Get Mystery Box with random crypto!

ምዕራባውያን የአፍሪካን ቀንድና የቀይ ባሕርን የኢኮኖሚና የፖለቲካ ስትራቴጂ አካባቢ ለመቆጣጠር በአ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

ምዕራባውያን የአፍሪካን ቀንድና የቀይ ባሕርን የኢኮኖሚና የፖለቲካ ስትራቴጂ አካባቢ ለመቆጣጠር በአፍሪካ የመግቢያ በር ላይ የተቀመጡት ከቀጠናው በቅድሚያ ማጥፋት በቀዳሚነት የያዙት አጀንዳቸው እነዚህን ነበር።

1. የአንድነት ምልክት የሆነው ዘውድ፣
2. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና
3.ላገሩ ቀናዒ የሆነው የዐማራ ማኅበረሰብ

ስለሆነም የኢትዮጵያን ጥሬ ሀብት ለመበዝበዝ እና ቅኝ ገዥነታቸውን ለማረጋገጥ በቅድሚያ እነዚህን ተቋሞች መፋራረስ እንዳለባቸው አመኑ። ምክንያቱም ዘውዱ የኢትዮጵያን ሕዝብ በአንድነቱ የሚያስተሳሥር ምልክት ነው ተብሎ በምዕራባውያን ዘንድ ተፈርጇል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ቅዱስ ጊዮርጊስን ከመንበሩ አስነስታ ወደ ዓድዋ ያዘመተች፣ ለኢትዮጵያ ህልውና፤ ስለነፃነትና ስለሰው ልጅ ክብር የምታስተምር፤ በግንባር ቀደምትነት የምትቀሰቅስና የምትመራ ናት ተብላ
በዘንዶ ዐይናቸው ውስጥ ገባች። በሦስተኛ ደረጃ ጥርስ የተነከሰበት በመንግስት ምስረታው፣ በፖለቲካ አመራሩና በድንበር ጥበቃው ተግባር ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ ሲያደርግ የኖረው የዐማራው ሕዝብ ነው። ለዚህ ምክንያት የሆነውን ደግሞ ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ታህሳስ 11 ቀን 1985 ዓ.ም. በደብረ ብርሃን ከተማ መዐሕድ በጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ታሪካዊ ንግግር እንዲህ አስረድተውናል፣

" ሦስተኛ እንዲጠፋ የተወሰነበት የዐማራው ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያ ጠላቶች አባባል በራሱና በታሪኩ የሚተማመን አትንኩኝ ባይ፣ ለነፃነቱና ለህልውናው ከምንም በላይ ለሃይማኖቱ እና ለሐገሩ ዳርድንበር መከበር የሚሞት በመሆኑ ነበር፡፡ ይህም ሕዝብ በታሪክ ውስጥ በገሃድ እንደሚታየው በማናቸውም ጊዜ ቢሆን ለውጭ ኃይልና ለውጭ ጠላት ለሐገሩ መዋረድና መደፈር መሳሪያ ሆኖ የማያውቅና የማይደለል ከመሆኑም በላይ በሐገሩና በሃይማኖቱ ጉዳይ ዐማራው አክራሪ ነው በመባሉ ነው፡፡ ዐማራን ማጥፋትም ለየት ያለና ራሱን የቻለ ሥልት የተቀየሰ ሲሆን፣ ዐማራው በጣላቱ ፊት ተባብሮ እንዳይቆም ለማድረግ በስም ከፋፍለው በተለይ የሸዋ ዐማራ ከምድረገጽ እንዲጠፋ ካልተደረገ በቀር
የጣሊያ ወረራ ጊዜያዊ ድል ከመሆኑ ባሻገር ሐገሪቱን በቅኝ ግዛትነት ለመያዝ አንችልም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰው በዚህ ዕቅድ ለመግፋት እንደወሰኑ በታሪክ የተረጋገጠ ነው፡፡"
(ምጽአተ ዐማራ፣ 526)

በተጨማሪም፣ በቅርቡ የጎንደር ዩኒቨርስቲ በወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት የተፈጸመውን ወረራና መዋቅራዊ ዘር ማጥፋት የምርምር ውጤት ይፋ ባደረገው መጽሐፉ እንዲህ ይላል፣

"ኢትዮጵያዊያን ለሉዓላዊነታቸው የሚሰጡት ትኩረት እንዲሁም ለሀገር ዳር ድንበር ሲሉ በኢትዮጵያ ጠላቶች ላይ ያስመዘገቧቸው አንጸባራቂ ድሎች በአለም ላይ ወዳጅ ያፈሩትን ያክል፣ ጥቂት የማይባሉ ጠላቶችንም ፈጥረዋል፡፡ እነዚህ ጠላቶች በሁለት መልኩ ኢትዮጵያ ላይ ክስ ያቀርባሉ፡፡ አንደኛ ኢትዮጵያ የራሷን ሀብት የውጭ ሀይሎች እንዳሻቸዉ ገብተው እንዲዘርፉና ወደ አገራቸው እንዲያግዙ አለመፍቀዷ ሲሆን፤ ሁለተኛ ደግሞ ቅኝ ገዥዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአድዋ ጦርነት ላይ ማንበርከኳ ለመላ ጥቁሮች የነጻነት ትግል እንዲቀጣጠል፣ በአፍሪካና ላቲን አሜሪካ አህጉሮች ውስጥ በቅኝ ተገዢነት ሲሰቃዩ የነበሩ ሕዝቦች ቅኝ ገዢን ማሸነፍ ይቻላል የሚለውን ስሜት መፍጠሩ ነው፡፡ እነዚህ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማንበርከክ ዋናው ዋልታና ማገር ሆኖ አገሪቷን የያዛት የትኛው ሕዝብ እንደሆነ ቀድመው መረጃ በመሰብሰብ፣ ጥናት በማድረግ፤ 'ኢትዮጵያን ማሸነፍ ወይም መበተን ከሚቻልባቸው መንገዶች አንዱ የአማራን ሕዝብ በማጥፋት ወይም በማዳከም ነው' የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ጠላቶች የዐማራን ሕዝብ ለማጥፋት ወይም ለማዳከም የተለያዩ ስልቶችን ነድፈው ተንቀሳቅሰዋል፡፡" (ጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ 1)

ኢምፔሪያሊስቶች ዐማራ የሚባል ታላቅ የሃገር ጉልላት ማፍረስ የፈለጉበት ምክንያት ከላይ እንደተገለጸው ዐማራ አገር ወዳድ፣ ለማንም የማይበረከክ፣ የአገሪቱን ሀብት የማያስነካ፣ በራሱ ባህልና ታሪክ የሚመካ እና ዐድዋ ላይ የአውሮፓን ቅኝ ገዥ ኃይል ቅስም ሰብሮ የመለሰ
ምርጥ አርበኛ ሕዝብ በመሆኑ በዘንዶ አይናቸው ውስጥ እንዲገባ አድርጓታል።


የአሜሪካ ሴኔት “የዐማራ ነገድ ጨቋኝ፣ ፀረ-ምዕራባዊያን አመለካከት ያለውና የአውሮፓውያንን ክብር ያሳጣ" ብሎ ያምናል። ይህ ፀረ- ዐማራ አመለካከት አብዛኞቹ ምእራባዊያን ፖለቲከኞች የሚጋሩት ነው። ለዚህ ምክንያት ደግሞ ኢትዮጵያ ጂኦ-ፖለቲካሊ እስትራቴጂክ ሃገር በመሆኗ ነው።

ዚቢነው ብሬጅንስኪ፤ የአሜሪካ የደህንነት አማካሪ፤ ሶቭየቶችን በመጥላት፤ ለሶቭየቶች አጎብዳጅ የሆኑትን፤ “ኩባን፤ አንጎላን፤ ኢትዮጵያን፤ ወዘተ ማድከም አለብን ብሎ ነበር። (ድርጅታዊ ምዝበራ፣ 56) በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ታሪክ ውስጥ ከዝነኞቹ ቀዳሚው ዶክተር ሄንሪ ኪሲንጀር ነው፡፡ ሰውየው በፕሬዚዳንት ሪቻርድ ኒክሰን እና ጄራርድ ፎርድ ዘመን የአሜሪካ መንግስት የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆኖ የሰራ ሲሆን በ1960'ዎቹ "ቀይ ባህር ለጦር ሥልት ያለው ጥቅም" የሚል ለአሜሪካ መንግሥት ጥናቱን አቅርቦ ነበር።

"ኢትዮጵያ ሰላም ካገኘች ሕዝቧ ሠራተኛና ታታሪ ስለሆነ፣ በዓለም ብድር ዕዳም እንደ ሌሎቹ የሦስተኛ ዓለም አገሮች ተዘፍቃ የማታውቅና የኮራች አገር በመሆኗ አንድ ቀን ራሷን የቻለች አገር ትሆናለች፡፡ ዕድል አግኝታ በዘመናዊ ሥልጣኔ ብትገፋ ደግሞ የምትቻል አገር አይደለችም፡፡ ስለዚህ ከንጉሥ ኃይለ ሥላሴ በኋላ ኢትዮጵያን የሚመራ መንግሥት ሰላም እንዳያገኝ፣ አገሪቱም እንደ ዓረብ አገሮች ተከፋፍላና ተነጣጥላ መበታተን አለባት፡፡ ለወደፊት በቀይ ባህር አሜሪካ የምትጫወተው ሚና እንዳይመነምን፣ መደናቀፍ ከሚገባቸው በቀይ ባህር አዋሳኝ ካሉ ታዳጊ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆን አለባት፡፡

"የቀይ ባህር ወተት የሆነውን የዓረብን ነዳጅ በነፃ ያለ ቀረጥ ማለብ የምንችለው መንግሥታችን ኢትዮጵያን ከጎረቤቷ ከሱማሊያ ጋር ብቻ ሳይሆን፣ ክፍለ ሀገሮቿን ራሳቸውን በሰሜንና በደቡብ ከፋፍሎ፣ የደከመውን ወገን በመርዳት ያላመፀውን ጎሳ በመነሳሳት፣ በዳር ድንበሯ ዘለዓለም ሁከትና ጦርነት እንዳይለያት በማድረግ ፀረ መንግሥት ተዋጊዎችን በሲአይኤ በማደራጀት ሰላም መንሳት ያስፈልጋል፡፡

"የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንካራና ብርቱ ቢሆንም ቅሉ፣ በሥልጣን ፍላጎቱ ደካማ ጎን አለው፡፡ አንዱ በሌላው ላይ መንገሥ ዋና ምኞቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያን በታሪካቸው ዴሞክራሲያዊ መንግሥት መሥርተው አያውቁም፡፡ ከጥንት ጀምሮ ቢሆን አንዱ ንጉሥ ሌላውን በመግደል ሥልጣን መቀማማትና ማመፅ ባህላቸው፣ ልማዳቸውና ታሪካቸውም ነውና፡፡ እኛ ያሳደግነው ውሻም ቢሆን ሊነክሰን ቢሞክር የመንግሥት ግልበጣ በማካሄድ፣ ለአንዲት ዘመን እንኳ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሰላም መኖር የለበትም፡፡ ሰሜናዊና ደቡባዊ፣ እንዲሁም ኤርትራ፣ ትግሬ፣ ዐማራ፣ ኦሮሞ እየተባባሉ እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ለረዥም ጊዜ ከኖሩ፣ ቀይ ባህር ለአሜሪካ መንግሥት ጠቃሚ በር ሆኖ ይኖራል፡፡"
(ሪፖርተር፣ ታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም.)