Get Mystery Box with random crypto!

በላይነህ ክንዴ እናመሰግናለን። ትውልድ ድሉንና ነፃነቱን አስጠብቆ መቀጠል የሚችለው ሲማርና ሳይንስ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

በላይነህ ክንዴ እናመሰግናለን። ትውልድ ድሉንና ነፃነቱን አስጠብቆ መቀጠል የሚችለው ሲማርና ሳይንስ ላይ ተመራምሮ ቴክኖሎጂን ሲታጠቅ ብቻ ነው። በአድዋ ተቀራራቢ ትጥቅ የነበራቸው ኢትዮጵያና ጥሊያን ከ40 አመት በኋላ በማይጨው ጦርነት ጥሊያን ያሸነፈችው ዘመናዊ መሳሪያ ፈብርካ ታጥቃ ስትመጣ፣ ኢትዮጵያውያን 40 ዓመት ሙሉ በነፃነት አልጋቸው ተኝተው እያንቀላፉ ስለነበር ነው። ስለዚህ እውቀትን፣ ተቋምን መሠረት ያደረገ ሥራ ለትውልዱ ትልቅ ውለታ መዋል ነው።እስራኤላውያን ጨርሶ ከመጥፋት የዳኑትና ከዓለም ኃያላን ተርታ የተመደቡት ትውድልድ ላይ፣ ቴክሎጂ ላይ በመሥራታቸው ነው።

አቶ በላይነህ ክንዴ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ አምስት ዋና ዋና ፕሮጀክቶችን ለባህር ዳር ከተማ እና አከባቢዋ ለማሳካት ያቀዳቸውን ፦

1. አብርሆት በባ/ር (የሕዝብ ቤተ-መጽሐፍት) ግንባታ
2. ባ/ር የብስክሌት ከተማ ፕሮጀክት
3. የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ፓርክ
4. ሞዴል ት/ቤት ግንባታ
5. ጣና የጤና ምርምር ማዕከል ግንባታ

ከፍተኛ ገንዘብ ለመሥጠት ቃል ገብተዋል። አብርሆት በባ/ር (የሕዝብ ቤተ-መጽሐፍት) ግንባታ ሙሉ ወጭውን በመሸፈን አሰርተው ለማስረከብ ቃል መግባተቸውን ተከትሎ ላይበራሪው "በላይነህ ክንዴ ቤተ-መጽሐፍት" ተብሎ እንደሚሰየም ተነግሯል። ይገባዋል


በነገራችን ላይ በላይነህ ክንዴ፦

ማንኩሳ ላይ ከሜድሮክ ጋር አንድ ትልቅ የተሟላ ትምህርት ቤት አሰርቶ አስረክቧል፣

ፍኖተ ሰላም ላይ ዲጅታል ቤተ መፅሃፍት ቤት አሰርቷል፣

ቡሬ እድገት በህብረት ት/ቤት እያስገነባ ነው

እናም እውቀት ላይ እያፈሰሰው ያለው መዋዕለ ንዋይ ሊያስመሰግነው ይገባል።