Get Mystery Box with random crypto!

በምዕራብ ጎጃም፤ ሰሜን አቸፈር ወረዳ ሊበን ከተማ የሆነው ነገር እጅግ በጣም ልብ ይሰብራል፣ በፎቶ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

በምዕራብ ጎጃም፤ ሰሜን አቸፈር ወረዳ ሊበን ከተማ የሆነው ነገር እጅግ በጣም ልብ ይሰብራል፣ በፎቶ የምትመከቱት ልጅ ህይወቱ አልፏል። መብራትና ውሃ ለጠየቀ ማኅበረሰብ ጥይት አይገባውም ነበር። ነገርግን በሰላማዊ መንገድ ለጠየቀው መልስ በጉቦ (Bribery)፣ በሥልጣን መባለግ (Abuse of power)፣ በስርቆትና ዘረፋ (Embezzlement)፣ በጥቅም ተካፋይነት (kickbacks) የተጨማለቁ የወረዳው አመራሮች ምላሽ በጥይት አርከፍክፎ መግደል ሆኗል። የወረዳው የፀጥታ አባል በወሰዱት እርምጃ ሦስት ልጆቹን ማለትም ወጣት ኤርሚያስ አብየ፣ ወጣት ዳኛቸው አዲስን እና ወጣት ቸርነትን ተኩሶ አቁስሏል። ከእነዚህ መካከል በፎቶ የምትመለከቱት የ16 ዓመት ወጣት ኤርምያስ አብየ በጥበብ ጊዮን ሆስፒታል ሲረዳ ቢቆይም ዛሬ ሕይወቱ አልፏል።

በጣም የሚያሳዝነው 460 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የሚያመነጨው ጣና በለስ የሚገኘው በዚሁ ወረዳ ቁንዝላ ከተማ አካባቢ ነው። ነገርግን ከቁንዝላ ጀምሮ፣ ሳንክራ፣ ደንቦላ፣ ሊበን፣ ይስማላ፣ ዲላሞ፣ ዱርቤቴ እንዲሁም ጭንባና ሻሁራ እንደ ኦሪት ዘመን በጨለማ የሚኖር ማኅበረሰብ ነው። በዚህ የተበሳጨው ማኅበረሰብ በግልፅ ወደ አደባባይ ወጥቶ “ሻማ በቃን! አቸፈር ጨልሞ ሱዳን አይበራም!” የሚል ግልጽ መልእክት ስላስተላለፉ በጥይት ተረሽነዋል። አሁን ለወረዳው የምናስተላልፈው ግልጽ መልእክት አለ። ይሄን ህገ ወጥ ተግባር የፈፀሙ የፖሊስ አባል በህግ ፊት መቅረብ አለባቸው። የተቋረጠው መብራትም በአስቸኳይ እንዲስተካከል እንጠይቃለን።