Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! ይደንቃል ...ሕወሓት ከሽብርተኝነት መሰረዙን ሰማን... ሕወሓት 7,003 የሚሆኑ ዐ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! ይደንቃል ...ሕወሓት ከሽብርተኝነት መሰረዙን ሰማን... ሕወሓት 7,003 የሚሆኑ ዐማሮች በጦርነቱ ምንም አይነት ተሳትፎ ሳይኖራቸው ህጻናት፣ ነፍሰጡሮች፣ አጥቢ እናቶች፣ አቅመደካሞችን፣ አረጋዊያንን፣ የሀይማኖት አባቶችንና አካል ጉዳተኞችን መስማት የተሳናቸውን፣ ማየት የተሳናቸውን፣ የመንቀሳቀስ እክል ያለባቸውን፣ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ሳይቀር ያለርህራሄ ጨፍጭፏል ግን ከደሙ ነፃ ነው ተብሏል።

ሕወሓት፣ 18,496 ዐማሮች ሴቶች፣ ህጻናት፣ እመጫት እናቶች፣ የአካል ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካማ ሽማግሌዎች ብሎም የሀይማኖት አባቶችን ጭምር ምግብ እና ገንዘብ አምጡ፤ ትጥቅ ደብቃቹሀል፤ መከላከያን ሸሽጋቹሀል፤ የፋኖ፣ የሚኒሻና የአመራሮችን ቤት ጠቁሙ በማለት በእርግጫና በመሳሪያ ሰደፍት ምት፣ የፊጥኝ አስረው በጩቤ በመተልተል፣ ጥይት ተኩሶ በማቁሰል፣ አስሮ በመጎተት፣ "ዐማራ፣ ዐማራ ምንድነው? ዐማራ አ*ህ*ያ ነው?" እያለ በተደጋጋሚ ባደረሰባቸው ጥቃት ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ገና ቁስላቸው ሳይደርቅ ሕወሓት
ከሽብርተኝነት መዝገብ ተሰርዟል።

-በሕወሓት፣ 1968 ዐማሮች.. ህጻናት፣ እመጫት እናቶች እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች የትዳር አጋር እንዲሁም መነኩሴዎች ሳይቀር ተገደው ተደፍረዋል፣ ከነዚህ መካከል 29'ኙ ወንዶች ግብረሰዶም ተፈጽሞባቸዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በምርመራው እንዳረጋገጠው፣ ጭና ቀበሌ አንድን አባት ከገደሉ በኋላ የ7 ዓመት ሕፃን ልጃቸውንም “ይህ አድጎ ነው የሚወጋን" ብለው በእናቱ ፊት በጥይት ተኩሰው ገድለውታል። ሕወሓት ግን ሽብርተኛ አይደለም ተብሏል።

-በሸዋሮቢት ከተማ የቀበሌ 02 ነዋሪ የሆኑ ዓለም በቃኝ ብለው ሥጋቸውን እና ነፍሳቸውን ለፈጣሪ የሰጡ የ85 ዓመት መነኩሴ በተኙበት በውድቅት ሌሊት አንድ የትግሬ ወ*ን*በ*ዴ በር ሰብሮ ከገባ በኋላ በጥፊ መታት እማሆይ መሬት ላይ ሲወድቁ ደግሞ ይህ ሰው መሳይ የትግሬ አ*ው*ሬ ጭንቅላቸውንና ሆዳቸውን ደጋግሞ እረገጣቸው። በዚህ አላበቃም አስገድዶ ደፈራቸው፤ ምንኩስናቸውን አረከሰው። እማሆይ ከተደፈሩ በኋላ በማግሥቱ ሙሉ ቀን በማህጸናቸው ደም ሲፈሳቸው ዋለ። እኚህ እናት ዛሬ የምንኩስና ቆባቸውን አውልቀው ዘመድ እንደሞተበት ሰው ጥቁር ማቅ ለብሰው የሞት ቀናቸውን የሚጠባበቁ አዛውንት ሆነዋል። ሕወሓት ግን ከሽብርተኝነት ተሰርዟል።

በሕወሓት በተወረሩ በስምንቱም ዞኖች ማለትም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ወሎ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በዋግኽምራ ብሔረሰብ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በሰሜን ጎንደር፣ በደቡብ ጎንደር፣ በጥቅሉ፦

-594,943 የግለሰቦች ቁስ በሳር፣ በቆርቆርና በብልኬት የተሰሩ ቤቶችን ጨምሮ አውድሟል፤ ዘርፏል።

- 1156 ቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሦስት ዩኒቪርሲቲዎች ወልዲያ፣ ወሎና መቅደላ አምባ
እና 55 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን ጨምሮ አውድሟል፤ ዘርፏል።

-በሁሉም የተወረሩ አካባቢዎች 184 የሚደርሱ ኢንዱስትሪዎች ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን፣ 666 የሚሆኑት በከፊል ወድመዋል። በጥቅሉ 824 የሚደርሱ ብረታብረትና እንጨት፣ የጨርቃጨርቅና የቆዳ፣ የአግሮ ኢንዱስትሪና ኬሚካልና የግንባታ ግብዓት ኢንዱስሪዎች በሕወሓት ሙሉ በሙሉና በከፊል ወድመዋል።

- በኢንቨስትመንት ዘርፎች በኢንዱስትሪ፣ ንግድ፣ ግብርና፣ ማህበራዊ እና ሌሎች 1775 ኢንቨስትመንት አውድሟል፤ ዘርፏል።

- በቱሪዝም ዘርፍ ሕወሓት 868 ቅርሶች ላይ ውድመት አድርሷል፤ ከዚህም ውስጥ 457 ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ሲሆኑ፣ 190 የክርስትናና የእስልምና እምነት ተቋማትን ዘርፏል፣ አቃጥሏል፣ አውድሟል። ዐፄ ምኒልክ ከጅቡቲ እና ከፈረንሳይ መንግስታት ጋር ግንኙነት ያደረጉበት የስልክ ቀፎ፣ በአድዋ ጦርነት ጊዜ ያገለገሉ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች፣ በ1890 ከፈረንሳይ መንግሥት የተበረከተው መድፍ፣ በኢትዮ-ጥልያን ጦርነት ጊዜ በኢትዮጵያዊያን የተማረከው የአየር መቃወሚያ፣ ዳግማዊ ምኒልክ አድዋ ላይ የተዋጉበት የጦር ጎራዴ ከደሴ ሙዝየም ሰርቆ ወስዷል።

-በስምንቱም ዞኖች 653 የተለያዩ የጤና ተቋማትን 297 ጤና ኬላዎችን፣ 272 ጤና ጣቢያዎችን፣ 30 የመጀመሪያ እና ጠቅላላ ሆስፒታሎችን፣ አንድ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ 25 የግል ክሊኒኮችንና 21 ፋርማሲዎችን፣ 4 የደም ባንኮችን፣ አንድ የኦክስጅን ማምረቻ፣ አንድ የጤና ተቋም፣ በክልሉ ብቸኛ የሆውን የዐማራ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የደሴ ቅርንጫፍ ዘርፏል፤ አውድሟል።

- በ8 ዞኖች 37,516 እንስሳቶች በጥይት ገድሏል፣ 174,708 ዘርፎ ወስዷል፣ አርዶ የበላቸውና ትራፊያቸውን ወደ ሜዳ ለውሻ ለአራዊት የጣላቸው 92,944 ሲሆን፣ በጥቅሉ 305,168 የእንስሳት ቁጥር አውድሟል።

በጥቅሉ ሕወሓት በቤተሰብ ጥሪት፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት፣ የግል ድርጅቶች፣ እንዱሁም የመሰረተልማት አውታሮች ላይ ባደረሰው መጠነ ሰፊ ጉዳት በጥቅሉ ሲተመን 291,816,377,952.78 (ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ አስራ ስድስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ሦስት ብር) ነው። ግን ከሽብርተኝነት ተሰርዟል።

ወዳጄ...አየህ አይደል ኢትዮጵያ በዐማራ ኪሳራ የቆመች ሀገር ናት። ዐማራን በጨቋኝነት የፈረጀው ህገመንግስት እንዲቀየር 5 ዓመት ሙሉ ጠይቀህ ምላሽ የሰጠህ የለም።ከጉራፈርዳ እስከ ማይካድራ ለፈሰሰው የዐማራ የደም ተጠያቂ የለም።