Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.61K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-03-01 20:43:04
10.9K viewsTadele Tibebu, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 20:42:53 የዓድዋ ድል በዓል ዋዜማ #በደብረማርቆስ

"…በሁለት ወገን የተሣለ ሰይፍ ሆነው የሚወለዱ ጀግኖች ምድር። የጀግናው በላይ ዘለቀም፣ የመልአከ ብርሃናት አድማሱ ጀምበሬ፣ የክቡር ዶክተር ሀዲስ አለማየሁ፣ የየኔታ ዮፍታሄ ንጉሤ፣ የእማሆይ ገላነሽ፣ የሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው፣ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ የንጉሥ ተክለሃይማኖት ሃገሯ የጥንቷ መንቆረር፣ የአሁኗ ደብረ ማርቆስም የታላቁን የዓድዋ የድል በዓል ዋዜማ በዚህ መልኩ እያከበረች ትገኛለች። #ዘመዴ
9.3K viewsTadele Tibebu, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 20:40:31
9.1K viewsTadele Tibebu, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 20:40:22 የዓድዋ ድል በዓል ዋዜማ #በደብረብርሃን ከተማ
9.0K viewsTadele Tibebu, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 20:07:52
4.0K viewsTadele Tibebu, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 20:07:42 ከደጋ ዳሞት 6000 ጦር ይዘው የዘመቱት አሥርግና አደገኛው የጎጃሙ ዐማራ ራስ መንገሻ አቲከም እኒህ ናቸው።

እስከ ምሳ ሰዓት ድረስ የሜጀር ቶሴሊ የሚመራውን የጥልያን ጦር ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀሩ ድባቅ የመቱት ራስ መኮንን ከሐረር፣ ራስ ሚካኤል ከወሎ፣ ራስ ወሌ ከቤጌምድር፣ ራስ መንገሻ አቲከም ከጎጃም፣ ፊታውራሪ ገበየሁ ተክሌ ከሸዋ ዐማሮች ናቸው። በጥልያን በኩል ከተሰለፈው 2450 ውስጥ 200 ብቻ እስኪቀር ድባቅ የመቱት፣ ከ34 የጥልያን መኮንኖች የጦር መሪውን ቶሴሊ ጨምሮ 31'ዱን የገደላቸው ይህ ጥምር የዐማራ ሠራዊት ነው። የጦር ጀኔራሉን ማጆር ቶዚሊን የገደለው ፊታውራሪ አባ ውርጂ ናቸው። አርበኛው ከጀኔራል ማጆር ቶዞሊን ጋር ፊት ለፊት ተገናኙ። ሽጉጡን እስኪያወጣ ድረስ ውርጂ ጊዜ አልሰጠውም። ትግል ገጥመው ተያይዘው ገደል ገቡ። የሁለቱም የህይወት ፍጻሜ ሆነ። አላጌ ላይ ከፊታውራሪ አባ ውርጂ በተጨማሪ ሌላ የሞተ ጀግና የጦር መሪ አለ። እርሱም ጊድን ገብሬ የሚባል የላስታና የዋግ የጦር መሪ ነበር። እህቱም ጥይት በቀሚስ ጫፍ እየቋጠረች ስታቀብል አብራ ሞታለች። እነዚህ ሁለት ሰዎች እንዲህ ተሞግሰዋል፤

"ጊድን ገብሬ የባሕር አዞ
አሁን ይደርሳል ጥይቱን መዞ
ጊድን ገብሬ ጥቁሩ ዐንበሳ
የላስታው ውጋት የዋግ ነቀርሳ
የጊድን እህት ምጥን ወይዘሮ
ጥይት አቀባይ እንዳመልማሎ"
(ሥርገው፣ ዳግማዊ ምኒልክ፣ 229-230)

በዚያው ሰሞን ልጁም አዋቂውም ዐማራውም ትግሬውም ገበየሁ ገበየሁ ብሎ አነሣው። ጎበዝ አየሁ ብሎ ስም አወጣለት። ገጣሚም እንዲህ ሲል አሞግሷል፤

"የንጉሥ ፊታውራሪ የጎራው ገበየሁ
አላጌ በሩ ላይ ማልዶ ቢገጥማቸው
ለምሳም አልበቁት ቁርስ አደረጋቸው"
(ሥርገው፣ ዳግማዊ ምኒልክ፣ 230፣
ታሪክ ዘመን፣ 233-241)
4.1K viewsTadele Tibebu, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 19:43:56
5.0K viewsTadele Tibebu, 16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 19:43:29 የአድዋው ጀግና ናቸው። የቤጌምድር ዐማራ ናቸው።
ከዐፄ ቴዎድሮስ ከፍተኛ ሹም ከነበሩት ከአፈንጉሥ ወርቄ ይወለዳሉ። የአድዋው መብረቅ ደጃዝማች መሸሻ ወርቄ ማለት እኒህ ናቸው።
4.9K viewsTadele Tibebu, edited  16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 19:22:09
5.9K viewsTadele Tibebu, 16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 19:21:52 #ሼር_ፖስት ይሁን! ራስ መኮነን ከሐረር ይዞት የዘመተው ከ15 በላይ ጦር በአብዛኛው የጎንደር ዐማራ መሆኑን በቀደም ገልጬ ነበር። ይህንም በሁለት የዘመኑ የዐይን ምስክር ጽሐፊዎች ተረጋግጧል። የመጀመሪያው የራሳቸው የራስ መኮነን ዜና መዋዕል ጸሐፊ ግራጌታ ኃይለጊዮርጊስ በለጠ ሲሆኑ፣ ሁለተኛው ደግሞ በራስ መኮነን ቤተመንግሥት ያደገው ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም ናቸው።

ግራጌታ በግእዝ ቋንቋ በጻፉት ዜና መዋዕል አብዛኛውን የራስ መኮነን ሠራዊት የጎንደር ወታደሮች እንደነበሩ ጠቅሰዋል። የጎንደር ዐማራ ወታደሮችን ከራስ መኮነን ጋር በሐረር እንዲቀመጡ ያደረጉት ዳግማዊ ምኒልክ ናቸው።
ግእዙ በአማርኛ ሲተርጉም እንዲህ ይላል፣

". . . ከዚያም ዳግማዊ ምኒልክ ከደጃዝማች መኮንን ጋር የተዋቸውን የጎንደርን ወታደሮች 'ከልጄ ከደጃዝማች መኮንን ጋር በፍቅር ተቀመጡ፡ እንደ መንፈሳዊ ድንጋይና እንደ ንጉሥ ታቦት ጽኑ፡ ከብዙዎቹ የመንግሥቴ ሰራዊት እናንተ ተመርጣችኋልና" አላቸውም። ደጃዝማች መኮንንም "አንተም እንደ ዓይን ብሌን ጠብቃቸው፤ እነሱ እንደ እጅና እነ እግር ይሁኑህ" አሏቸው። ንጉሠችን ምኒልክን ይህንን ተናግረው ወደ ሸዋ ተመለሱ፤ በሰላም በደኅና ሸኙዋቸው"
(ዜናሁ፡ ለልዑል፡ ራስ መኮንን፣ 24-25)

ምኒልክ ወደ ሐረር በአቀኑ ግዜ ነበር የጎንደር ወታደሮች ከሌላው ሠራዊት ተመርጠው ከደጃዝማች መኮንን ጋር በሐረር እንዲቀመጡ ያደረጉት። ደጃዝማች መኮንንም እንደ ዐይኑ ብሌን እንዲንከባከባቸው ነግረው ከሐረር ወደ ሸዋ ተመልሰዋል። ከስድስት ዓመት በኋላ ራስ መኮነን በ1888 ዓ.ም. ወደ አድዋ ይዞ የዘመተው ጦር በሐረር የነበረውን የጎንደር ዐማራ ሠራዊት አሰልፎ ነው።

ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያትም በጻፉት ኦቶባዮግራፊያቸው ይሄንኑ ያረጋግጣሉ። የሐረር ሠራዊት ቀዳሚው ጎንደሬ እንደሆነ፣ በሐረር የጎንደሬዎች እንደራሴ ግራዝማች ጎሹ እንደሚባል፣ እንዲያውም ለፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ደጃዝማች ጎሹ "ጎንደሬ ለተፈሪ መክቶ ይሞታል። ለዚህ እኔ አለሁ" ብሎ በአንደበቱ እንዳረጋገጠለት፣ ተክለሐዋርያትም ግራዝማች ጎሹን "እንማማል" ሲለው፤ "ብከዳ ምድር ትክዳኝ" ብሎ እንደማለለት ጽፈዋል። (ኦቶባዮግራፊ፣ 284-285)

በነገራችን ላይ ግራዝማች ጎሹ የዐፄ ቴዎድሮስ ወታደር ነበሩ። የትውልድ ስፍራቸው ቋራ ነው። በአድዋ ጦርነት ቆስሎ በሕይወት የተረፈው እና በ1927 ዓ.ም. ኦጋዴን ወልወል ላይ መሰዋት የሆነው የፊታውራሪ አለማየሁ ጎሹ አባትም ናቸው።

ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ ወድቆ ጦራቸው ሲበተን ጎሹ ወደ ሸዋ ተሻግሮ ምኒልክ ያደራጁት "ጎንደሬ" የሚባለው የዐፄ ቴዎድሮስ ወታደሮች ሻለቃ መሪ ነበሩ። ምኒልክ ለራስ መኮነን በሐረር ጠባቂ እንዲሆኑት የተውለት ይህን ታማኝና ምርጡን የጎንደሬ ሠራዊት ነበር። የዚህ ሠራዊት መሪ ደግሞ የቋራው ግራዝማች ጎሹ ሲሆን፣ በራስ መኮነን ስር ሆኖ የሐረር ሠራዊት ቀዳሚ የሆነውን የጎንደሬ ጦር እየመራ ወልወል ላይ መሰዋት የሆነው ልጁን አለማየሁን አስከትሎ ወደ አድዋ ዘምቷል።

ይህ እውነተኛ ታሪክ ገና አልተጻፈም። በራስ መኮነን መሪነት ወደ አድዋ ዘምቶ ኅዳር 28 ቀን 1888 ዓ.ም. አምባላጌ ላይ፣ ታኅሳስ 1888 ዓ.ም. መቐለ ላይና በመጨረሻም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. አድዋ ላይ የተዋደቀው የሐረር ዘማች ጎንደሬ ዐማራ ገድል ገና አልተነገረም። በራስ መኮንን እየተመሩ ከሐረር ተነስተው ወደ አድዋ ከዘመቱት የጎንደር ዐማራ ጦር ከሚታወቁ ዝነኛ መሪዎቹ መካከል ግራዝማች ጎሹ፣ ፊታውራሪ ዓለሙ፣ ፊታውራሪ ኮላሴ ብሩ፣ ልጃቸው ልጅ አበበ ኮላሴ፣ ቀኛዝማች ወልደ ጻዲቅ ታሪክ ገና አልተጻፈም። (ኦቶባዮግራፊ፣ 55) በጣም የሚያስገርመው በ1928 ዓ.ም. በኢትዮ-ጥሊያን ጦርነት ወቅት የጎንደሬው ዐማራ የአድዋው ዘማች የፊታውራሪ ኮላሴ ልጆች ፊታውራሪ ጓንጉል ኮላሴና ወንድማቸው ኃይለማርያም ኮላሴ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ታንክ የማረኩ መሆናቸውን ጳውሎስ ኞኞ መዝግቧል።

ምንጭ፦
-ግራጌታ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘሐረር፣ ዜናሁ ለልዑል ራስ መኮንን፣ በ1965 ዓ.ም. በአርቲስቲክ ማተሚያ ሊሚትድ.

-ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም (ፊታውራሪ)፣ ኦቶባዮግራፊ፣ 2007 ዓ.ም. 4ኛ ዕትም. አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ.

#ጥቆማ በዚህ አጋጣሚ ሆን ተብሎ እንዲጠፋ የተደረገው የግራጌታ ኃይለ ጊዮርጊስ "ዜናሁ ለልዑል ራስ መኮነን" የግዕዝ መጽሐፍ ቴሌግራም ላይ በpdf ጭኘዋለሁ አውርዳችሁ ማንበብ
6.3K viewsTadele Tibebu, 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ