Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.42K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2023-02-26 19:45:34
8.7K viewsTadele Tibebu, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 19:45:23 የባህርዳር ወጣት በነቂስ ወጥቶ ለእስክንድር ነጋ ድጋፉን ገልጿል። እናመሰግናለን።
8.7K viewsTadele Tibebu, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 19:04:04
10.2K viewsTadele Tibebu, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 19:03:55 እስክንድር ነጋ እና አብረውት የታሰሩት አሁን ተፈተዋል
9.9K viewsTadele Tibebu, 16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 13:41:37
13.8K viewsTadele Tibebu, 10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 13:41:17 የዐማራን ጀግና በዐማራ ሆ*ዳ*ም ማሸነፍ ማለት ይሄ ነው።
ሽብርተኛው ህወሓት በዐማራ ህዝብ ላይ የዘረጋውን የአፓርታይድ ሥርዓት ይበልጥ ለማጠናከርና የኢኮኖሚውን አውታር፣ የፖለቲካውን ቦታ ለመቆጣጠር የነበራቸውን ፍላጎት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርለት እዛው ከዐማራው አብራክ የወጡ ሆ*ዳ*ም ዐማሮችን ሥልጣን ላይ አስቀምጦ የዐማራ ጀግኖችን እንዲያጠፉ አድርጓል። በጣም የሚያስገርመው ይሄን ዘዴውን በጦርነቱ ግዜም ተግባራዊ አድርጎታል። ለሕወሓት ታጣቂዎች መረጃዎችን አሾልከው የሚሰጡ ሆ*ዳ*ም ዐማራዎች ነበሩ። ለምሳሌ በጉናና በክምር ድንጋይ ጦርነቱን እንዲያስተባብር የተመደበ አንድ የብልፅግና ካድሬ ለሕወሓት መረጃ አሳልፎ ሲሰጥ የስልክ ልውውጡ ተጠልፎ እርምጃ እንደተወሰደበት የምናስታውሰው ነው። ይህ የተደረሰበት እንጂ በ*ሆ*ዳ*ቸ*ው ተገዝተው መረጃ አሰልፈው ይሰጡ የነበሩ ከፍተኛና መካከለኛ ሆ*ዳ*ም አመራሮች ነበሩ። ሕወሓትም ይህን ስትራቴጂ "የዐማራ ጀግኖችን በዐማራ ሆ*ዳ*ሞ*ች ማሸነፍ" ይለው ነበር።

የአብይ አሕመዱ ኦነግ-ብልፅግናም እየተከተለው ያለው አካሄድ የዐማራ ጀግኖችን በዐማራ ሆ*ዳ*ሞ*ች ማጥፋት ነው። እንደ ዔሳው ብርኩናቸውን የሸጡ አመራሮች የዐማራ ጀግኖችን በማጥፋት እየተባበሩ ናቸው። በአቶ ታምራት ላይኔ የተጀመረው ሆ*ዳ*ም*ነ*ት ውርስ ሆኖ መተላለፉ ግን ያሳዝናል።

እነዚህ ሰዎች የራሳቸው ሀሳብ የሌላቸው አብይ አሕመድ ተኙ ሲላቸው የሚተኙ፣ ተነሱ ሲላቸው የሚነሱ አስተላላፊ ቱቦዎች ናቸው። የአብይ እሐመድን ንቅዘት እየተከታተሉ የሚሸፍኑ ገመና ሸፋኞች ናቸው። ቁልፍ ችግራቸው ቱቦነት፣ አድርባይነት (Opportunism) እና መስሎ አዳሪነት ነው። አብይ አሕመድ የሥልጣን በር ካሳያቸው ሙሉ ዐማራን በክላሽ ረፍርፎ የመሄድ ችግር የለባቸውም።

ታሪክ፣ "የኦሪት ዘመን አይሁዳውያን ራሳቸው ከወርቅ ጠፍጥፈው በሰሩት ጥጃ ስር በመወድቅ ይሰግዱለት ነበር፣" ይለናል። ይህ ይሁዳውያኑ ድርጊት በባእድ አምልኮት ምሳሌነት ለትውልድ ተላልፏል፡፡ በአብይ አሕመድ እና በብአዴን ውስጥ ባሉ አመራሮች እየታዘብነው ያለው የይሁዳውያኑን የወርቅ ጥጃ የመሰለ የባእድ አምልኮታዊነት ያለ ነው። ለንጉሣቸው ለአብይ እያጎነበሱ ሥልጣናቸውን የሙጥኝ ብለው ከሰውነት ጎድለው ዐማራን ማዋረድና እንዳይደራጅ ማድረግ።

የዐማራን ጀግና በዐማራ ሆ*ዳ*ም ማሸነፍ!
13.4K viewsTadele Tibebu, edited  10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 13:34:20
12.2K viewsTadele Tibebu, 10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 13:34:06 ሀ. አለቃ ተክለ ኢየሱስ ዋቅጅራ የንጉሥ ተክለ ሃይማኖትንና የጎጃምን ታሪክ መሠረት አድርገው በጻፉት መጽሐፍ እንዲህ ይላል፣

"... ሸዬና ጎጃሜ ቤጌምድሬ እንደ እሳት እራት እየዘለለ እየገባ በውጅግራና በሲናደር አየሁ በባንትይርጋ ዘለሰው።... ያንጊዜ የኢጣልያ ጦር አለቃ ጂኒናር በራትሪ ድሮ የናቀው ጦር ጠገነነውና በድንጉላው ተጋብቶ ወደ ሀገሩ ፈረጠጠ። የ3ቱን ቀን መንገድ በአንድ ቀን ጋልቦ ደረሰው። የቀረው እግረኛው ግን እሮጣለሁ ሲል ጫማው እየከበደው አውልቆ እንዳይሮጥ አቀበትና ቁልቁለት ጠጠር እየወጋው የኋሊት እየተኮሰ እሮጣለሁ ሲል ከእንዝርት የቀለለ የጁየ፣ ከነብር የፈጠነ ቤገምድሬ፣ ተቋንጣ የደረቀ ትግሬ፣ ከአሞራ የበረረ ሸዬ፣ ከንብ የባሰ ጎጃሜ እያባረረ በየመንገዱ ዘለሰው። አውሬ የጨነው ነጭ መጋዣ እየመሰለ በየዱሩ ሆዱን ገልብጦ ወደቀና የአሞራ ቀለብ ሆነ።"(ተክለ ኢየሱስ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ 305)

እንደ አለቃ ተክለ ኢየሱስ በአድዋ ጦርነት የተሰለፉት ተዘርዝረዋል። ከእንዝርት የቀለለ የየጁ ዐማራ፣ ከነብር የፈጠነ የቤጌምድር ዐማራ፣ ከአሞራ የረበበ የሸዌ ዐማራ፣ ከንብ የባሰ የጎጃም ዐማራ በዚህ ጦርነት የነበራቸውን ሚና ገልጠውለታል። ይቀጥሉና "ያ ቀን ጦርነቱ ብርቱ ነበረ። በነግህ ተኩስ የተጀመረ ማታ ተለያየ። ያን ቀን ከዐማራውም ከኢጣሊያውም እየቆሰለ እሚያነሳው እየታጣ ሐሩር እየያዘውም በውሃ ጥም ሲጨነቅ ከየደገላው እሳት እነተነሳ አቃጥሎ ፈጀው። ያን ጊዜ መንገዱ ባይከፋ፣ ሠራዊቱ ባይጎዳ፣ ዐማራ ጨክኖ ቢከተል ኖሮ ጣሊያን አንድ ለዘር አይተርፍም ነበር። አስመራን አስለቅቆ ከጥንት ሀገሩ ይሰደው ነበር።" (ተክለ ኢየሱስ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ 306)

ለ. በሌላ በኩል ይኸኑ ጦርነት ፕርፌሰር አፈወርቅ ገብረየሱስ "ዳግማዊ ምኒልክ" በሚለው መጽሐፋቸው እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል፤

"...ሸዋ ፈረሰኛ፣ ጎጃም እግረኛ፣ የትግሬ ነ.ፍ.ጠ..ኛ፣ ያማራ ስልተኛ ከቦ ያናፋው፣ ይቀላው፣ ያንገድገው ጀመር። ...ከንዝርት የቀለለ የጁዬ፣ ተነብር የፈጠነ ቤጌምድሬ፣ ተቋንጣ የደረቀ ትግሬ እየደረሰ ፈጀው፣ አሰጣው፣ ዘለሰው።"
(አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ፣ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ፣ 100)

እንዲህ አይነቱ በዘመኑ የተዘገቡ ታሪኮች ትውልድ እንዲያውቃቸው ባለመደረጉ ግፍ ተፈጽሞብናል ብለው አፈታሪክ በመውሰድ እና ቃላትን በይመስላል በማገጣጠም (wild guess based on phonetic combination) በስሁት ትርክት የአኖሌን ሐውልት ያቆሙ የትላንት የታሪክ ምርኮኞች ታሪክን በማዛባት (manipulation of history) የትውልዱን አእምሮ በድንቁርና ምርጊት እየደፈኑት ይገኛሉ።


ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut
12.2K viewsTadele Tibebu, edited  10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 13:34:06 #ሼር_ፖስት የዚህ መረጣዊ አቀራረብ (Unavoidable selection) ዋና ዓላማ ምኒልክን ከዓድዋ መነጠል፣ "የኔ ነው" የሚሉትን አጉልቶ ማሳዬት ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ብርቅዬነቷን (exceptionalism) በመናድ በፍርስራሿ ላይ "ታላቋን ኦሮምያ" መገንባት ነው። መረጣዊ አቀራረብ ስንል የታሪክ ሐቆችን በመካድ (abuse by denial of historical facts)፣ የዓድዋን ዋና መሪ የምኒልክን ታሪክ ሆን ብሎ በመዝለል የምኒልክ ታዛዥ የነበረውን ባልቻን ማንገሥ ነው። እንደምታዮት ጊዜ፣ ቦታ ፣ እና ክስተትን በማዛነፍ,፣ አብይ አሕመድን 127 ዓመት ወደኋላ ጎትተው ወስደው ያለቦታው አስቀምጠውታል።

እነዚህ "ከዋሸህ ትልቅ ውሸት ዋሽ፣ ደጋግመህም ተናገረው። ቀስ በቀስ ሰዎች እያመኑት ይሄዳሉ" የሚለውን የናዚ ፓርቲ የፕሮፓጋንዳ ሚኒስቴር የነበረው ጆሴፍ ጎብልስ ፍልስፍና የሚከተሉ ሂትለራዊያን በዚሁ መልኩ መረጣዊ አቀራረብን ሲያመጡ ትክክለኛው የአድዋ ጦርነት ታሪክ ደግሞ ሊነገራቸው ይገባል።

ወደ አድዋ ከዘመቱት ነገሥታቶች፣ አዋጊዎች፣ ራሶችና ጠቅላይ አገረ ገዢዎች፣ ደጃዝማቾች፣ ፊታውራሪዎች፣ ቀኛዝማቾች፣ ግራዝማቾች፣ ባላምባራሶች በአመዛኙ ከዐማራው ነገድ አብራክ የወጡ ዐማሮች ናቸው። በመሪ ደረጃ ከኦሮሞ የዘመቱት አፈ ንጉስ ነሱቡ መስቀሎ እና
ሻቃ ኢብሳ ብቻ ናቸው። በጅሮንድ ባልቻ እና ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ በጉልበት ኦሮሞ የተደረጉ ጉራጌዎች ናቸው።

ከዚህ ውጭ የሌቃ ለቀምቱ ሞረዳ በከሬ በኋላ ገብረእግዚአብሔር፣ የጅማው ገዥ አባ ጅፋር፣ የሌቃ ቄለሙ ጆቴ ቱሉ፣ የወላይታው ካዎ ጦና፣ የአውሳው ገዥና ባላባት መሐመድ አንፋሪ፣ የቤን ሻንጉሉ ሼህ ሆጄሌ፣ የአፋሩ ሡልጣን ጧላ እና አፍሬ፣ ስም እያላቸው በዐድዋ ጦርነት ጊዜ አንዘምተው ብለው የቀሩ ሀገረ ገዥዎች ናቸው።

ከዚህ ውጭ፦

1. የመንዝ ባላባት ከሆኑት ከክቡር ደጃዝማች ወልደ ሚካኤል ወልደ መለኮትና ከንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ልጅ ከልዕልት ተናኘ ወርቅ በ1834 ዓ.ም. የተወለደው ራስ መኮነን ወልደ ሚካዔል ዐማራ ናቸው። ራስ መኮነን ከሐረር ይዞት የዘመተው ከ15 ሺህ በላይ ጦር በአብዛኛው የጎንደር ዐማራ ነው። ይህን ማወቅ የሚፈልግ በዘመኑ የዐይን ምስክር ጽሐፊዎች የጻፉትን የራስ መኮነን ዜና መዋዕል ጸሐፊ ግራጌታ ኃይለጊዮርጊስ እና ሁለተኛው ደግሞ በራስ መኮነን ቤተመንግሥት ያደገው ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያምን "ኦቶባዮግራፊ" ማንበብ ነው።

2.አድዋ ላይ የተሰውት የአንባላጌው አንበሳ ፊታውራሪ ገበየሁ ተክሌ የግድም ወርቅ ዐማራ ናቸው።

3. የጎቦዞች ጎበዝ የሆነው የምኒልክ የአክስት ልጅ ባሻህ አብዬ ዐማራ ነው።

4. እጦሩ ሜዳ መካከል ዘሎ በመግባት የጠላትን መድፍ የማረከው ደጃዝማች ጫጫ ዐማራ ነው።

5. የራስ መንገሻ አቲከም አማች የወይዘሮ አስካለ ማርያም መንገሻ ባል ቀኛዝማች ታፈሰ አባይነህ ዐማራ ነው።

6.ዲፕሎማቱ ፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ እና የጀግኖቹ ጀግና ፊታውራሪ ተክሌ ዐማሮች ናቸው።

7. ከ35 ሺ በላይ የጎንደር ጦር እየመሩ ወደአድዋ የዘመቱት
የዐፄ ምኒልክ ባለቤት የእቴጌ ጣይቱ ወንድም ራስ ወሌ ቡጡል ኃይለ ማርያም እና የእቴጌ ጣይቱ የእኅት ልጅ የወይዘሮ ደስታ ብጡል ልጅ ደጃዝማች ገሠሠ ወልደ ሐና ዐማራ ናቸው።

8. በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበሩት የፊታውራሪ ተሰማ ባንቴ አባት ባላምባራስ ባንቴ ዐማሮች ናቸው።

9."ማን በነገረው ለጣልያን ደርሶ፤ ሚካኤል መጣ ረመጥ ለብሶ!” የተባለላቸውና ከ15 ሺ በላይ ጦር የዘው የዘመቱት
የወሎው ንጉሥ ሚካኤል አሊ፣ የዐፄ ፋሲል የልጅ ልጅ የሆኑት የኢማም አሊ አመዴ ልጅ ናቸው።

10.አነጣጣሪው መድፈኛ ራስ አባተ ቧያላው ንጉሡ ከአባታቸው ከደጃዝማች ቧያለው ንጉሡና ከእናታቸው ከዋግ ተወላጇ ከወይዘሮ ዓመተማርያም ሀጎስ በ1863 ዓ.ም. መንዝ ውስጥ የተወለዱ ዐማራ ናቸው።

11. ከፊታውራሪ ገበዬሁ ጋር በመሆን ጀኔራል አልቤርቶኒንና ጀኔራል አሪሞንዲን አድዋ ላይ ጥለው የወደቁት ፊታውራሪ ተገኜ ወርቄ የጎጃም ዐማራ ናቸው።

12. አድዋ ላይ በፈረስ ሆነው ሰልፉን እያለፉ ሲማርኩ እና ብዙ የጀግንነት ሥራ ሲሠሩ ቆይተው ምሸት ላይ በመድፍ ተመተው የወደቁት ደጃዝማች በሻህ አቦዬ የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የልጅ ልጅና የምኒልክ አክስት የወይዘሮ አያህሉሽ
ልጅ ናቸው።

13. ከዐፄ ቴዎድሮስ ከፍተኛ ሹም ከነበሩት ከአፈንጉሥ ወርቄ የሚወለዱት ደጃዝማች መሸሻ ወርቄ የቤጌምድር ዐማራ ናቸው።

14.ከ20 ሺህ በላይ የጎጃም ዐማራ ሠራዊት ይዘው ወደ አድዋ የዘመቱ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት፣ አሥርግና አደገኛው ራስ መንገሻ አቲከም የጎጃም ዐማራ ናቸው።

15. የአምባሰል ገዥ የነበሩት፣ እነ ጊድን ገብሬን ያካተተው ተዋጊ ሠራዊት የመሩት፣ ማርያም ሸዊቶ ላይ ጀኔራል አልቤርቶኒን የማረኩት ዋግ ሹም ጓንጉል ብሩ የዳግማዊ ዐፄ ተክለጊዮርጊስ የወንድም ልጅ የዋግሹም ብሩ ልጅ ናቸው።

16. በተጨማሪ በአድዋ ጦርነት ዝነኛ የነበሩት እነ
ባላምባራስ አጥናፌ፣ ደጃዝማች ተሰማ ናደው፣
ደጃዝማች ወልዴ፣ ደጃዝማች ውቤ አጥናፍ ሰገድ፣
ቱርክ ባሻ ታምሬ፣ አጋፋሪ ወልደ ገብርዔል፣ ባሻ ገድሌ፣ ሊቀ መኳስ አድነው፣ ባላምባራስ ወሰኔ፣ ባላምባራ አየለ፣ አዝማች ዛማኑኤል፣ በጅሮንድ ከተማ፣ አዛዥ በዛብህ፣ ቀኛዝማች መኮነን፣ አሳላፊ ገበዬሁ እና ልጅ ናደው ዐማሮች ናቸው።

እነዚህና ሌሎች ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ያስቻሉ ምርጥ የዐማራ ኢትዮጵያዊ ተዋጊዎች ናቸው። በአድዋ ጦርነት አብዛኛውን የዘመተው የሠራዊት ብዛት ስንመለከት ደግሞ፣ በአብዛኛው የዐማራ ህዝብ በሚኖርባቸው ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ እና ከሸዋ ነው።

የአድዋ ጦርነት ከተጠናቀቀ ከስድስት ዓመታት በኋላ በ1894 ዓ.ም. ጆርጅ ኤፍ ኤች በርክሌይ የአድዋ ዘመቻና የዐፄ ምኒልክ አነሣሥ (The campaign of Adowa and the Rise of Menelik) በሚለው መጽሐፉ የአድዋን አሰላለፍ ጽፏል። መጽሐፉን ዳኛው ወልደሥላሴ በ1967 ዓ.ም. ተርጉመውታል። እንግሊዛዊው የታሪክ ዘጋቢ ጆርጅ በርክሌይ ኢትዮጵያን የጦር አበጋዞች በመጥቀስ እንደጻፈው በአድዋ ጦርነት ከኢትዮጵያ የዘመተውን ሠራዊት 145 ሺህ ነው።

1. ከጎንደር ባጠቃላይ የዘመተው 35 ሺህ ሲሆን ፈረሰኛው 10,000፣ የጦር መሳሪያ የያዘው 20,000 ተከታዩ 10,000 ነበር።

2. ከጎጃም ባጠቃላይ የዘመተው 20 ሺህ ሲሆን፣ ፈረሰኛው 8,000፣ የጦር መሣሪያ የያዘ 11,000፣ ተከታይ 2,000 ነበር።

3. ከወሎ እና ከሸዋ የዘመተው 70 ሺህ ሲሆን ፈረሰኛው 35,000፣ የጦር መሳሪያ የያዘው 28,000፣ ተከታይ 8,000 ነበር።

4. ከትግሬ 20 ሺህ የዘመተ ሲሆን፣ ፈረሰኛው 4,000፣ የጦር መሳሪያ የያዘው 15,000፣ ተከታይ 8,000 ነበር። ባጠቃላይ 145 ሺህ ሠራዊት ወደ አድዋ የዘመተ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 57,000 ፈረሰኛ፣ 75,000 የጦር መሳሪያ የታጠቀ፣ 28,000 ተከታይ ነበር።
(በርክሌይ፣ 10)

እነዚህን ናቸው በቋጥኝና በተሰነጣጠቁ የአባ ገሪማ ገድሎች፣ በአድዋ ተራራዎች፣ በእንዳ ኪዳነ ምሕረት ኮረብታ፣ በማርያም ሻዊቶ ሸለቆ፣ ጣሊያንን ተዋግተው ድል ያደረጉት። ጦርነቱንና የጦርነቱን ታሪክ የተከታተሉ ሰዎች ምስክርነት ብንስማ ይሻላል።
11.6K viewsTadele Tibebu, edited  10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 19:36:39
11.7K viewsTadele Tibebu, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ