Get Mystery Box with random crypto!

'...ወደ ንባብና ወደ እውቀት ካልመጣህ...እየተነሳህና እየፎከርህ ሦስት አውርድ አራት አውርድ እ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

"...ወደ ንባብና ወደ እውቀት ካልመጣህ...እየተነሳህና እየፎከርህ ሦስት አውርድ አራት አውርድ እየዘፈንህ ምትሻገረው ዘመን የለም ወደፊት። እመ አምላክን..እመ አምላክን..ከልቤ ነው ምናገረው ለመቀለድ አይደለም። ይሄን ዘመን የምንሻገረው በእውቀት ብቻ ነው። የተደገሰልን በጣም ብዙና ሰፊ ነው። ጠላቶቻችን ደግሞ ዝምብለው በጀልነት አልመጡም። በእውቀት ነው የመጡት። በኢንቨስትመንት ነው የመጡት። በተደራጀ መንገድ ነው የመጡት። እንጂ ዝምብሎ 'ጉድ.!ጉድ.! ኢትዮጵያ እንደዚህ ሆነች' እያልህ ነው የምትቀረው ልንገርህ። መውጣት የምንችለው በሥርዓት፣ በዲስፕሊን ብቻ ነው። አትንዘላዘሉ። አያምርባችሁም።
ፉከራው ልክ ይኑረው። ቀረርቶው ልክ ይኑረው። መፎክር ያለብህ አሁን ቴክኖሎጂ invite ማድረግ ስትችል ነው። መፎርና እርፍ አዋደህ አሁንም ትፎክራለህ እንዴ..? ነውር አይደለም እንዴ በ21ኛው ክፍለ ዘመን"

"እናም በዚህ ዘመን መፎከር ከአለብን፣ መዝመት ከአለብን በድንቁርና ላይ ነው። መሻገርና በዘላቂነት ከችግር መላቀቅ ከአለብን ወደ እውቀት ነው መሄደ ያለብን።" ይሄን የተናገረው ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ነው።

የዲያቆንን ሀሳብ እኔም የምጋራው ነው። ጠላት የመጣው በእውቀትና በኢንቨስትመንት ነው። እጅግ በጣም ተራቀው ነው የመጡት። እኛ አዳነች አቤቤን በፎቶ ሸብ እንሳደባለን፣ እናላግጣለን፣ እናቅራራለን፣.... እሷ ግን በእቅዳቸው መሠረት መሬት ላይ ሥራውን እየሰራች ነው። ዶክተር አብይ አሕመድን በስድብ ስናብጠለጥል እንውላለን እሱ በኢትዮጵያዊነት ስም ተደብቆ ሰርዶ የነካ ሥራውን እያጣደፈው ነው። ወደኛ ስንመጣ ፉከራና ቀረርቶ ይበዛል። ስትራቴጂካና ታክቲክ ነድፎ የሚንቀሳቀስ ሳይሆን ያለው ጥርሱን እየነከሰ "ቆይ ጠብቅ" የሚል ነው ያለው። ስለዚህ ዛቻውንም፣ ቀረርቶውንም ቀነስ አድርገን በእውቀት ላይ የተመሠረተ ተሻጋሪ ሥራ ካልሰራን በስተቀር መጪው ግዜ ከአሁኑ የባሰ እንደሚሆን ነብይ መሆን አይጠይቅም።

አሁን የፖለቲካ መድረኩን እውቀት ያላቸው ሰዎች ሊረከቡት ይገባል። ዝምብሎ ያለ እውቀት እንደ ቁራ ሲጮኽ የሚውለው ፖለቲከኛና አክቲቪስት ለግዜው ዞር ብሎ ቢቆይ ለዐማራ ህዝብ ትልቅ ውለታ መዋል ነው። እንደ ህፃን ከረሜላ ፖለቲካውን የሚጨማለቁበት ሰዎች ለግዜው ገለል ተደርገው
አዋቂዎች፣ ስትራቴጂስቶች፣ የመዳረሻችን ፍኖተ-መርሁ መቅረፅ የሚችሉ፣ ዛሬን ሳይሆን ነገን ታሳቢ ያደረገ ዘላቂ ሥራ ሊሰሩ የሚችሉ አቅም ያላቸው ሰዎች ወደፊት መምጣት አለባቸው።

ምሁራን ስል ብዙ ዲግሪ ያላቸውን እያልኩኝ አይደለም፣ አዋቂዎችን ነው። ብዙ ዲግሪ ኖሮት በድንቁርና የሚኖረው ብዙ ነው። እንደገና ዲግሪም ኖሯቸው የተደበቁ አዋቂዎች አሉ። የሚፈለጉት እነዚህ ናቸው። በነገራችን ላይበዚህ ጉዳይ ባለፈው በአማራ ቴሌቪዥን ዶክተር ዓለማየሁ ልክ እንደ ዲያቆን ብርሃኑ አድማሱ የተናገረው ትኩረቴን ስቦታል።
እንዲህ ነበር ያለው፣

"...በነገራችን ላይ ማህይምነትና ድቁርና ሁለቱ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ማህይም የሚል የትምህርት እድል ያላገኘ ነው። ድንቁርና ግን የትምህርት እድልም አግኝቶ በማህይምነት ግርሻ የተጠቃው ነው። ፈረንጆች ምን ይላሉ arogance (እብሪተኝነት) Ignorance (አለማወቅን) ያመጣል። arogance እና Ignorance ይመጋገባሉ። ማህይምነት ሲያገረሽብህ እብሪተኛ ትሆናለህ፤ እብሪተኛ ስትሆን ደግሞ የበለጠ ማህይምነት ያገረሽብሃል። እናም ብዙዎቻችን በዲግሪያችን ጀርባ በድቁርና ነው የምንኖረው። ሰውም እንዳይመክረን ዲግሪ አላቸው ይባላል። በእድርም ስትሄድ ዶክተር ይናገር ነው የሚባለው። ግን ሰውየው መሃይምነት ውስጥ ነው ያለው።.... እና ምንድነው እየሆነ ያለው ብላችሁ ያያችሁት እንደሆነ...መደማመጥ የሌለው፣ መነጋገር የሌለበት፣ ማንተማመነው፣ ለችግሮቻችን መፍትሔ ማናገኘው የምሁር ቁጥር እንጂ የአዋቂ ቁጥር ስለሌለ ነው። ለምን ያላችሁ እንደሆነ አብዛኞቻችን በመሃይምነት ግርሻ ውስጥ ስላለን ነው። የዲግሪ ፎቶ በየቤቱ ስትሄዱ ግድግዳ ላይ ታያላችሁ። በትክክል ያ የሚያሳየው ሰውዬው በማህይምነት መኖሩን ነው። ምክንያቱም ማረጋገጫው ያ ብቻ ነው። ሌላ ምን ያሳያል? ምን እናሳያለን ሌላ?...."

ስለዚህ ወደ አማራ ፖለቲካ አዋቂዎች ካልመጡ በስተቀር በእውቀትና በኢንቨስትመንት ተደራጅተው የመጡ ጠላቶች በስትራቴጂና በታክቲክ በድቁርና ግርሻ የሚኖሩትን አያሞኙ መሄዳቸውን ይቀጥላሉ.....