Get Mystery Box with random crypto!

እንደ ሄነሪ አፍሪካ ውስጥ የአሜሪካን ጅኦ-ፖለቲካዊ ፍላጎቶች በተሳካ ሁኔታ ለማስፈፅም ኢትዮጵያን | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

እንደ ሄነሪ አፍሪካ ውስጥ የአሜሪካን ጅኦ-ፖለቲካዊ ፍላጎቶች በተሳካ ሁኔታ ለማስፈፅም ኢትዮጵያን ሁሌም ቢሆን በጎሳና በብሔረሰብ ከፋፍሎ እንዲተዳደሩ ማድረግ ዘመን የማይሽረው መመሪያቸው ነው። ለዚህም ነው ምእራባዊያን በተለይም የዘመናችን ኢምፔሪያሊስት ሃገረ አሜሪካ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ጀምሮ በኢትዮጵያ ተከስተው ባለፉ አብዮቶችና አንኳር ፖለቲካዊ ክስተቶች፣ የርስበርስ ጦርነቶች፣ በኤርትራ የመገንጠል ጥያቄ፣ በስልሳዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ፣ በታህሳሱ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራና በመሳሰሉት ቀጥተኛና የእጅ አዙር ተሳትፎ ሲያደርጉ የቆዩት። ቅኝ ገዥዎች ፍላጎታቸውን ካለምንም ችግር ለማሳካት ኤርትራ ፣ ትግሬ ፣ ዐማራ ፣ ኦሮሞ እየተባባሉ ዕርስ በርሳቸው ሳይስማሙ እንዲኖሩ ኢትዮጵያን በጎሳና በቋንቋ መከፋፈል፣ ከምንም በላይ ግን የዐማራ ነገድን ለይቶ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ ለማስጠላትና ለማስመታት ሁሉም ነገዶች በአምባገነኑ ዐማራ እየተጨቈኑ እንዳሉ በመስበክ በነጻ አውጭነት ለተደራጁት እንደ ሕወሓት ላሉ ቡድኖች ልዩ ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩት አሁንም ድጋፍ እያደረጉ ያሉት፤ ህወሓትና ኦነግ የኢምፔሪያሊስቶች እጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ (Neo-colonialism) አስፈጻሚ በመሆናቸው ነው።

በ2010 ዓ.ም. የአውሮፓ ፓርላማ አንድ ውሣኔ አሳልፎ ነበር። ውሳኔውም እንዲህ የሚል ነበር፤

"whereas Ethiopia is a highly diverse country in terms of religious beliefs and cultures; whereas some of the largest ethnic communities, particularly the Oromo and the Somali (Ogaden), have been marginalized in favour of the Amhara and the Tigray, with little participation in political representation"

ትርጉም፤ "ኢትዮጵያ በሃይማኖት እና በባህል የተለያየ ማኅበረሰብ የሚኖርባት አገር ሆና፣ ታላቆቹ ነገዶች፤ በተለይም ኦሮሞ እና የኦጋዴን ሶማሊዎች፣ በዐማራውና በትግሬው ወደ ዳር ተገፍተዋል፣ በፖለቲካ ያላቸው የውክልና ተሳትፎ ትንሽ ነው"

ይህ በዐማራው ነገድ ላይ የተሰነዘረ መሠረተ ቢስ ውንጀላ የዐማራውን ነገድ በምዕራባውያን ሳይቀር ጥርስ የተነከሰበት ነገድ መሆኑን በግልጽ ያሳዬ ክስተት ነው። ዐማራው ባለፉት 25 ዓመታት የኦሮሞ እና የሶማሊያ ፖለቲካ ድርጅቶች ከትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር ጋር አብረው፣ በዐማራው ነገድ ላይ የዘር መጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጽመውበታል። ሀብት ንብረቱን ነጥቀውታል። ከፍተኛ የሆነ የሥነ-ልቦና ሰላባ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፍተውበታል። እንደ እንስሳ ታርዷል። ተሰልቧል። በገፍ ለዘመናት ከኖረበት አካባቢ ተባሯል።በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነባራዊ ዕውነታ ይህ ሆኖ እያለ፣ ፓርላማው ያሳለፈው ውሳኔ ዐማራውን ለበለጠ ጥቃት
የሚያግልጠው ከመሆኑም በላይ በኢትዮጵያ ከሚኖሩ ነገዶችና ጎሣዎች ጋር ለሚኖረው የወደፊት ግንኙነት ለማፍረስ የታሰበ ውሳኔ ጭምር ነው። የዐማራው ነገድ በደረሰበት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል፣ ፓርላማው ድምፅ እንኳን ባይሆነው፣ አጥፊ ነው ብሎ መፈረጁ በዐማራ ላይ ያላቸውን የተንኮል አቋም ያሳያል።

የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲ አይ ኤ በ 2000 ዓ ም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ባወጣው አንድ ዶክዩመንት በኢትዮጵያ ያሉ ጎሳዎች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት በዘመነ ወያኔ መጎናጸፋቸውን ገልጾ ስለ መጪው የኢትዮጵያ እጣፈንታ ሲተነብይ በዚህ የሃገሪቱ ፖለቲካዊ አብዮት ጥቅሙ የተነካበት ዐማራ የተባለው ጨቋኝ ነገድ የቀድሞ የበላይነቱን ለማስመለስ በሚያደርገው ጥረት ምክንያትነት ሃገሪቷ እንደምትፈራርስ ያትታል። ነገሩን በጥልቀት ስንመለከተው በራሱ የሚተማመን፣ የሃገሩንና የህዝቡን ጥቅም የሚያስቀድምና ለነሱ ፍላጎት ታዛዥ ያልሆነ እምቢተኛ ስርዓት በየትኛውም ሃገር እንዳይፈጠርና እንዳያብብ በማንኛውም መንገድ ማረጋገጥ ተቀዳሚው ተግባራቸው ያደረጉት ምእራባዊያን ኢምፔሪያሊስቶች የዐማራን ነገድ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የቆመ የሃገሪቱ ጥቅም አስጠባቂ አድርገው የለዩት በመሆኑና የዚህ ነገድ በወሳኝ የሃገሪቱ የስልጣን እርከን ላይ መኖር በቀጠናው ላላቸው ኢምፔሪያሊስት አጀንዳ የማይመች መሆኑን በታሪክ ሂደት ስላመኑበት የዐማራውን ነገድ ኢላማ ያደረጉ ተገንጣይ ሃይሎችን በጉያቸው ሸጉጠው ከመደገፍ በተጨማሪ በዐማራው ላይ ለሚደርሱ ተደጋጋሚ ጉልህ ኢ-ሰብአዊ በደሎች ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸውና ለወያኔ ትግሬ መንግስት እድሜ መርዘም ትልቁን ሚና መጫወታቸው የሚከተሉትን የፀረ-ዐማራ ፖሊሲ ያስረግጥልና።

ነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም. የአሜሪካ ፕሬዚዳንት
ጆ ባይደን የዓለም አቀፉን የሰብዓዊ ድጋፍ ቀን አስመልክቶ አንድ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ፕሬዚዳንቱ በተለያዩ ሀገራት የደረሱ ሰብአዊ ቀውሶችን እና የተፈፁሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ከጠቀሱ በኋላ የተከሰተውን የሰብአዊ ቀውስ ተከትሎ የዕርዳታ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ አስተዳደራቸው 13 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን፣ ዩክሬን፣ አፍጋኒስታን፣ ሶማሊያ፣ ባንግላዴሽ፣ ጆርዳን እና የመንን እንደሀገር በስም ጠቅሰው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ከተናገረ በኋላ፣ ኢትዮጵያን በተመለከተ ግን በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ብቻ በማንሳት አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ያደረሰውን ሰብአዊ ቀውስ እና ግፍ በግዴለሽነት አልፎታል። የአሜሪካ መንግስት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአሜሪካን አለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይዲ)፣ አመንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዪማን ራይትስዎች፣ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት (ሲፒጄ)፣ አይ ፒ አይ፣ ጄኖሳይድዋች፣ አለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት(ቢቢሲ፣ ሲኤንኤ፣ አልጀዚራ) የመሳሰሉት ድርጅቶች ሳይቀር የዐማራ ሕዝብ የመጥፋት ጥላ ወድቆበት፣ በመከራ ጉም ተሸፍኖ፣ ህዝቡ ተበታትኖ፣ ክብሩ ተገፎ በከባድ ፈተና ወድቆ ሲሰቃይና እንደ ጎሽ እየተፈለገ በጥይት ሲታደን፣ ሲፈናቀል፣ ንብረቱን ሲቀማና ሲቃጠል በጉዳዩ ጣልቃ ላለመግባት ጆሮ ዳባ ልበስ የፀረ ዐማራ አመለካከቱ በምእራባዊያን ዘንድ ምን ያህል ስር እንደሰደደ ትልቅ አስረጅ ክስተት ነው።

ከዚህ በታች ያለውን ቪዲዮ በጥሞና አዳምጡ። ከቪዲዮው የተወሰነው ትርጉም የሚከተለው ነው፣


"ከሰሃራ በታች ያሉ አፍሪካ ለላቁ ሀገራትአለም አቀፋዊ ብልጽግና መሰረታዊ ሆነዋል እናም ለዚህ አፍሪካ ምትጫወተው ሚና ነበራት። የጥሬ ዕቃ አምራችነት ሚና አላት። ሰብሰሃራን አፍሪካ ከዚህ ሚና ከፍ እንዲሉ አንፈቅድም። አፍሪካ ባለችበት ድህነት መኖሯን እንድትቀጥል ሁሉንም ነገር እናደርጋለን። ይህ ለእያንዳንዳችን ብልፅግና በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ማለት ሁሉም የኢኮኖሚ መዋቅሮች፣ ሁሉም አለምአቀፍ ተቋማት አና ለሁሉም ሰው የምናስተምረው ኢኮኖሚክስ አፍሪካ ባለችበት ድህነት እንድትቆይ ታስቦ የተነደፈ ነው፤ እናም አውሮፓም ሆነ አሜሪካ ወይም አሁን ቻይና ተመሳሳይ ነገር ነው ምንፈልገው አፍሪካ በድህነት መኖሯን እንድትቀጥል ምክንያቱም እነዚያ ጥሬ ዕቃዎች ያስፈልጉናል። ያውም በወረደና በርካሽ ዋጋ። ገባችሁ ይህ ነው ዓላማው። እንደዛ ስንል ግን አፍሪካ ምንም ልታደርግ አትችልም ማለት አይደለም።