Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት ይሁን! ራስ መኮነን ከሐረር ይዞት የዘመተው ከ15 በላይ ጦር በአብዛኛው የጎንደር ዐ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት ይሁን! ራስ መኮነን ከሐረር ይዞት የዘመተው ከ15 በላይ ጦር በአብዛኛው የጎንደር ዐማራ መሆኑን በቀደም ገልጬ ነበር። ይህንም በሁለት የዘመኑ የዐይን ምስክር ጽሐፊዎች ተረጋግጧል። የመጀመሪያው የራሳቸው የራስ መኮነን ዜና መዋዕል ጸሐፊ ግራጌታ ኃይለጊዮርጊስ በለጠ ሲሆኑ፣ ሁለተኛው ደግሞ በራስ መኮነን ቤተመንግሥት ያደገው ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም ናቸው።

ግራጌታ በግእዝ ቋንቋ በጻፉት ዜና መዋዕል አብዛኛውን የራስ መኮነን ሠራዊት የጎንደር ወታደሮች እንደነበሩ ጠቅሰዋል። የጎንደር ዐማራ ወታደሮችን ከራስ መኮነን ጋር በሐረር እንዲቀመጡ ያደረጉት ዳግማዊ ምኒልክ ናቸው።
ግእዙ በአማርኛ ሲተርጉም እንዲህ ይላል፣

". . . ከዚያም ዳግማዊ ምኒልክ ከደጃዝማች መኮንን ጋር የተዋቸውን የጎንደርን ወታደሮች 'ከልጄ ከደጃዝማች መኮንን ጋር በፍቅር ተቀመጡ፡ እንደ መንፈሳዊ ድንጋይና እንደ ንጉሥ ታቦት ጽኑ፡ ከብዙዎቹ የመንግሥቴ ሰራዊት እናንተ ተመርጣችኋልና" አላቸውም። ደጃዝማች መኮንንም "አንተም እንደ ዓይን ብሌን ጠብቃቸው፤ እነሱ እንደ እጅና እነ እግር ይሁኑህ" አሏቸው። ንጉሠችን ምኒልክን ይህንን ተናግረው ወደ ሸዋ ተመለሱ፤ በሰላም በደኅና ሸኙዋቸው"
(ዜናሁ፡ ለልዑል፡ ራስ መኮንን፣ 24-25)

ምኒልክ ወደ ሐረር በአቀኑ ግዜ ነበር የጎንደር ወታደሮች ከሌላው ሠራዊት ተመርጠው ከደጃዝማች መኮንን ጋር በሐረር እንዲቀመጡ ያደረጉት። ደጃዝማች መኮንንም እንደ ዐይኑ ብሌን እንዲንከባከባቸው ነግረው ከሐረር ወደ ሸዋ ተመልሰዋል። ከስድስት ዓመት በኋላ ራስ መኮነን በ1888 ዓ.ም. ወደ አድዋ ይዞ የዘመተው ጦር በሐረር የነበረውን የጎንደር ዐማራ ሠራዊት አሰልፎ ነው።

ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያትም በጻፉት ኦቶባዮግራፊያቸው ይሄንኑ ያረጋግጣሉ። የሐረር ሠራዊት ቀዳሚው ጎንደሬ እንደሆነ፣ በሐረር የጎንደሬዎች እንደራሴ ግራዝማች ጎሹ እንደሚባል፣ እንዲያውም ለፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ደጃዝማች ጎሹ "ጎንደሬ ለተፈሪ መክቶ ይሞታል። ለዚህ እኔ አለሁ" ብሎ በአንደበቱ እንዳረጋገጠለት፣ ተክለሐዋርያትም ግራዝማች ጎሹን "እንማማል" ሲለው፤ "ብከዳ ምድር ትክዳኝ" ብሎ እንደማለለት ጽፈዋል። (ኦቶባዮግራፊ፣ 284-285)

በነገራችን ላይ ግራዝማች ጎሹ የዐፄ ቴዎድሮስ ወታደር ነበሩ። የትውልድ ስፍራቸው ቋራ ነው። በአድዋ ጦርነት ቆስሎ በሕይወት የተረፈው እና በ1927 ዓ.ም. ኦጋዴን ወልወል ላይ መሰዋት የሆነው የፊታውራሪ አለማየሁ ጎሹ አባትም ናቸው።

ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ ወድቆ ጦራቸው ሲበተን ጎሹ ወደ ሸዋ ተሻግሮ ምኒልክ ያደራጁት "ጎንደሬ" የሚባለው የዐፄ ቴዎድሮስ ወታደሮች ሻለቃ መሪ ነበሩ። ምኒልክ ለራስ መኮነን በሐረር ጠባቂ እንዲሆኑት የተውለት ይህን ታማኝና ምርጡን የጎንደሬ ሠራዊት ነበር። የዚህ ሠራዊት መሪ ደግሞ የቋራው ግራዝማች ጎሹ ሲሆን፣ በራስ መኮነን ስር ሆኖ የሐረር ሠራዊት ቀዳሚ የሆነውን የጎንደሬ ጦር እየመራ ወልወል ላይ መሰዋት የሆነው ልጁን አለማየሁን አስከትሎ ወደ አድዋ ዘምቷል።

ይህ እውነተኛ ታሪክ ገና አልተጻፈም። በራስ መኮነን መሪነት ወደ አድዋ ዘምቶ ኅዳር 28 ቀን 1888 ዓ.ም. አምባላጌ ላይ፣ ታኅሳስ 1888 ዓ.ም. መቐለ ላይና በመጨረሻም የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. አድዋ ላይ የተዋደቀው የሐረር ዘማች ጎንደሬ ዐማራ ገድል ገና አልተነገረም። በራስ መኮንን እየተመሩ ከሐረር ተነስተው ወደ አድዋ ከዘመቱት የጎንደር ዐማራ ጦር ከሚታወቁ ዝነኛ መሪዎቹ መካከል ግራዝማች ጎሹ፣ ፊታውራሪ ዓለሙ፣ ፊታውራሪ ኮላሴ ብሩ፣ ልጃቸው ልጅ አበበ ኮላሴ፣ ቀኛዝማች ወልደ ጻዲቅ ታሪክ ገና አልተጻፈም። (ኦቶባዮግራፊ፣ 55) በጣም የሚያስገርመው በ1928 ዓ.ም. በኢትዮ-ጥሊያን ጦርነት ወቅት የጎንደሬው ዐማራ የአድዋው ዘማች የፊታውራሪ ኮላሴ ልጆች ፊታውራሪ ጓንጉል ኮላሴና ወንድማቸው ኃይለማርያም ኮላሴ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ታንክ የማረኩ መሆናቸውን ጳውሎስ ኞኞ መዝግቧል።

ምንጭ፦
-ግራጌታ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘሐረር፣ ዜናሁ ለልዑል ራስ መኮንን፣ በ1965 ዓ.ም. በአርቲስቲክ ማተሚያ ሊሚትድ.

-ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም (ፊታውራሪ)፣ ኦቶባዮግራፊ፣ 2007 ዓ.ም. 4ኛ ዕትም. አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ.

#ጥቆማ በዚህ አጋጣሚ ሆን ተብሎ እንዲጠፋ የተደረገው የግራጌታ ኃይለ ጊዮርጊስ "ዜናሁ ለልዑል ራስ መኮነን" የግዕዝ መጽሐፍ ቴሌግራም ላይ በpdf ጭኘዋለሁ አውርዳችሁ ማንበብ