Get Mystery Box with random crypto!

እስኪ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ትግል ለማካሄድ እንዲረዳን ዛሬ ደግሞ የኦስትሪያዊ ባሮን ሮማን ፕሮ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

እስኪ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ትግል ለማካሄድ እንዲረዳን ዛሬ ደግሞ የኦስትሪያዊ ባሮን ሮማን ፕሮችስካ መጽሐፍ ልጋብዛችሁ። ለሌሎችም ሼር አድርጉት።

ከምዕራባውያን ሰላዮች መካከል አንዱ በጃን ሆይ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖር የነበረው ኦስትሪያዊ ባሮን ሮማን ፕሮችስካ ነው። ፕሮችስካ የጣልያን ወግንና የነበረው የጀርመን ናዚስት ብዕረኛ የነበረ ሰው ነው። ይህ ግለሰብ ጥልያን ኢትዮጵያን ከመውረሯ በፊት ለሁለት ዓመታት ያህል በአዲስ አበባ የኦስትሪያ ቆንስላ ውስጥ ተቀምጦ በኢትዮጵያ ይኖሩ ለነበሩ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች አማካሪ፣ በሌላ ሥራ ላይ ለተሰማሩ የውጭ ዜጎች የሕግ አማካሪና ጠበቃ ሆኖ እየሠራ ጎን ለጎን አውሮፓውያን ኢትዮጵያን እንዴት ሊወሩና ሊይዙ እንደሚባ ጥናት ያካሄድ ነበር። ኢትዮጵያን መቆጣጠር የሚቻለው ዐማራ የሚባለውን ጀግና ህዝብ ማዳከም ሲቻል ብቻ መሆኑን፣ ዐማራውን ለማዳከም ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ ነገዶችንና ጎሣዎችን በዐማራው ላይ ማነሳሳት እንደሚገባ፣ ይሄን የጥናቱን ውጤት ደግሞ በአውሮፓ በሚታተሙ ጋዜጦች እያወጣ ጥልያን፣ እንግሊዝና ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በዚህ ጥናት መሠረት እንዲመሩ ከፍተኛ ቅስቀሳ ያደርግ ነበር። በዚህም ምክንያት ጥልያን ኢትዮጵያን ከመውረሯ ሁለት ዓመት ቀድሞ በንጉሡ ትእዛዝ ኢትዮጵያን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። ይህ በዐማራ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ የነበረው ሰው ወደ አውሮፓ ከተመለሰ በኋላ በ1927 ዓ.ም. ቪየና ላይ ጥናታዊ ስትራቴጂካዊ ሀሳቡን ወደ መጽሐፍ በመቀየር "Abyssinia the Powder Barrel” ወይንም "ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል" በሚል ርእስ አሳተመ።

ይህ መጽሐፍ የጣልያን ወረራ ከመጀመሩ አንድ ዓመት በፊት በ1927 ዓ.ም 'Abissinia Pericolo Nero' ወይንም "አቢሲንያ ጥቁሯ ሥጋት" በሚል ርእስ በጣልያንኛ ተተርጉሞ ወጣ። ከላይ እንደገለፅነው የመጽሐፉ ዋና ማጠንጠኛ የአድዋ ጦርነት ድል ነጮችን እንዲንቁ እንዳደረጋቸው፣ ነጮችን የሚጠሉ ሕዝቦች ያሉባት፣ የነጮች ክብርና መብት የማይጠበቅባት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ነገዶችና ጎሳዎች ከአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ሊያገኙት የሚገባቸውን ጥቅሞች በዐማራ ኃያልነት ምክንያት እንዳጡ፣ በዚህም ምክንያት በምዕራባዊያን ኢምፔሪያሊስቶች በሞግዚትነት መተዳደርን እንደሚመርጡ ማስረጃ የሚለውን ሁሉ እየጠቀሰ ለማስረዳት ይሞክራል፡፡

ሀገሪቱን ለማስተካከል ሦስት መፍትሔዎችን ያቀርባል፡፡ ኢትዮጵያን በአውሮፓ ቀንበር ለማናቅ አስተዳደሩን በቋንቋና በጐሣ መሠረት አወቃቅሮ መከፋፈል እና አገሪቱን በቅኝ ግዛት ለመያዝ ዐማራዎች ማስወገድ በዋናነት ያስቀምጣቸዋል።


ባሮን ሮማን ፕሮችስካ የዐማራ ነገድ አፍሪካን ጠቅልሎ በቁጥጥር ስር ከማዋል አልፎ ለነጭ ዘሮች የማይመለስ ኃይል መሆኑንና፣ ይሄን አስፈሪ ነገድ ነጮች ተባብረው አስቸኳይ እርምጃ ካልወሰዱበት የሚያቆመው ስለማይኖር ለማዳከም በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ነገዶችና ጎሣዎች እንዲነሱበት ፖሊሲ ቀርፀ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ማሳሰቡን ተከትሎ፣ የተለያዩ የምዕራባውያን ፖሊሲ አውጭዎች የዐማራን ህዝብ ለማጥፋት ወይንም የነፃነት ስነ-ልቦናውን ለመስበር፣ ላለፉት 70 እና 80 ዓመታት በኢትዮጵያ ላይ ለሚያወጡት ፖሊሲ መጽሐፉን እንደ ግብአት ሲጠቀሙበት ኖረዋል።

የጥሊያኑ ፕሮፖጋንዲስት ፕሮችስካ "መታሰብና መታወስ ያለበት ጉዳይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩት አብዛኞዎቹ ሕዝቦች ተጨቋኞች ናቸው፤ ጨቋኟቹ ገዢዎች ደግሞ ዐማሮች ናቸው" (Abyssina The powder Barrel፣ 79) ብሎ የጻፈውን የ60'ዎቹ ታጋዮች የትግል ፍኖተ ካርታ፣ የማታገያ ማኒፌስቶ የሚቀዳበት "ሰፊ ምንጭ" አድርገው ተጠቀሙበት። ኢትዮጵያዊው ሂትለር ዋለልኝ መኮነን ደግሞ "የኢትዮጵያዊነት ትርጓሜ የዐማራ ገዢ መደብ ፍልስፍናን የማጉላትና ኢትዮጵያዊ ማለት አማርኛ የሚናገር፣ ክርስቲያን የሆነና ሸማ የሚለብስ ነው" በማለት የፕሮችስካን ቀኖና ገልብጦ አሳትሞታል።

የዋለልኝ "የብሔሮች ጥያቄ በኢትዮጵያ" የሚለው መጽሐፍ ለፋሺስት ጥሊያን የአምስት አመታት አገዛዝ እንደ መመሪያና ማንዋል ያገለገለው፣ “አቢሲኒያ ፔሪኮሎ ኔሮ” የሚለው የባሮን ፕሮችስካ ፀረ-ዐማራ መጽሐፍ የካርቦን ግልባጩ ነው ምንም ልዩነት የለውም። በፕርችስካና በዋለልኝ መካከል ቢያንስ የ34 ዓመት ልዩነት አለ። ፕሮችስካ መጽሐፉን የጻፈው በ1927 ዓ.ም. ሲሆን፣ በጀበሃ ዋለልኝ የታተመው መጽሔት እና መጽሐፍ ደግሞ በ1961 ዓ.ም. ነው።

ፋሺስቶች ዐማራን ነጥለው ለማጥፋት የቀየሱት የጎሳ ንድፍ ከጥልያን ሽንፈት ጋር በ1933 ዓ.ም. ቢያከትምም፤ የጥሊያንን ቅያስ ከተቀበረበት አንሥተው እንደገና ለአዲስ ሕይወት ያበቁት እንዲሁም በቀጣዩ ዘመን ለዐማራ ማኅበረሰብ በአቋራኝ የችግር ቀለበት (vicious circle) ውስጥ እንዲገባ የፖለቲካ ፈንጅ ያጠመዱት ሻቢያና ህወሓት ናቸው።

ለማንኛውም መሐፉን ከስር አስቀምጬዋለሁ። እንግሊዘኛውንና ደበበ እሸቱ የተረጎመውን አማርኛውን። ከሁለት አንዱን አውርዳችሁ አንብቡት። ዛሬ የእረፍት ቀን ስለሆነ እስከማታ ትጨርሱታላችሁ ገፁ ትንሽ ነው።

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut