Get Mystery Box with random crypto!

' በርግጥ የሚያደርጉት ነገር ይኖራል። ጉዳዩ እንደዚህ ነው። ምክንያቱም አፍሪካ የተለየ ነገር ብታ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

" በርግጥ የሚያደርጉት ነገር ይኖራል። ጉዳዩ እንደዚህ ነው። ምክንያቱም አፍሪካ የተለየ ነገር ብታደርግ የማረጋግጥላችሁ ነገር በአውሮፓ ውስጥ ላሉ ሁሉ ሰሜን አሜሪካ እና እስያን ጨምሮ ያለን የኑሮ ደረጃ ዝቅ ይላል፤ ይወድቃል። እናም ያ ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል። ማረጋግጥላችሁ ግን ምዕራባውያን የሚመጣውን ነገር እንጋፈጣለን እንጂ በቀላሉ ይህ እንዲሆን አንፈቅድም። ስለዚህ የብዙ ምዕራባውያን ምሁራን ሥራ የሚሆነው አፍሪካውያን የሚያደርጉትን ነገር ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ማሳመን ነው። እናም ድሃ የሆኑት በራሳቸው ጥፋት እንጂ በኛ እንዳልሆነ ማሳየት፤ መንገር። ስለዚህ በአካዳሚክ ተቋማት ውስጥ የምናደርገው ይህን ነው። ዝቅተኛ እድገት እንዲፈጠር ያደረገው መሠረታዊ ኃይል ቅኝ ግዛት መሆኑን እናውቃለን።

"አሁንም አፍሪካ ወደ እንዱስትሪ እንድትሸጋገር እና ማምረት እንድትጀምር አንፈቅድም። ገባችሁ ይህን ለማስቆም ሁሉንም ነገር እናደርጋለን። ይህ እንዳይሆን እንዴት እንደምናደርግ ላሳያችሁ ነው። ስለዚህ ቀደም ባሉት ግዜያት በኮሪያ፣ በጃፓን እና ታይዋን ፈጣን የኢንዱስትሪ ልማት ሂደት ነበረን። ይህ ፈጣን እድገት ከአፍሪካ ጥሬ እቃን በመምጠጥ ዋጋው ጨመረ፣ እነዚያ ሀገራት ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ካጠናቀቁ በኋላ ግን ከሰሃራ በታች ያለው የአፍሪካ እድገት እንደገና መውደቅ ጀመረ። ለዚህም በሰሃራ በታች ያሉ አፍሪካ ሀገሮች ተወቃሽ ሆኑ። አምራቾች ሳይሆኑ የጥሬ ዕቃ አቅራቢዎች። የዋጋ ምንዛሬ እነዚህን ሀገራት እያፈራረሰ ሲሆን፣ ብዙዎቹ ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ናቸው። ከቅኝ ግዛት በኋላ እነዚህ ሀገሮች ወደኋላ እንዲቀሩ አዲስ አወቃቀር አስፈልጎን ነበር። ከዚህ ውስጥ የመጀመሪያው እርዳታ ነው። እርዳታ እንሰጣለን። እርዳታ ምንድነው? እርዳታ የምንሰጥበት ዋነኛ ምክንያት አፋኝ አገዛዞች ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ነው። ይህ ነው ግልፀኝነት፣ ዲሞክራሲ ከምንላቸው እና ከመሳሰሉ በሬ ወለድ አይነት ጀርባ ያሉን ሴራ። ሁሉም የበሬ ወለደ ነገር ነው። ነገርግን ሌሎች አገሮች ላይ ይሰራል። ብድር እንሰጣለን፤ የሀገሩ መሪዎች ብድሩን ካልተቀበሉ ይገደላሉ። ይህ ልክ እንደ ኢኮኖሚክስ ነው። የኢኮኖሚ ጦርነት ነው። ሀብታሞች በድሆች ላይ ጦርነት ያውጃሉ፣ በየቦታው ይከሰታል፣ ባለፀጎች መንግሥትን ይቆጣጠራሉ ያለ ነገር ነው። የእውነት ዲሞክራሲ አለ ብላችሁ ታምናላችሁ? አስቡት እስቲ ማለቴ ዋናው እድገት ነው። ማነው ድጎማና የገቢ ድጋፍ የሚያደርገው? አውሮፓ...አሜሪካ። በዓለም ላይ የነሱን አርሶአደር ለመደገፍ ትልቅ በጀት ያላቸው አውሮፓ እና አሜሪካ ናቸው። ተመልክቱ እንዴት ጥገኛ እንዳደረግናቸው። ቀጣዩ ዙርም የሚኖረው WTO ያንን ለመከልከል የተነደፈ ነው። ማንኛውም ወደመሰላሉ አናት ላይ እወጣለሁ የሚለውን ለማገድ።"