቃል ኪዳን ቀን፣ ግንቦት 11 ቀን የአቡነ ሐራ ፀበል ተባርኮ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት ቀንን እና ጥቅምት 19 ቀን የፃድቁ አቡነ ሐራን የልደታ ቀን ምክንያት በማድረግ ብዙ ህዝብ ከተለያየ አካባቢ ይሰበሰባል፡፡

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut
14.9K viewsTadele Tibebu, edited  04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 19:52:23 ዐማራ ድንቅ ምድር፣ ሰሜን ተራራ፣ ላሊበላ፣ ፋሲል፣ ጮቄ ተራራ፣ ሙሉ ኢኮሎጂ፣ ግዮን፣..ቱባ ባህል..ድንቅ ህዝብ!
11.4K viewsTadele Tibebu, 16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 19:15:42
12.2K viewsTadele Tibebu, 16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 19:15:31 የዐማራ ህዝብ ከልጆቹ የሚፈልገው ኑሮውን የሚኖሩለት፣ ችግሩን የሚያዳምጥለት፣ ፍኖተ-መርሁን የሚቀርፅለት፣ ከድህነት ይወጣ ዘንድ የሚያግዙትን ነው። የዐማራ ህዝብ የሚፈልገው እንደ ታምራት ላይኔ የሚሰድበውን፣ እንደ መላኩ ተፈራ የሚጨፈጭውን፣ እንደ ዋለልኝ መኮነን የሚከሰውን፣ እንደ ብአዴን ከሕወሓት ጉያ ተሸሽጎ የሚጨቁነውን፣ የሚዘርፈውንና የሚያዘርፈውን አይደለም።

የዐማራ ህዝብ የሚፈልገው፤ ድህነቱን የሚያስወግድ፣ ከአለበት ምጥ አውጥቶ እንደ ሙሴ የሚያሻግረውን ነው። ዐማራ የሚፈልገው እንደ ፕሮፌሰር አሥራት ክብሩን ለማስጠበቅ የሚታገሉትን፣ ትምህርት ቤት የሚገነቡለትን፣ መንገድ የሚሰሩለትን፣ ክሊኒክ የሚያንፁለትን ዐማሮችን ነው። በትግል ስም ገንዘቡን እየገፈፉ ቦርጫቸውን የሚያሰፉትን፤ ሀብት ንብረቱን ዘርፈው የሚያሸሹትን፣ ተሳድበው ለተሳዳቢ አሳልፈው የሚሰጡትን፣ ተሸማቀው የሚያሸማቅቁትን ዐማሮች አይደለም የሚሻው።

ዐማራ የሚፈልገው ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ህይወቱ
ሲያልፍ፣ መዐሕድን ወደ መኢአድ እንደቀየረው ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል ያሉ ከሃዲዎች ሳይሆን፣ መዐሕድን አጠናክሮ ሊያስቀጥል የሚችል ፕሮፌሰር ነው።

ዐማራ የሚፈልገው ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ እያለ በጎጥ የሚከፋፍለው ሳይሆን፣ እንደ ደጃዝማች ፀሐዩ ዕንቁ ሥላሴ "የዐማራ አንገቱ አንድ ነው" በማለት አንድነቱን የሚያጠናክርለትን ነው። ዐማራን ለመበተን የትግሬው ስሁል ሚካኤል ዘመነ መሳፍንትን መርቆ ሲከፍት፣ ስሁል የበተነውን ሀገር መልሶ ለመሰብሰብ መሰዋእትነት እንደከፈለው ዐፄ ቴዎድሮስ ያለ ጀግና እንጂ የሚፈለገው እንደ ዘመነ መሳፍንት በጎጥ ከፋፍሎ የሚያናክስ ለዐማራ አያስፈልገውም። አብን ሲያጠፋ አርማው ላይ እንዳለው ንስር አድሶ ህይወት የሚዘራ ሰው እንጂ የጠፋው ሲሳደብ የሚውል አላጣንም። አሥራት ቴሌቪዥንን የሚያስቀጥል እንጂ አሥራትን አክስሞ የሚፎልል ሰው አላጣንም።

የዐማራ ህዝብ የዝነኛ ችግር የለበትም። ዝነኞች'ማ ሞልተውታል። በጥሊያን ጎዳና ቪቫ ምኒልክ፣ ቪቫ ጣይቱ የተባለላቸው ነገሥታቶች፣ እንደ ዶክተር መላኩ በያን ያሉ ፓን አፍሪካኒስቶች፣ እንደ አበበ ደምሴ ያሉ ዝነኛ ሩዋጮች፣ እንደ አክሊሉ ሀብተወልድ ያሉ የሊግ ኦፍ ኔሽን ተሟጋቾች፣ እንደ ሙሉጌታ ተስፋዬ ያሉ ባለቅኔዎች፣ እንደ ሀዲድ አለማየሁ ያሉ ብዕረኞች፣ እንደ ራስ አባተ ቧያለው ያሉ አነጣጣሪ መድፈኞች፣ እንደ ፊታውራሪ ገበየሁ ተክሌ ያሉ ምሽግ ሰባሪዎች፣ እንደ ፊታውራሪ ገብርዬ ያሉ ታማኞች፣ እንደ በላይ ዘለቀ ያሉ ጥሊያንን ያርበደበዱ አርበኞች፣ አንቱ የተባሉ ፕሮፈሰሮች፣ ባለፀጋዎች ሞልተውታል። እነዚህ ሁሉ ለኢትዮጵያ መልካም ሥራ ሰርተው ያለፉ ናቸው። ሊከበሩ ይገባል። አሁን በዚሁ ወቅት የሚያስፈልጉን ደግሞ የዐማራ ህዝብ ጥያቄ ሲነሳ ስለኢትዮጵያዊነት እና ስለአለማቀፋዊነት እየደሰኮሩ ራሳቸውን የሚያታልሉ ዐማሮች ሳይሆኑ፣ በቀጥታ እንደ ፕሮፌሰር አሥራት ህዝባቸውን ለመታደግ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚደርጉ ፕሮፌሰሮች ናቸው።
12.0K viewsTadele Tibebu, edited  16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 07:51:40
3.9K viewsTadele Tibebu, 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 07:51:34 "...ወደ ንባብና ወደ እውቀት ካልመጣህ...እየተነሳህና እየፎከርህ ሦስት አውርድ አራት አውርድ እየዘፈንህ ምትሻገረው ዘመን የለም ወደፊት። እመ አምላክን..እመ አምላክን..ከልቤ ነው ምናገረው ለመቀለድ አይደለም። ይሄን ዘመን የምንሻገረው በእውቀት ብቻ ነው። የተደገሰልን በጣም ብዙና ሰፊ ነው። ጠላቶቻችን ደግሞ ዝምብለው በጀልነት አልመጡም። በእውቀት ነው የመጡት። በኢንቨስትመንት ነው የመጡት። በተደራጀ መንገድ ነው የመጡት። እንጂ ዝምብሎ 'ጉድ.!ጉድ.! ኢትዮጵያ እንደዚህ ሆነች' እያልህ ነው የምትቀረው ልንገርህ። መውጣት የምንችለው በሥርዓት፣ በዲስፕሊን ብቻ ነው። አትንዘላዘሉ። አያምርባችሁም።
ፉከራው ልክ ይኑረው። ቀረርቶው ልክ ይኑረው። መፎክር ያለብህ አሁን ቴክኖሎጂ invite ማድረግ ስትችል ነው። መፎርና እርፍ አዋደህ አሁንም ትፎክራለህ እንዴ..? ነውር አይደለም እንዴ በ21ኛው ክፍለ ዘመን"

"እናም በዚህ ዘመን መፎከር ከአለብን፣ መዝመት ከአለብን በድንቁርና ላይ ነው። መሻገርና በዘላቂነት ከችግር መላቀቅ ከአለብን ወደ እውቀት ነው መሄደ ያለብን።" ይሄን የተናገረው ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ነው።

የዲያቆንን ሀሳብ እኔም የምጋራው ነው። ጠላት የመጣው በእውቀትና በኢንቨስትመንት ነው። እጅግ በጣም ተራቀው ነው የመጡት። እኛ አዳነች አቤቤን በፎቶ ሸብ እንሳደባለን፣ እናላግጣለን፣ እናቅራራለን፣.... እሷ ግን በእቅዳቸው መሠረት መሬት ላይ ሥራውን እየሰራች ነው። ዶክተር አብይ አሕመድን በስድብ ስናብጠለጥል እንውላለን እሱ በኢትዮጵያዊነት ስም ተደብቆ ሰርዶ የነካ ሥራውን እያጣደፈው ነው። ወደኛ ስንመጣ ፉከራና ቀረርቶ ይበዛል። ስትራቴጂካና ታክቲክ ነድፎ የሚንቀሳቀስ ሳይሆን ያለው ጥርሱን እየነከሰ "ቆይ ጠብቅ" የሚል ነው ያለው። ስለዚህ ዛቻውንም፣ ቀረርቶውንም ቀነስ አድርገን በእውቀት ላይ የተመሠረተ ተሻጋሪ ሥራ ካልሰራን በስተቀር መጪው ግዜ ከአሁኑ የባሰ እንደሚሆን ነብይ መሆን አይጠይቅም።

አሁን የፖለቲካ መድረኩን እውቀት ያላቸው ሰዎች ሊረከቡት ይገባል። ዝምብሎ ያለ እውቀት እንደ ቁራ ሲጮኽ የሚውለው ፖለቲከኛና አክቲቪስት ለግዜው ዞር ብሎ ቢቆይ ለዐማራ ህዝብ ትልቅ ውለታ መዋል ነው። እንደ ህፃን ከረሜላ ፖለቲካውን የሚጨማለቁበት ሰዎች ለግዜው ገለል ተደርገው
አዋቂዎች፣ ስትራቴጂስቶች፣ የመዳረሻችን ፍኖተ-መርሁ መቅረፅ የሚችሉ፣ ዛሬን ሳይሆን ነገን ታሳቢ ያደረገ ዘላቂ ሥራ ሊሰሩ የሚችሉ አቅም ያላቸው ሰዎች ወደፊት መምጣት አለባቸው።

ምሁራን ስል ብዙ ዲግሪ ያላቸውን እያልኩኝ አይደለም፣ አዋቂዎችን ነው። ብዙ ዲግሪ ኖሮት በድንቁርና የሚኖረው ብዙ ነው። እንደገና ዲግሪም ኖሯቸው የተደበቁ አዋቂዎች አሉ። የሚፈለጉት እነዚህ ናቸው። በነገራችን ላይበዚህ ጉዳይ ባለፈው በአማራ ቴሌቪዥን ዶክተር ዓለማየሁ ልክ እንደ ዲያቆን ብርሃኑ አድማሱ የተናገረው ትኩረቴን ስቦታል።
እንዲህ ነበር ያለው፣

"...በነገራችን ላይ ማህይምነትና ድቁርና ሁለቱ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ማህይም የሚል የትምህርት እድል ያላገኘ ነው። ድንቁርና ግን የትምህርት እድልም አግኝቶ በማህይምነት ግርሻ የተጠቃው ነው። ፈረንጆች ምን ይላሉ arogance (እብሪተኝነት) Ignorance (አለማወቅን) ያመጣል። arogance እና Ignorance ይመጋገባሉ። ማህይምነት ሲያገረሽብህ እብሪተኛ ትሆናለህ፤ እብሪተኛ ስትሆን ደግሞ የበለጠ ማህይምነት ያገረሽብሃል። እናም ብዙዎቻችን በዲግሪያችን ጀርባ በድቁርና ነው የምንኖረው። ሰውም እንዳይመክረን ዲግሪ አላቸው ይባላል። በእድርም ስትሄድ ዶክተር ይናገር ነው የሚባለው። ግን ሰውየው መሃይምነት ውስጥ ነው ያለው።.... እና ምንድነው እየሆነ ያለው ብላችሁ ያያችሁት እንደሆነ...መደማመጥ የሌለው፣ መነጋገር የሌለበት፣ ማንተማመነው፣ ለችግሮቻችን መፍትሔ ማናገኘው የምሁር ቁጥር እንጂ የአዋቂ ቁጥር ስለሌለ ነው። ለምን ያላችሁ እንደሆነ አብዛኞቻችን በመሃይምነት ግርሻ ውስጥ ስላለን ነው። የዲግሪ ፎቶ በየቤቱ ስትሄዱ ግድግዳ ላይ ታያላችሁ። በትክክል ያ የሚያሳየው ሰውዬው በማህይምነት መኖሩን ነው። ምክንያቱም ማረጋገጫው ያ ብቻ ነው። ሌላ ምን ያሳያል? ምን እናሳያለን ሌላ?...."

ስለዚህ ወደ አማራ ፖለቲካ አዋቂዎች ካልመጡ በስተቀር በእውቀትና በኢንቨስትመንት ተደራጅተው የመጡ ጠላቶች በስትራቴጂና በታክቲክ በድቁርና ግርሻ የሚኖሩትን አያሞኙ መሄዳቸውን ይቀጥላሉ.....
3.9K viewsTadele Tibebu, edited  04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 19:05:25
11.6K viewsTadele Tibebu, 16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 19:05:22 በነገራችን ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማለት" አብይ አሕመድ ቀሚስ ለብሶ" ማለት ናት። ዮዲት ጉዲት አዳነች አቤቤ
ዛሬ ሪፖርት ያደረገችው በዐማሮች ላይ ሂትለራዊ ጄኖሳይድ እንዲፈጸም ግልፅ ጥሪ ነው። የጄኖሳይድ ዋች ፕሬዝደንት ግሬገሪ ስታንተን ከአስቀመጣቸው 8 የጄኖሳይድ ደረጃዎች መካከል፣ መከፋፈል (Classification)፣ ስያሜ መስጠት (symbolization) እና የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ሰለባ ማድረግ (Polarization) ይገኙበታል። ዮዲት ጉዲት አዳነች አበቤ ዛሬ ሪፖርት ያደረገችው እነዚህን መስፈርቶች ሙሉ ለሙሉ የሚያሟላና ለቀጣዩ ጅምላ ግድያ (Genocide) የሚያመቻች ነው

አንድን ማኅበረሰብ አስቀድሞ፣ “ከአንዳንድ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ከፍተኛ ፍልሰት መንግስትን በመጣል በኃይል ስልጣን ለመቆጣጠር ያለመ ነው” የሚል
አግላይ ስያሜ መስጠት ያን ማኅበረሰብ ለማፈን፣ ለመመንጠርና (ethninc cleansing) ወደ ጅምላ የዘር ፍጅት (genocide) ለማምራት ሆን ተብሎ የተሰራጨ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ነው።

ይህን ዐማራውን ነጥለው የፈጠራና አፍራሽ አጀንዳ ማድረግ፣ የሳይኮሎጂ ጦርነት፣ የጥላቻ ጦርነት፣ መልካም ስሙን የማጠልሸት ጦርነት፣ ብዥታን የመፍጠር ጦርነት ማንም በዝምታ ማየት የለበትም። አዳነች አቤቤ በግልፅ የሩዋንዳውን የዘር ፍጀት አነሣስቶ እንዳስፈፀመው አርቲኤልኤም (RTLM) በዐማራ ሕዝብ ላይ ግልፅ የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋ ቅስቀሳ አድርጋለች።
12.0K viewsTadele Tibebu, 16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ