Get Mystery Box with random crypto!

Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tadeletibebu — Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
የሰርጥ አድራሻ: @tadeletibebu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 58.61K
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-03-13 17:39:20
7.1K viewsTadele Tibebu, 14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 17:38:59 በምዕራብ ጎጃም፤ ሰሜን አቸፈር ወረዳ ሊበን ከተማ የሆነው ነገር እጅግ በጣም ልብ ይሰብራል፣ በፎቶ የምትመከቱት ልጅ ህይወቱ አልፏል። መብራትና ውሃ ለጠየቀ ማኅበረሰብ ጥይት አይገባውም ነበር። ነገርግን በሰላማዊ መንገድ ለጠየቀው መልስ በጉቦ (Bribery)፣ በሥልጣን መባለግ (Abuse of power)፣ በስርቆትና ዘረፋ (Embezzlement)፣ በጥቅም ተካፋይነት (kickbacks) የተጨማለቁ የወረዳው አመራሮች ምላሽ በጥይት አርከፍክፎ መግደል ሆኗል። የወረዳው የፀጥታ አባል በወሰዱት እርምጃ ሦስት ልጆቹን ማለትም ወጣት ኤርሚያስ አብየ፣ ወጣት ዳኛቸው አዲስን እና ወጣት ቸርነትን ተኩሶ አቁስሏል። ከእነዚህ መካከል በፎቶ የምትመለከቱት የ16 ዓመት ወጣት ኤርምያስ አብየ በጥበብ ጊዮን ሆስፒታል ሲረዳ ቢቆይም ዛሬ ሕይወቱ አልፏል።

በጣም የሚያሳዝነው 460 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የሚያመነጨው ጣና በለስ የሚገኘው በዚሁ ወረዳ ቁንዝላ ከተማ አካባቢ ነው። ነገርግን ከቁንዝላ ጀምሮ፣ ሳንክራ፣ ደንቦላ፣ ሊበን፣ ይስማላ፣ ዲላሞ፣ ዱርቤቴ እንዲሁም ጭንባና ሻሁራ እንደ ኦሪት ዘመን በጨለማ የሚኖር ማኅበረሰብ ነው። በዚህ የተበሳጨው ማኅበረሰብ በግልፅ ወደ አደባባይ ወጥቶ “ሻማ በቃን! አቸፈር ጨልሞ ሱዳን አይበራም!” የሚል ግልጽ መልእክት ስላስተላለፉ በጥይት ተረሽነዋል። አሁን ለወረዳው የምናስተላልፈው ግልጽ መልእክት አለ። ይሄን ህገ ወጥ ተግባር የፈፀሙ የፖሊስ አባል በህግ ፊት መቅረብ አለባቸው። የተቋረጠው መብራትም በአስቸኳይ እንዲስተካከል እንጠይቃለን።
7.2K viewsTadele Tibebu, edited  14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 11:57:22
14.7K viewsTadele Tibebu, 08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 11:57:09 እስኪ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ትግል ለማካሄድ እንዲረዳን ዛሬ ደግሞ የኦስትሪያዊ ባሮን ሮማን ፕሮችስካ መጽሐፍ ልጋብዛችሁ። ለሌሎችም ሼር አድርጉት።

ከምዕራባውያን ሰላዮች መካከል አንዱ በጃን ሆይ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖር የነበረው ኦስትሪያዊ ባሮን ሮማን ፕሮችስካ ነው። ፕሮችስካ የጣልያን ወግንና የነበረው የጀርመን ናዚስት ብዕረኛ የነበረ ሰው ነው። ይህ ግለሰብ ጥልያን ኢትዮጵያን ከመውረሯ በፊት ለሁለት ዓመታት ያህል በአዲስ አበባ የኦስትሪያ ቆንስላ ውስጥ ተቀምጦ በኢትዮጵያ ይኖሩ ለነበሩ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች አማካሪ፣ በሌላ ሥራ ላይ ለተሰማሩ የውጭ ዜጎች የሕግ አማካሪና ጠበቃ ሆኖ እየሠራ ጎን ለጎን አውሮፓውያን ኢትዮጵያን እንዴት ሊወሩና ሊይዙ እንደሚባ ጥናት ያካሄድ ነበር። ኢትዮጵያን መቆጣጠር የሚቻለው ዐማራ የሚባለውን ጀግና ህዝብ ማዳከም ሲቻል ብቻ መሆኑን፣ ዐማራውን ለማዳከም ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ ነገዶችንና ጎሣዎችን በዐማራው ላይ ማነሳሳት እንደሚገባ፣ ይሄን የጥናቱን ውጤት ደግሞ በአውሮፓ በሚታተሙ ጋዜጦች እያወጣ ጥልያን፣ እንግሊዝና ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በዚህ ጥናት መሠረት እንዲመሩ ከፍተኛ ቅስቀሳ ያደርግ ነበር። በዚህም ምክንያት ጥልያን ኢትዮጵያን ከመውረሯ ሁለት ዓመት ቀድሞ በንጉሡ ትእዛዝ ኢትዮጵያን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። ይህ በዐማራ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የነበረው ሰው ወደ አውሮፓ ከተመለሰ በኋላ በ1927 ዓ.ም. ቪየና ላይ ጥናታዊ ስትራቴጂካዊ ሀሳቡን ወደ መጽሐፍ በመቀየር "Abyssinia the Powder Barrel” ወይንም "ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል" በሚል ርእስ አሳተመ።

ይህ መጽሐፍ የጣልያን ወረራ ከመጀመሩ አንድ ዓመት በፊት በ1927 ዓ.ም 'Abissinia Pericolo Nero' ወይንም "አቢሲንያ ጥቁሯ ሥጋት" በሚል ርእስ በጣልያንኛ ተተርጉሞ ወጣ። ከላይ እንደገለፅነው የመጽሐፉ ዋና ማጠንጠኛ የአድዋ ጦርነት ድል ነጮችን እንዲንቁ እንዳደረጋቸው፣ ነጮችን የሚጠሉ ሕዝቦች ያሉባት፣ የነጮች ክብርና መብት የማይጠበቅባት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ነገዶችና ጎሳዎች ከአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ሊያገኙት የሚገባቸውን ጥቅሞች በዐማራ ኃያልነት ምክንያት እንዳጡ፣ በዚህም ምክንያት በምዕራባዊያን ኢምፔሪያሊስቶች በሞግዚትነት መተዳደርን እንደሚመርጡ ማስረጃ የሚለውን ሁሉ እየጠቀሰ ለማስረዳት ይሞክራል፡፡

ሀገሪቱን ለማስተካከል ሦስት መፍትሔዎችን ያቀርባል፡፡ ኢትዮጵያን በአውሮፓ ቀንበር ለማናቅ አስተዳደሩን በቋንቋና በጐሣ መሠረት አወቃቅሮ መከፋፈል እና አገሪቱን በቅኝ ግዛት ለመያዝ ዐማራዎች ማስወገድ በዋናነት ያስቀምጣቸዋል።


ባሮን ሮማን ፕሮችስካ የዐማራ ነገድ አፍሪካን ጠቅልሎ በቁጥጥር ስር ከማዋል አልፎ ለነጭ ዘሮች የማይመለስ ኃይል መሆኑንና፣ ይሄን አስፈሪ ነገድ ነጮች ተባብረው አስቸኳይ እርምጃ ካልወሰዱበት የሚያቆመው ስለማይኖር ለማዳከም በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ነገዶችና ጎሣዎች እንዲነሱበት ፖሊሲ ቀርፀ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ማሳሰቡን ተከትሎ፣ የተለያዩ የምዕራባውያን ፖሊሲ አውጭዎች የዐማራን ህዝብ ለማጥፋት ወይንም የነፃነት ስነ-ልቦናውን ለመስበር፣ ላለፉት 70 እና 80 ዓመታት በኢትዮጵያ ላይ ለሚያወጡት ፖሊሲ መጽሐፉን እንደ ግብአት ሲጠቀሙበት ኖረዋል።

የጥሊያኑ ፕሮፖጋንዲስት ፕሮችስካ "መታሰብና መታወስ ያለበት ጉዳይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩት አብዛኞዎቹ ሕዝቦች ተጨቋኞች ናቸው፤ ጨቋኟቹ ገዢዎች ደግሞ ዐማሮች ናቸው" (Abyssina The powder Barrel፣ 79) ብሎ የጻፈውን የ60'ዎቹ ታጋዮች የትግል ፍኖተ ካርታ፣ የማታገያ ማኒፌስቶ የሚቀዳበት "ሰፊ ምንጭ" አድርገው ተጠቀሙበት። ኢትዮጵያዊው ሂትለር ዋለልኝ መኮነን ደግሞ "የኢትዮጵያዊነት ትርጓሜ የዐማራ ገዢ መደብ ፍልስፍናን የማጉላትና ኢትዮጵያዊ ማለት አማርኛ የሚናገር፣ ክርስቲያን የሆነና ሸማ የሚለብስ ነው" በማለት የፕሮችስካን ቀኖና ገልብጦ አሳትሞታል።

የዋለልኝ "የብሔሮች ጥያቄ በኢትዮጵያ" የሚለው መጽሐፍ ለፋሺስት ጥሊያን የአምስት አመታት አገዛዝ እንደ መመሪያና ማንዋል ያገለገለው፣ “አቢሲኒያ ፔሪኮሎ ኔሮ” የሚለው የባሮን ፕሮችስካ ፀረ-ዐማራ መጽሐፍ የካርቦን ግልባጩ ነው ምንም ልዩነት የለውም። በፕርችስካና በዋለልኝ መካከል ቢያንስ የ34 ዓመት ልዩነት አለ። ፕሮችስካ መጽሐፉን የጻፈው በ1927 ዓ.ም. ሲሆን፣ በጀበሃ ዋለልኝ የታተመው መጽሔት እና መጽሐፍ ደግሞ በ1961 ዓ.ም. ነው።

ፋሺስቶች ዐማራን ነጥለው ለማጥፋት የቀየሱት የጎሳ ንድፍ ከጥልያን ሽንፈት ጋር በ1933 ዓ.ም. ቢያከትምም፤ የጥሊያንን ቅያስ ከተቀበረበት አንሥተው እንደገና ለአዲስ ሕይወት ያበቁት እንዲሁም በቀጣዩ ዘመን ለዐማራ ማኅበረሰብ በአቋራኝ የችግር ቀለበት (vicious circle) ውስጥ እንዲገባ የፖለቲካ ፈንጅ ያጠመዱት ሻቢያና ህወሓት ናቸው።

ለማንኛውም መሐፉን ከስር አስቀምጬዋለሁ። እንግሊዘኛውንና ደበበ እሸቱ የተረጎመውን አማርኛውን። ከሁለት አንዱን አውርዳችሁ አንብቡት። ዛሬ የእረፍት ቀን ስለሆነ እስከማታ ትጨርሱታላችሁ ገፁ ትንሽ ነው።

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut
14.5K viewsTadele Tibebu, edited  08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 21:43:48
6.6K viewsTadele Tibebu, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 21:43:45 በላይነህ ክንዴ እናመሰግናለን። ትውልድ ድሉንና ነፃነቱን አስጠብቆ መቀጠል የሚችለው ሲማርና ሳይንስ ላይ ተመራምሮ ቴክኖሎጂን ሲታጠቅ ብቻ ነው። በአድዋ ተቀራራቢ ትጥቅ የነበራቸው ኢትዮጵያና ጥሊያን ከ40 አመት በኋላ በማይጨው ጦርነት ጥሊያን ያሸነፈችው ዘመናዊ መሳሪያ ፈብርካ ታጥቃ ስትመጣ፣ ኢትዮጵያውያን 40 ዓመት ሙሉ በነፃነት አልጋቸው ተኝተው እያንቀላፉ ስለነበር ነው። ስለዚህ እውቀትን፣ ተቋምን መሠረት ያደረገ ሥራ ለትውልዱ ትልቅ ውለታ መዋል ነው።እስራኤላውያን ጨርሶ ከመጥፋት የዳኑትና ከዓለም ኃያላን ተርታ የተመደቡት ትውድልድ ላይ፣ ቴክሎጂ ላይ በመሥራታቸው ነው።

አቶ በላይነህ ክንዴ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ አምስት ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን ለባህር ዳር ከተማ እና አከባቢዋ ለማሳካት ያቀዳቸውን ፦

1. አብርሆት በባ/ር (የሕዝብ ቤተ-መጽሐፍት) ግንባታ
2. ባ/ር የብስክሌት ከተማ ፕሮጀክት
3. የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ፓርክ
4. ሞዴል ት/ቤት ግንባታ
5. ጣና የጤና ምርምር ማዕከል ግንባታ

ከፍተኛ ገንዘብ ለመሥጠት ቃል ገብተዋል። አብርሆት በባ/ር (የሕዝብ ቤተ-መጽሐፍት) ግንባታ ሙሉ ወጭውን በመሸፈን አሰርተው ለማስረከብ ቃል መግባተቸውን ተከትሎ ላይበራሪው "በላይነህ ክንዴ ቤተ-መጽሐፍት" ተብሎ እንደሚሰየም ተነግሯል። ይገባዋል


በነገራችን ላይ በላይነህ ክንዴ፦

ማንኩሳ ላይ ከሜድሮክ ጋር አንድ ትልቅ የተሟላ ትምህርት ቤት አሰርቶ አስረክቧል፣

ፍኖተ ሰላም ላይ ዲጅታል ቤተ መፅሃፍት ቤት አሰርቷል፣

ቡሬ እድገት በህብረት ት/ቤት እያስገነባ ነው

እናም እውቀት ላይ እያፈሰሰው ያለው መዋዕለ ንዋይ ሊያስመሰግነው ይገባል።
6.7K viewsTadele Tibebu, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 17:26:01 " በርግጥ የሚያደርጉት ነገር ይኖራል። ጉዳዩ እንደዚህ ነው። ምክንያቱም አፍሪካ የተለየ ነገር ብታደርግ የማረጋግጥላችሁ ነገር በአውሮፓ ውስጥ ላሉ ሁሉ ሰሜን አሜሪካ እና እስያን ጨምሮ ያለን የኑሮ ደረጃ ዝቅ ይላል፤ ይወድቃል። እናም ያ ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል። ማረጋግጥላችሁ ግን ምዕራባውያን የሚመጣውን ነገር እንጋፈጣለን እንጂ በቀላሉ ይህ እንዲሆን አንፈቅድም። ስለዚህ የብዙ ምዕራባውያን ምሁራን ሥራ የሚሆነው አፍሪካውያን የሚያደርጉትን ነገር ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ማሳመን ነው። እናም ድሃ የሆኑት በራሳቸው ጥፋት እንጂ በኛ እንዳልሆነ ማሳየት፤ መንገር። ስለዚህ በአካዳሚክ ተቋማት ውስጥ የምናደርገው ይህን ነው። ዝቅተኛ እድገት እንዲፈጠር ያደረገው መሠረታዊ ኃይል ቅኝ ግዛት መሆኑን እናውቃለን።

"አሁንም አፍሪካ ወደ እንዱስትሪ እንድትሸጋገር እና ማምረት እንድትጀምር አንፈቅድም። ገባችሁ ይህን ለማስቆም ሁሉንም ነገር እናደርጋለን። ይህ እንዳይሆን እንዴት እንደምናደርግ ላሳያችሁ ነው። ስለዚህ ቀደም ባሉት ግዜያት በኮሪያ፣ በጃፓን እና ታይዋን ፈጣን የኢንዱስትሪ ልማት ሂደት ነበረን። ይህ ፈጣን እድገት ከአፍሪካ ጥሬ እቃን በመምጠጥ ዋጋው ጨመረ፣ እነዚያ ሀገራት ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ካጠናቀቁ በኋላ ግን ከሰሃራ በታች ያለው የአፍሪካ እድገት እንደገና መውደቅ ጀመረ። ለዚህም በሰሃራ በታች ያሉ አፍሪካ ሀገሮች ተወቃሽ ሆኑ። አምራቾች ሳይሆኑ የጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች። የዋጋ ምንዛሬ እነዚህን ሀገራት እያፈራረሰ ሲሆን፣ ብዙዎቹ ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ናቸው። ከቅኝ ግዛት በኋላ እነዚህ ሀገሮች ወደኋላ እንዲቀሩ አዲስ አወቃቀር አስፈልጎን ነበር። ከዚህ ውስጥ የመጀመሪያው እርዳታ ነው። እርዳታ እንሰጣለን። እርዳታ ምንድነው? እርዳታ የምንሰጥበት ዋነኛ ምክንያት አፋኝ አገዛዞች ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ነው። ይህ ነው ግልፀኝነት፣ ዲሞክራሲ ከምንላቸው እና ከመሳሰሉ በሬ ወለድ አይነት ጀርባ ያሉን ሴራ። ሁሉም የበሬ ወለደ ነገር ነው። ነገርግን ሌሎች አገሮች ላይ ይሰራል። ብድር እንሰጣለን፤ የሀገሩ መሪዎች ብድሩን ካልተቀበሉ ይገደላሉ። ይህ ልክ እንደ ኢኮኖሚክስ ነው። የኢኮኖሚ ጦርነት ነው። ሀብታሞች በድሆች ላይ ጦርነት ያውጃሉ፣ በየቦታው ይከሰታል፣ ባለፀጎች መንግሥትን ይቆጣጠራሉ ያለ ነገር ነው። የእውነት ዲሞክራሲ አለ ብላችሁ ታምናላችሁ? አስቡት እስቲ ማለቴ ዋናው እድገት ነው። ማነው ድጎማና የገቢ ድጋፍ የሚያደርገው? አውሮፓ...አሜሪካ። በዓለም ላይ የነሱን አርሶአደር ለመደገፍ ትልቅ በጀት ያላቸው አውሮፓ እና አሜሪካ ናቸው። ተመልክቱ እንዴት ጥገኛ እንዳደረግናቸው። ቀጣዩ ዙርም የሚኖረው WTO ያንን ለመከልከል የተነደፈ ነው። ማንኛውም ወደመሰላሉ አናት ላይ እወጣለሁ የሚለውን ለማገድ።"
11.5K viewsTadele Tibebu, 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 17:26:00 እንደ ሄነሪ አፍሪካ ውስጥ የአሜሪካን ጅኦ-ፖለቲካዊ ፍላጎቶች በተሳካ ሁኔታ ለማስፈፅም ኢትዮጵያን ሁሌም ቢሆን በጎሳና በብሔረሰብ ከፋፍሎ እንዲተዳደሩ ማድረግ ዘመን የማይሽረው መመሪያቸው ነው። ለዚህም ነው ምእራባዊያን በተለይም የዘመናችን ኢምፔሪያሊስት ሃገረ አሜሪካ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጀምሮ በኢትዮጵያ ተከስተው ባለፉ አብዮቶችና አንኳር ፖለቲካዊ ክስተቶች፣ የርስበርስ ጦርነቶች፣ በኤርትራ የመገንጠል ጥያቄ፣ በስልሳዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ፣ በታህሳሱ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራና በመሳሰሉት ቀጥተኛና የእጅ አዙር ተሳትፎ ሲያደርጉ የቆዩት። ቅኝ ገዥዎች ፍላጎታቸውን ካለምንም ችግር ለማሳካት ኤርትራ ፣ ትግሬ ፣ ዐማራ ፣ ኦሮሞ እየተባባሉ ዕርስ በርሳቸው ሳይስማሙ እንዲኖሩ ኢትዮጵያን በጎሳና በቋንቋ መከፋፈል፣ ከምንም በላይ ግን የዐማራ ነገድን ለይቶ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ ለማስጠላትና ለማስመታት ሁሉም ነገዶች በአምባገነኑ ዐማራ እየተጨቈኑ እንዳሉ በመስበክ በነጻ አውጭነት ለተደራጁት እንደ ሕወሓት ላሉ ቡድኖች ልዩ ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩት አሁንም ድጋፍ እያደረጉ ያሉት፤ ህወሓትና ኦነግ የኢምፔሪያሊስቶች እጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ (Neo-colonialism) አስፈጻሚ በመሆናቸው ነው።

በ2010 ዓ.ም. የአውሮፓ ፓርላማ አንድ ውሣኔ አሳልፎ ነበር። ውሳኔውም እንዲህ የሚል ነበር፤

"whereas Ethiopia is a highly diverse country in terms of religious beliefs and cultures; whereas some of the largest ethnic communities, particularly the Oromo and the Somali (Ogaden), have been marginalized in favour of the Amhara and the Tigray, with little participation in political representation"

ትርጉም፤ "ኢትዮጵያ በሃይማኖት እና በባህል የተለያየ ማኅበረሰብ የሚኖርባት አገር ሆና፣ ታላቆቹ ነገዶች፤ በተለይም ኦሮሞ እና የኦጋዴን ሶማሊዎች፣ በዐማራውና በትግሬው ወደ ዳር ተገፍተዋል፣ በፖለቲካ ያላቸው የውክልና ተሳትፎ ትንሽ ነው"

ይህ በዐማራው ነገድ ላይ የተሰነዘረ መሠረተ ቢስ ውንጀላ የዐማራውን ነገድ በምዕራባውያን ሳይቀር ጥርስ የተነከሰበት ነገድ መሆኑን በግልጽ ያሳዬ ክስተት ነው። ዐማራው ባለፉት 25 ዓመታት የኦሮሞ እና የሶማሊያ ፖለቲካ ድርጅቶች ከትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር ጋር አብረው፣ በዐማራው ነገድ ላይ የዘር መጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጽመውበታል። ሀብት ንብረቱን ነጥቀውታል። ከፍተኛ የሆነ የሥነ-ልቦና ሰላባ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፍተውበታል። እንደ እንስሳ ታርዷል። ተሰልቧል። በገፍ ለዘመናት ከኖረበት አካባቢ ተባሯል።በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነባራዊ ዕውነታ ይህ ሆኖ እያለ፣ ፓርላማው ያሳለፈው ውሳኔ ዐማራውን ለበለጠ ጥቃት
የሚያግልጠው ከመሆኑም በላይ በኢትዮጵያ ከሚኖሩ ነገዶችና ጎሣዎች ጋር ለሚኖረው የወደፊት ግንኙነት ለማፍረስ የታሰበ ውሳኔ ጭምር ነው። የዐማራው ነገድ በደረሰበት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል፣ ፓርላማው ድምፅ እንኳን ባይሆነው፣ አጥፊ ነው ብሎ መፈረጁ በዐማራ ላይ ያላቸውን የተንኮል አቋም ያሳያል።

የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲ አይ ኤ በ 2000 ዓ ም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ባወጣው አንድ ዶክዩመንት በኢትዮጵያ ያሉ ጎሳዎች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት በዘመነ ወያኔ መጎናጸፋቸውን ገልጾ ስለ መጪው የኢትዮጵያ እጣፈንታ ሲተነብይ በዚህ የሃገሪቱ ፖለቲካዊ አብዮት ጥቅሙ የተነካበት ዐማራ የተባለው ጨቋኝ ነገድ የቀድሞ የበላይነቱን ለማስመለስ በሚያደርገው ጥረት ምክንያትነት ሃገሪቷ እንደምትፈራርስ ያትታል። ነገሩን በጥልቀት ስንመለከተው በራሱ የሚተማመን፣ የሃገሩንና የህዝቡን ጥቅም የሚያስቀድምና ለነሱ ፍላጎት ታዛዥ ያልሆነ እምቢተኛ ስርዓት በየትኛውም ሃገር እንዳይፈጠርና እንዳያብብ በማንኛውም መንገድ ማረጋገጥ ተቀዳሚው ተግባራቸው ያደረጉት ምእራባዊያን ኢምፔሪያሊስቶች የዐማራን ነገድ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የቆመ የሃገሪቱ ጥቅም አስጠባቂ አድርገው የለዩት በመሆኑና የዚህ ነገድ በወሳኝ የሃገሪቱ የስልጣን እርከን ላይ መኖር በቀጠናው ላላቸው ኢምፔሪያሊስት አጀንዳ የማይመች መሆኑን በታሪክ ሂደት ስላመኑበት የዐማራውን ነገድ ኢላማ ያደረጉ ተገንጣይ ሃይሎችን በጉያቸው ሸጉጠው ከመደገፍ በተጨማሪ በዐማራው ላይ ለሚደርሱ ተደጋጋሚ ጉልህ ኢ-ሰብአዊ በደሎች ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸውና ለወያኔ ትግሬ መንግስት እድሜ መርዘም ትልቁን ሚና መጫወታቸው የሚከተሉትን የፀረ-ዐማራ ፖሊሲ ያስረግጥልና።

ነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም. የአሜሪካ ፕሬዚዳንት
ጆ ባይደን የዓለም አቀፉን የሰብዓዊ ድጋፍ ቀን አስመልክቶ አንድ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ፕሬዚዳንቱ በተለያዩ ሀገራት የደረሱ ሰብአዊ ቀውሶችን እና የተፈፁሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ከጠቀሱ በኋላ የተከሰተውን የሰብአዊ ቀውስ ተከትሎ የዕርዳታ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ አስተዳደራቸው 13 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን፣ ዩክሬን፣ አፍጋኒስታን፣ ሶማሊያ፣ ባንግላዴሽ፣ ጆርዳን እና የመንን እንደሀገር በስም ጠቅሰው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ከተናገረ በኋላ፣ ኢትዮጵያን በተመለከተ ግን በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ብቻ በማንሳት አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ያደረሰውን ሰብአዊ ቀውስ እና ግፍ በግዴለሽነት አልፎታል። የአሜሪካ መንግስት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአሜሪካን አለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይዲ)፣ አመንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዪማን ራይትስዎች፣ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት (ሲፒጄ)፣ አይ ፒ አይ፣ ጄኖሳይድዋች፣ አለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት(ቢቢሲ፣ ሲኤንኤ፣ አልጀዚራ) የመሳሰሉት ድርጅቶች ሳይቀር የዐማራ ሕዝብ የመጥፋት ጥላ ወድቆበት፣ በመከራ ጉም ተሸፍኖ፣ ህዝቡ ተበታትኖ፣ ክብሩ ተገፎ በከባድ ፈተና ወድቆ ሲሰቃይና እንደ ጎሽ እየተፈለገ በጥይት ሲታደን፣ ሲፈናቀል፣ ንብረቱን ሲቀማና ሲቃጠል በጉዳዩ ጣልቃ ላለመግባት ጆሮ ዳባ ልበስ የፀረ ዐማራ አመለካከቱ በምእራባዊያን ዘንድ ምን ያህል ስር እንደሰደደ ትልቅ አስረጅ ክስተት ነው።

ከዚህ በታች ያለውን ቪዲዮ በጥሞና አዳምጡ። ከቪዲዮው የተወሰነው ትርጉም የሚከተለው ነው፣


"ከሰሃራ በታች ያሉ አፍሪካ ለላቁ ሀገራትአለም አቀፋዊ ብልጽግና መሰረታዊ ሆነዋል እናም ለዚህ አፍሪካ ምትጫወተው ሚና ነበራት። የጥሬ ዕቃ አምራችነት ሚና አላት። ሰብሰሃራን አፍሪካ ከዚህ ሚና ከፍ እንዲሉ አንፈቅድም። አፍሪካ ባለችበት ድህነት መኖሯን እንድትቀጥል ሁሉንም ነገር እናደርጋለን። ይህ ለእያንዳንዳችን ብልፅግና በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ማለት ሁሉም የኢኮኖሚ መዋቅሮች፣ ሁሉም አለምአቀፍ ተቋማት አና ለሁሉም ሰው የምናስተምረው ኢኮኖሚክስ አፍሪካ ባለችበት ድህነት እንድትቆይ ታስቦ የተነደፈ ነው፤ እናም አውሮፓም ሆነ አሜሪካ ወይም አሁን ቻይና ተመሳሳይ ነገር ነው ምንፈልገው አፍሪካ በድህነት መኖሯን እንድትቀጥል ምክንያቱም እነዚያ ጥሬ ዕቃዎች ያስፈልጉናል። ያውም በወረደና በርካሽ ዋጋ። ገባችሁ ይህ ነው ዓላማው። እንደዛ ስንል ግን አፍሪካ ምንም ልታደርግ አትችልም ማለት አይደለም።
9.9K viewsTadele Tibebu, 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 17:26:00 ምዕራባውያን የአፍሪካን ቀንድና የቀይ ባሕርን የኢኮኖሚና የፖለቲካ ስትራቴጂ አካባቢ ለመቆጣጠር በአፍሪካ የመግቢያ በር ላይ የተቀመጡት ከቀጠናው በቅድሚያ ማጥፋት በቀዳሚነት የያዙት አጀንዳቸው እነዚህን ነበር።

1. የአንድነት ምልክት የሆነው ዘውድ፣
2. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና
3.ላገሩ ቀናዒ የሆነው የዐማራ ማኅበረሰብ

ስለሆነም የኢትዮጵያን ጥሬ ሀብት ለመበዝበዝ እና ቅኝ ገዥነታቸውን ለማረጋገጥ በቅድሚያ እነዚህን ተቋሞች መፋራረስ እንዳለባቸው አመኑ። ምክንያቱም ዘውዱ የኢትዮጵያን ሕዝብ በአንድነቱ የሚያስተሳሥር ምልክት ነው ተብሎ በምዕራባውያን ዘንድ ተፈርጇል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ቅዱስ ጊዮርጊስን ከመንበሩ አስነስታ ወደ ዓድዋ ያዘመተች፣ ለኢትዮጵያ ህልውና፤ ስለነፃነትና ስለሰው ልጅ ክብር የምታስተምር፤ በግንባር ቀደምትነት የምትቀሰቅስና የምትመራ ናት ተብላ
በዘንዶ ዐይናቸው ውስጥ ገባች። በሦስተኛ ደረጃ ጥርስ የተነከሰበት በመንግስት ምስረታው፣ በፖለቲካ አመራሩና በድንበር ጥበቃው ተግባር ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ ሲያደርግ የኖረው የዐማራው ሕዝብ ነው። ለዚህ ምክንያት የሆነውን ደግሞ ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ታህሳስ 11 ቀን 1985 ዓ.ም. በደብረ ብርሃን ከተማ መዐሕድ በጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ታሪካዊ ንግግር እንዲህ አስረድተውናል፣

" ሦስተኛ እንዲጠፋ የተወሰነበት የዐማራው ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያ ጠላቶች አባባል በራሱና በታሪኩ የሚተማመን አትንኩኝ ባይ፣ ለነፃነቱና ለህልውናው ከምንም በላይ ለሃይማኖቱ እና ለሐገሩ ዳርድንበር መከበር የሚሞት በመሆኑ ነበር፡፡ ይህም ሕዝብ በታሪክ ውስጥ በገሃድ እንደሚታየው በማናቸውም ጊዜ ቢሆን ለውጭ ኃይልና ለውጭ ጠላት ለሐገሩ መዋረድና መደፈር መሳሪያ ሆኖ የማያውቅና የማይደለል ከመሆኑም በላይ በሐገሩና በሃይማኖቱ ጉዳይ ዐማራው አክራሪ ነው በመባሉ ነው፡፡ ዐማራን ማጥፋትም ለየት ያለና ራሱን የቻለ ሥልት የተቀየሰ ሲሆን፣ ዐማራው በጣላቱ ፊት ተባብሮ እንዳይቆም ለማድረግ በስም ከፋፍለው በተለይ የሸዋ ዐማራ ከምድረገጽ እንዲጠፋ ካልተደረገ በቀር
የጣሊያ ወረራ ጊዜያዊ ድል ከመሆኑ ባሻገር ሐገሪቱን በቅኝ ግዛትነት ለመያዝ አንችልም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰው በዚህ ዕቅድ ለመግፋት እንደወሰኑ በታሪክ የተረጋገጠ ነው፡፡"
(ምጽአተ ዐማራ፣ 526)

በተጨማሪም፣ በቅርቡ የጎንደር ዩኒቨርስቲ በወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት የተፈጸመውን ወረራና መዋቅራዊ ዘር ማጥፋት የምርምር ውጤት ይፋ ባደረገው መጽሐፉ እንዲህ ይላል፣

"ኢትዮጵያዊያን ለሉዓላዊነታቸው የሚሰጡት ትኩረት እንዲሁም ለሀገር ዳር ድንበር ሲሉ በኢትዮጵያ ጠላቶች ላይ ያስመዘገቧቸው አንጸባራቂ ድሎች በአለም ላይ ወዳጅ ያፈሩትን ያክል፣ ጥቂት የማይባሉ ጠላቶችንም ፈጥረዋል፡፡ እነዚህ ጠላቶች በሁለት መልኩ ኢትዮጵያ ላይ ክስ ያቀርባሉ፡፡ አንደኛ ኢትዮጵያ የራሷን ሀብት የውጭ ሀይሎች እንዳሻቸዉ ገብተው እንዲዘርፉና ወደ አገራቸው እንዲያግዙ አለመፍቀዷ ሲሆን፤ ሁለተኛ ደግሞ ቅኝ ገዥዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአድዋ ጦርነት ላይ ማንበርከኳ ለመላ ጥቁሮች የነጻነት ትግል እንዲቀጣጠል፣ በአፍሪካና ላቲን አሜሪካ አህጉሮች ውስጥ በቅኝ ተገዢነት ሲሰቃዩ የነበሩ ሕዝቦች ቅኝ ገዢን ማሸነፍ ይቻላል የሚለውን ስሜት መፍጠሩ ነው፡፡ እነዚህ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማንበርከክ ዋናው ዋልታና ማገር ሆኖ አገሪቷን የያዛት የትኛው ሕዝብ እንደሆነ ቀድመው መረጃ በመሰብሰብ፣ ጥናት በማድረግ፤ 'ኢትዮጵያን ማሸነፍ ወይም መበተን ከሚቻልባቸው መንገዶች አንዱ የአማራን ሕዝብ በማጥፋት ወይም በማዳከም ነው' የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ጠላቶች የዐማራን ሕዝብ ለማጥፋት ወይም ለማዳከም የተለያዩ ስልቶችን ነድፈው ተንቀሳቅሰዋል፡፡" (ጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ 1)

ኢምፔሪያሊስቶች ዐማራ የሚባል ታላቅ የሃገር ጉልላት ማፍረስ የፈለጉበት ምክንያት ከላይ እንደተገለጸው ዐማራ አገር ወዳድ፣ ለማንም የማይበረከክ፣ የአገሪቱን ሀብት የማያስነካ፣ በራሱ ባህልና ታሪክ የሚመካ እና ዐድዋ ላይ የአውሮፓን ቅኝ ገዥ ኃይል ቅስም ሰብሮ የመለሰ
ምርጥ አርበኛ ሕዝብ በመሆኑ በዘንዶ አይናቸው ውስጥ እንዲገባ አድርጓታል።


የአሜሪካ ሴኔት “የዐማራ ነገድ ጨቋኝ፣ ፀረ-ምዕራባዊያን አመለካከት ያለውና የአውሮፓውያንን ክብር ያሳጣ" ብሎ ያምናል። ይህ ፀረ- ዐማራ አመለካከት አብዛኞቹ ምእራባዊያን ፖለቲከኞች የሚጋሩት ነው። ለዚህ ምክንያት ደግሞ ኢትዮጵያ ጂኦ-ፖለቲካሊ እስትራቴጂክ ሃገር በመሆኗ ነው።

ዚቢነው ብሬጅንስኪ፤ የአሜሪካ የደህንነት አማካሪ፤ ሶቭየቶችን በመጥላት፤ ለሶቭየቶች አጎብዳጅ የሆኑትን፤ “ኩባን፤ አንጎላን፤ ኢትዮጵያን፤ ወዘተ ማድከም አለብን ብሎ ነበር። (ድርጅታዊ ምዝበራ፣ 56) በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ታሪክ ውስጥ ከዝነኞቹ ቀዳሚው ዶክተር ሄንሪ ኪሲንጀር ነው፡፡ ሰውየው በፕሬዚዳንት ሪቻርድ ኒክሰን እና ጄራርድ ፎርድ ዘመን የአሜሪካ መንግስት የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆኖ የሰራ ሲሆን በ1960'ዎቹ "ቀይ ባህር ለጦር ሥልት ያለው ጥቅም" የሚል ለአሜሪካ መንግሥት ጥናቱን አቅርቦ ነበር።

"ኢትዮጵያ ሰላም ካገኘች ሕዝቧ ሠራተኛና ታታሪ ስለሆነ፣ በዓለም ብድር ዕዳም እንደ ሌሎቹ የሦስተኛ ዓለም አገሮች ተዘፍቃ የማታውቅና የኮራች አገር በመሆኗ አንድ ቀን ራሷን የቻለች አገር ትሆናለች፡፡ ዕድል አግኝታ በዘመናዊ ሥልጣኔ ብትገፋ ደግሞ የምትቻል አገር አይደለችም፡፡ ስለዚህ ከንጉሥ ኃይለ ሥላሴ በኋላ ኢትዮጵያን የሚመራ መንግሥት ሰላም እንዳያገኝ፣ አገሪቱም እንደ ዓረብ አገሮች ተከፋፍላና ተነጣጥላ መበታተን አለባት፡፡ ለወደፊት በቀይ ባህር አሜሪካ የምትጫወተው ሚና እንዳይመነምን፣ መደናቀፍ ከሚገባቸው በቀይ ባህር አዋሳኝ ካሉ ታዳጊ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆን አለባት፡፡

"የቀይ ባህር ወተት የሆነውን የዓረብን ነዳጅ በነፃ ያለ ቀረጥ ማለብ የምንችለው መንግሥታችን ኢትዮጵያን ከጎረቤቷ ከሱማሊያ ጋር ብቻ ሳይሆን፣ ክፍለ ሀገሮቿን ራሳቸውን በሰሜንና በደቡብ ከፋፍሎ፣ የደከመውን ወገን በመርዳት ያላመፀውን ጎሳ በመነሳሳት፣ በዳር ድንበሯ ዘለዓለም ሁከትና ጦርነት እንዳይለያት በማድረግ ፀረ መንግሥት ተዋጊዎችን በሲአይኤ በማደራጀት ሰላም መንሳት ያስፈልጋል፡፡

"የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንካራና ብርቱ ቢሆንም ቅሉ፣ በሥልጣን ፍላጎቱ ደካማ ጎን አለው፡፡ አንዱ በሌላው ላይ መንገሥ ዋና ምኞቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያን በታሪካቸው ዴሞክራሲያዊ መንግሥት መሥርተው አያውቁም፡፡ ከጥንት ጀምሮ ቢሆን አንዱ ንጉሥ ሌላውን በመግደል ሥልጣን መቀማማትና ማመፅ ባህላቸው፣ ልማዳቸውና ታሪካቸውም ነውና፡፡ እኛ ያሳደግነው ውሻም ቢሆን ሊነክሰን ቢሞክር የመንግሥት ግልበጣ በማካሄድ፣ ለአንዲት ዘመን እንኳ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሰላም መኖር የለበትም፡፡ ሰሜናዊና ደቡባዊ፣ እንዲሁም ኤርትራ፣ ትግሬ፣ ዐማራ፣ ኦሮሞ እየተባባሉ እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ለረዥም ጊዜ ከኖሩ፣ ቀይ ባህር ለአሜሪካ መንግሥት ጠቃሚ በር ሆኖ ይኖራል፡፡"
(ሪፖርተር፣ ታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም.)
10.9K viewsTadele Tibebu, 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 20:45:35 የነዚህ ጥቁር ሂትለራዊያንን ድርጊት ተመልከቱ
17.5K viewsTadele Tibebu, 17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ